April 21, 2020 

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/103858

ለውጥ ሥርዓትን በመቀየር ወይም በአዲስ በመተካት እንጅ ሰዎችን በሌሎች ሰዎች ወይም ደግሞ አንድን የፖለቲካ ማኅበር በሌላ በመተካት አይመጣም፤ አንዲህ ሆነ ማለት ደግሞ ያው የተለመደው ጉልቻ ቢለዎጥ ወጥ አያጣፍጥም ከሚለው ዛሬም አለመውጣታችን ያሳያል።

የሥርዓት ለውጥ የሚጀምረው የሥርዓቱ ቁንጮ የሆነውን ሕገመንግሥት ከመቀየር ነው። ሕገ-መንግሥታዊ ሽፋን የተሰጠው የህውሓት የከፋፍለህ ግዛው ትርክትም ፍሬያማነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ሚሊዮኖች በአገራቸው ላይ ባይተዋር ሆነው እንዲፈናቀሉ በማድረግም ኦነጋውያኑ ሕገ-መንግሥቱን በሚገባ ሥራ ላይ ማዋል ጀምረዋል፡፡

ምን ይሄ ብቻ ! ምን አልባትም ኢትዮጵያን እንደሶሪያ የሚያደርገውንና የኦነጋውያኑም ፍፃሜ የሚሆነውን በታሪካዊ ዳራውም በነባራዊ ሁኔታውም ፍፁም ተቀባይነት የሌለውን አዲስ አበባን የኦሮሚያ የማድረግ ቅዠትም ኦነጋውያኑ የሚመሩት ኦዴፓ በመግለጫም ጭምር በማስደገፍ ታሪክ የማይረሳው ጠባሳውን እያስቀመጠ ይገኛል፡፡