April 23, 2020

የፋኖ የጎበዝ አለቃ ጀግናው ሻለቃ መሳፍንት እና በመንግስት ተወካዮች አማካኝነት እረዘም ላለ ግዜ ሲደረግ የሰነባበተው ድርድር/ሽምግልና በዛሬው እለት በስኬት ተጠናቋል። ለዚህ ዋና ሃላፊነት ወስደው ከላይ ታች በማለት ከፍተኛውን ድርሻ የተጫወቱት የሃገር ሽማግሌዎች ናቸው።

ይህ አላስፈላጊ ፍጥጫ በሰላም ውይይት እንዲቋጭ ሁላችንም ስንወተውት ሰነባብተናል። በዚህ ወቅት በሃገር የጋራ ጠላት ጉዳይ ብቻ ላይ ነው ጦርነትም የግድ የሚሆን። ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ ባለመስጠቱ ስንወቅሰው የነበረው የመንግስት አካል አሁን ለተደረሰው ስምምነት በመድረሱ በዚሁ ቀጥሉ ልንል እንወዳለን።
ዳባት እንኳን እፎይ አልሽ!
ጎንደር ይህ የሰላምሽ መስፈን መሰረት ይሁንልሽ!
ሃሳብ ገብቶት የነበረው መላው አማራ ደስ ይበልህ!
ኢትዮጵያ በልጆሽች መሃል ደም አይፍሰስ ጠላቶችሽ ይከፉ!ይፋኖ ደጋፊዎች እንኴን ደስ አላችሁ።

ሙሉነህ ዮሃንስ