April 23, 2020

Posted by: ዘ-ሐበሻ

የሻብያው አንባገነን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂና የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ 15 በወህኒ ቤት 20 አመታት ሞላቸው!!!

‹‹በምን አወቅሽበት በመመላለሱ
ሲታሰር ወደ እኔ፣ ሲፈታ ወደ እሱ!!!››

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥት መርህ አልባ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የመከላከያ ኃይል ግንኙነት በጊዜው መልክ ሊይዝ ይገባል እንላለን፡፡  የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች መርህ አልባ የፖለቲካ ግንኙነትና የመቶ ዓመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ቀጣይ ፍንጮች ይስተዋላሉ፡፡

የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች በኤርትራም፣ በትግራይና፣ በኦሮሞ ስም አስሬ ቢምሉም ቢገዘቱም፣ የህዝቡ እጣ ፈንታ ሞት፣ እስራትና ስደት በቀር የተረፈው  ነገር የለም፡፡ የጦር አበጋዞቹና በስልጣን ሱስ በሰከሩ፣ አድርባይ ምሁራን በዴሞክራሲ ስም፣ በፌዴሮሽን ስም፣ በህገ-መንግሥት ስም በህዝብ ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  የጦር አበጋዞች ከህዝብ በዘረፉት ኃብትና ንብረት ተንደላቀው ይኖራሉ፡፡ ወያኔ ዘርፎ ትግራይ ገብቶል፣ ኦነግም ዘርፎ ወለጋ መሽጎል፣ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልጽግናም የመቶውን አመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ለማስፈፀም ላይ ታች ይላል፡፡  የፖለቲካው ሴራ ሲተነተን እንኮን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለክልላቸውም ህዝብ እንደማይበጁ እውነተኛ ማስረጃውን  እንሆ እንላለን፡-

ህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ  (ህግሓት) ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትነት ለመውጥት ሲታገል ቆይቶ በሜይ 24 ቀን 1993 እኤአ ነፃ ወጥቻለሁ ይላል፡፡ ሻቢያ  አንድ አውራ ፓርቲና ብቸኛ መንግሥት በመሆን ላለፉት 27 አመታት ሕገ መንግስትና ዴሞክራሲና ምርጫ  ገለመሌ የሚባል ዜና ፖለቲካና ሃተታ ሳይኖር በአንባገነንነት የገዛ የማፍያ ድርጅት ነው፡፡ የህግሓት መንግስት የስብዓዊ መብት ምህደር በዓለማችን ካሉት ነፃነት ደፍጣጮች የመጨረሻ ደረጃ ላይ  ይገኛል፡፡ የኤርትራ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃንና ፕሬስ ነፃነት በዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ማህደር በመጨረሻነት ከሰሜን ኮሪያን አፋኝነት ተርታ ተሰልፋለች፡፡ የኤርትራ መንግስት መርህ አልባ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች በማድረግ ከአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ኢጋድ እንዲሁም በአረብ ሊግ በታዛቢነት አባል መሆን ችሎል፡፡ ኤርትራ 117,600 ኪሎሜትር ስኩየር የቆዳ ስፋት ሲኖራት የቀይ ባህር የባህር በር አላት፡፡ ኤርትራ ህብረ ብሄር ሀገር ስትሆን የህዝብ የቌንቌ ስብጥር ዘጠኝ ዘውጌ ቡድኖች ይገኛሉ ከነዚህ ውስጥ፣ ትግርኛ 55 በመቶ፣ ትግረ 30 በመቶ፣ ሳሆ 4 በመቶ፣ ኩናማ 2 በመቶ፣ ቢለን 2 በመቶ፣ ራሻይዳ 2 በመቶ እንዲሁም የተለያዩ 5 በመቶ ዘውጌ ብሄር ብሄረሰቦች ቢኖሩም በዘር መደራጀትና እራስን በራስ እስከመገንጠል መብት የሚባል ገለመሌ የለም፡፡ በ2016 እኤአ የሥነ-ህዝብ ብዛት ቆጠራ 4,954,645 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሃገር ናት፡፡

ኢሳያስ አፈወርቂ ተቃዋሚ ፖለቲካ የነበሩትን ጂ 15 በመባል የሚታወቁትን የህሊና እስረኞች በአሰቃቂ ሁኔታ በማሰር በአለም ህብረተሰብ በአንባገነን ገዢነታቸው የሚታወቁ ሲሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ  የፖለቲካ ሴራ ጠንሳሽነትና ኦቦ አብይ አህመድ፣ አሽቃባጭነት ሊወድቅ ተንገዳግዶ የነበረው የኢሳያስ ፋሽስታዊ አገዛዝ እንደ እባብ አፈር ልሶ ዳግም ተነሳ፡፡

የጂ 15 የፖለቲካ እስረኞች The “G-15” Prisoners የኤርትራ አስራአንድ ከፍተኛ ሹማምንቶችና አስር ነፃ ጋዜጠኞች ከታሰሩ 20 አመታት አለፋቸው፡፡

These are the 11 government/party critics who were arrested and are believed to have been held in solitary confinement since September 2001. Five of them (designated by asterisks) are presumed dead based on credible reports discussed later in this report:1   

“The 20 men and one woman arrested in September 2001—11 high government officials and 10 independent journalists—have never been seen again. They have collectively come to be known as the G-15 because the original group of signatories to a manifesto critical of the government numbered 15. The government has provided no information about their whereabouts or conditions in the decade since their arrests. What is known about them has been garnered largely from information supplied by defectors who have fled the country. Kept hidden in a secret detention facility, 10 of the 21 have died in prison according to reports that Human Rights Watch has not been able to independently confirm. The others remain in solitary confinement, physically or mentally incapacitated, and emaciated. None of the 21 has been formally charged with a crime, much less convicted. Since the arrest of the journalists and closure of their newspapers, no independent news media have been allowed in Eritrea.”2

የኤርትራም ህዝባዊ ትግል በሻቢያ መርህ አልባ የአፍሪካ ቀንድ የበላይ የመሆን የፖለቲካ ሴራ የተነሳ ከጎረቤት አገራቶች ጋር ሁሉ ጠብያለሽ በዳቦ ሆነ፡፡ ሻብያ ከየመን በሃኒሽ ደሴት፣ ከጅቡቲ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳን ወዘተ ጋር አንባጎሮ ገጠመ፣ በዚህም የተነሳ ከዓለም አቀፍ ማህበራት ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቶቹ ተበጣጠሱ፡፡ የሻብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የአፍሪካ ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጁንግ ኡንንነት ተፈረጁ፡፡ በመለስ ዜናዊ ዘመን ኤርትራ በአሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና የጦር መሳሪያ ግዝ ማዕቀብ ተጣለባት፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከጦርነቱ በኃላ ኢኮኖሚያው ቀነጨረ፣ የመከላከያ ሠራዊታቸው አከርካሪው ተመታ፣ የስብዓዊ መብትና ጥሰትና የዴሞክራሲ አፈና ተስፋፋ፣ ሞት፣ እስራትና ግርፈት መጨቆኛ መሳሪያቸው ሆነ፡፡  ህዝባቸውም ተስፋ በመቁረጥ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ላለፈው ሁለት አስርታት ተሰደደ፡፡ የወጣቱ መፈክር ‹‹ለመኖር ሂድ/ተሰደድ!!›› ሲሆን በአንፃሩ የድንበር ጠባቂው ወታደር ‹‹ተኩስ ለመግደል!!›› ይላል፡፡ በ2011 እአኤአ 222,000 የኤርትራ ስደተኞች ከህዝቡ ቁጥር 5 በመቶ የተሰደደ ሲሆን በየወሩ 3000 ሽህ ወጣቶች ድንበር አቆርጠው ይሰደዳሉ፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ለህዝቡ ያበረከተው ገፀ በረከት ይሄ ሲሆን ከዚህ የማይማሩ የእኛ ዘረኛ የጦር አበጋዞች ህወሓት ትግራይን ገንጥሎ ህዝቡን በምድር ሲኦል እንደሚከቱት ይታወቃል፣ ኦነግ ኦሮሚያን ገንጥሎ ህዝቡን በምድር ሲኦል እንደሚከቱት ይታወቃል፡፡ “Despite the mortal danger of trying to escape the country, Eritrea’s most significant export over the past decade has been its fleeing citizens. Eritrea’s youths have adopted a secret motto: “Leave to live!” Despite border guards’ shoot-to-kill orders, the exodus persists. Over 222,000 Eritreans (almost five percent of the population) had fled the country as of January 2011, with about 3,000 fleeing per month.”

የኢትዮጵያና የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አንድም ቀን ከኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ህዝባዊ ትግል ጎን ቆሞው መለስ ዜናዊን ወይም ኢሳያስ አፈወርቂን ሲቃወሙ ተሰምተው አይታወቅም፡፡ የኢሳያስን ፋሽስታዊ አገዛዝ ዲሞክራቶቹ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ እያወደሱ ወያኔን ‹‹ነጻነትን የማያውቁ ነፃ አውጭዎች›› እያሉ ሻብያን ያለማለት ማፍያዊ መርህ አልባ አቆም ነው እንላለን፡፡ የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ15ቶች  ላይ የሚደርሰው የስብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የዴሞክራሲያዊ መብቶች አፈና፣ የግፍ እስራት ዓለም ሲያወግዘው እናንተ የኢሳያስ ቡችሎች ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ፣ ደህሚት፣ ወዘተዎች አሳፋሪ አቆም በታሪክ ያስጠይቃል፡፡ ኤርትራ በርሃ እያላችሁ ‹‹ ባትዋጋ እንኮን በል እንገፍ እንገፍ፣ የአባትህ ጋሻ ትሆኑ ይርገፍ!!!›› ተብሎ ተዘፍኖላችሁ ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ቀን ሳትደርሱለት፣ እንደ ሳይላክ የቀረው ደብዳቤ ‹‹ሳይዘምት የተመለሰው ነፃ አውጭ›› ብሎ ግንቦት 7 ይጻፍላችሁ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች የጋራ ህብረት ፈጥረው ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲና እኩልነት ቢታገሉ ኖሮ የሻብያና የወያኔ አንባገነን መሪዎች አገዛዝ በአጭር ይቀጭ ነበር  እንላለን፡፡

በኢኮኖሚ ዘርፎች ሻብያ ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፎ ያስቀረው ኃብትና ንብረት ለናሙና፡-

የኤርትራ ህዝብና የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ጂ 15 ጥያቄዎች አንኮሮቹ ውስጥ፤-በኤርትራ  የስብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ በኤርትራ  የፕሬስ ነፃነት  እንዲከበር፣ በኤርትራ  ህገመንግስት አረቆ እንዲፀድቅ፣ በኤርትራ  ህዝባዊ ምርጫ እንዲካሄድ ይጠይቃሉ፡፡ መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዘብ ለዝንተ ዓለም አብረው የኖሩ ናቸውና፡፡

ምንጭ (መታየት ያለባቸው ዩቲዩብ ቪዲዬዎች )

1- https://www.hrw.org/report/2011/09/22/ten-long-years/briefing-eritreas-missing-political-prisoners

2-https://www.youtube.com/watch?v=Dujr-s9uQPE / Eritrea: Political Prisoners

3-https://www.youtube.com/watch?v=h61Zfm5uyb0 /Nevsun in Eritrea : Dealing With a Dictator – the fifth estate