ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ወያኔ/ኢሕአዴግ አሸባሪ ታጣቂዎቹን የኦሮሞ ክልል በሚለው ሦስት የተለያዩ ዞኖች፣ በሐረርና ድሬዳዋከተሞች፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሚለው የተለያዩ ስፍራዎች፣ የአፋር ክልል በሚለው ድንበር አካባቢ፣ የደቡብ ክልል በሚለውም እንዲሁ ቤንች ማጅ ዞን፣ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ፣ በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች በአማራ ላይ እንደ አዲስ ዘምቶ ግድያዎችን፣ ማፈናቀሎችን፣ ዝርፊያዎችን ወዘተረፈ. በሰፊው እየተፈጸመ ይገኛል!!!
አማራ “ክልልህ ነው!” በተባለበት የተለያዩ አካባቢዎችም ፀረ አማራው ብአዴን “ፋኖ ናቹህ!” እያለ ከማሳደድ ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካበቢዎች ከግድያ ተርፈው ንብረታቸውን ተዘርፈው ተፈናቅለው የመጡና በረሀብም እየተቆሉ ያሉ ወገኖቻችንን አንዲትም ነገር ሳያቀርብ ያለ አንዳች ሐፍረት የምግብና ሌሎች አስቸኳይ እርዳታዎችን ሳያጓድልና ሳያስታጉል እያደረገላቸው እንደሆነ በብዙኃን መገናኛዎቹ በመለፈፍ የሥነ ልቡና ጥቃት በመፈጸምና ደም በማስለቀስ የድርሻውን ግፍ እየፈጸመ ይገኛል!!!
ይሄ ሁሉ መጠነ ሰፊ የተቀናጀ አረመኔያዊ የአገዛዙ ጥቃት ሲፈጸም ግን እንኳንና ሌላው ዜጋ ይቅርና አማራው እራሱ እንኳ ዓይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ ለማሳለፍ ጥረት አደረገ እንጅ አንዳችም ያደረግነው ነገር የለም!!!
የአማራ ሕዝብ ከትናንትናው በባሰ መልኩ አሁንም ማንም ተጠያቂ በማይሆንበት ሁኔታ ግፍና ሰቆቃ ሲፈጸምበትና ደሙ የትም ደመከልብ ሆኖ ሲቀር እያየ ሕግ ያለና ፍትሕ እንደሚያገኝ አድርጎ በማሰብ እያጠቃውና እያስጠቃው ካለው ፀረ አማራ አገዛዝ አንዳች ነገር መጠበቁ ወይም ተስፋ ማድረጉ ነው እጅግ አስገራሚውና ግራ የሚያጋባው ነገር!!!
እንደ አብን ያሉ በስሙ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶችም የአማራን ትግል እንዲጠልፉ የተደራጁ የአገዛዙ ቅጥረኞች እንጅ ለአማራ ሕዝብ ለመሞትና መሥዋዕትነት ለመክፈል የተመሠረቱ ድርጅቶች ባለመሆናቸው ሌላው ቀርቶ የአማራ ሕዝብ በሰላማዊ ትግል መብት የሆነውን እንደ አድማ፣ ተአቅቦና የተቃውሞ ሰልፍ ያሉ የሰላማዊ ትግል እርምጃዎችን እንዲወስድ በማድረግ መብቱ ደኅንነቱና ጥቅሙ እንዲከበርለት ጥቃቱን እየፈጸመበትና እያስፈጸመበት ያለውን አገዛዝ እንዲያስገድድ አድማ ተአቅቦና ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፍ የማደራጀትና የመምራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ አልቻሉም!!!
ቅጥረኞችና የቆሙትም እያስመሰሉ የፀረ አማራውን የጥፋት ኃይል የብአዴንን ጥቅም ለማስጠበቅ ነውና የይስሙላ መግለጫ እያወጡ ያላግጣሉ እንጅ ወደፊትም ይሄንን የሰላማዊ ትግል እርምጃ ፈጽሞ አያደርጉም!!!
አሁንማ ጭራሽ አድማ፣ ተአቅቦና የተቃውሞ ሰልፍ ላለማደራጀት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጥሩ ምክንያት አላቸው፡፡ የአማራ መከራ ግን የጀመረው ዛሬ አይደለም፡፡ የአማራ መከራ ለአንድ ቀን እንኳ ባላቆመበት ሁኔታ “እስከሞት ድረስ ታምነን ለአማራ ሕዝብ መብት፣ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ነጻነትና ጥቅም ለመታገል ተደራጅተናል!” እንደማለታቸው የሰላማዊ ትግል እርምጃዎችን ማለትም አድማን፣ ተአቅቦንና ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፍን በማድረግ በአገዛዙ ላይ ጫና ማሳደር ሊታሰባቸውና ሊሞክሩትም ያልቻሉት ሌላ በምንም ምክንያት ሳይሆን አስመሳይ የአገዛዙ ቅጥረኛ የካድሬ ጥርቅም በመሆናቸው ነው!!!
ለመሆኑ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ንጹሐን ዜጎችን በአሸባሪ ታጣቂዎች በግፍ መግደልን፣ መዝረፍንና ማፈናቀልንስ ማንና የትኛውስ ሕግ ነው የፈቀደው??? እራሱ አገዛዙ ያላከበረውንና አክብሮት የማያውቀውን ሕግስ የአማራ ሕዝብ የማክበር ግዴታ አለበት ወይ???
እንግዲህ ወገን ሆይ! ያለው እውነታ ይሄው በመሆኑና ተስፋ የምታደርገው ምንም ነገር ስለሌለ ዝምታውና መታገሱም መከራህንና ፍዳህን አበዛው እንጅ ምንም የፈየደልህ ነገር ስለሌለ በሚፈጸምብህ ግፍና ሰቆቃ በየተራ እየተለቀምክ ከማለቅህ በፊት ሕፃን ሽማግሌ ሴት ወንድ ሳትል ቆርጠህና ጨክነህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለነጻነትህ ተነሥ!!! ካልሆነ በዚህ የአምስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ለቅሞ እንደሚጨርስህ ዕወቅ!!! በዚህ ሁሉ ለዘመናት በሚፈጸምብህ አረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ እየሞትክ አልቀሀል እኮ ያለህ መስሎሃል ወገን???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው