ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
አምሳሉ በላይ ማን ነው??

ማሳሰብያ፤…ስለ ታላቅ ወንድሙ አላምረው በላይ አጭር የትግል ታሪክ በቅርቡ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
በአብሮ እደጉና የትግል ጓዱ ተቀባ በየነ እንደተነገረው፤….…
አምሳሉ በላይ ከአባቱ ከ ሀምሳ አለቃ በላይ ወንዴ እና ከእናቱ ወ/ሮ ሙሽሪት… በጎንደር አዘዞ ቀበሌ 20 ተወለደ። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ አንደኛና መለስተኛ ደርጃ ትምህርቱን በአፄ ፋሲል ት/ቤት ገብቶ ተከታትሏል። በትምህርቱ በጣም ጎበዝ፤ ብሩህ አዕምሮ ፤ በጣም ተግባቢና ሰውን አክባሪ የነበረው አምሳሉ በላይ ኢሕአፓን ተቀላቅሎ ለፍትህና ዴሞክራሲ መታገል የጀመረው በእድሜው ገና ወጣትና 14 ዓመቱ ሆኖ ነው።
አምሳሉ በላይ፤ የታላቅ ወንድሞቹን ፈለግ በመከተል እንደዘመኑ የዛ እድሜ ወጣቶች፤ የልጅነት ዝላይ ሳያምረው የደርግን አንባገነናዊና ፋሺስታዊ ስርአት አስወግዶ ህዝባዊ ስርአት እንዲመሰረት በአላማው ፀንቶ ታግሏል፤ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል።
በኋላም በ ፓርቲው ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎና የፓርቲው እስኳድ የነበረው ታላቅ ወንድሙ አላምረው በላይ በመላኩ ተፈራ አራጆች እጅ ወድቆ በኋላም በግፍ ሲገደል፤ አምሳሉ በላይ ፀለምት የነበረውን የኢሕአሠ ሰራዊት ተቀላቅሎ ሲታገል ከቆየ በኋላ በ 1971 ዓ፣ም ከደርግ ጋር ሲዋጋ የመጨረሻ እልፈቱን በራስ ዳሽን ተራሮች ላይ አድርጓል።
ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!