April 24, 2020 – Konjit Sitotaw

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስአለም ተክሌ ከ International Crisis Group (ICG) ጋር ባደረጉት ውይይት ምርጫው ከተራዘመ የህገመንግስቱ አንቀፅ 60 ፓርላማው እንዲፈርስና የአደራ መንግስት እንዲቋቋም የሚደነግግ መሆኑን ማስረዳታቸውን ከውጪ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ICG ከሳምንት በፊት ባወጣው ፅሁፍ በኮቪድ-19 ምክንያት ምርጫው የሚራዘም ከሆነ በቀጣይ ስለሚኖረው አስተዳደር ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ምክክር እንዲደረግ መጠየቁ ይታወሳል። ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ታህሳስ ወይም የካቲት ላይ ለማድረግ እቅድ ቢኖረውም የመጨረሻው ውሳኔ እስካሁን አልታወቀም።
—
የህገመንግስቱ አንቀፅ 60 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜው ከማለቁ በፊት ምክር ቤቱን የመበተንና ስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ይችላል ይላል። ነገር ግን የምክር ቤቱ የአምስት አመት የስልጣን ዘመን ካለፈ በኋላ ባለው ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን አንቀፅ ጠቅሶ ለተጨማሪ ወራት ላስተዳድር እንዲል ህገመንግስቱ ስልጣን አይሰጥም። ከመስከረም በኋላ የቅቡልነት (legitimacy) ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። መፍትሄው ምንድነው?
Source – THE FINFINNE INTERCEPT
