April 25, 2020Konjit Sitotaw

የአመራሩን መግለጫ ከፖሊስ ለማረጋገጥ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

_ የታሰረው በኮማንድ ፖስቱ መሆኑ ታውቋል _ ጠዋት ከቤቱ ተወስዶ በኮልፌ ፖሊስ መምሪያ ነው የታሰረው _ የእስሩ ምክንያት ባለፈው በኮልፌ አካባቢ ቤት የፈረሰባቸውን ሰዎች አነጋግረሃል የሚል ነው። _ በእስር እንደሚያቆዩት ተገልፆ ፍራሽና ልብስ እንዲገባለት ሆኗል _ እስክንድር ቤት የፈረሰባቸውን ማነጋገሩን አረጋግጧል። ለህዝብ መብት ነው የምታገለው፣ በዚህ ወቅት ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች እንግልት ተመልክቻለሁ፣ ይሄ እውነት ነው፣ ትክክልም ነው ብሏል!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ ፖሊስ አሰሮታል።

(Sintayehu Chekol )

አሁን በስልክ በደረሰኝ መረጃ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በስልክ ያናገርኩት ሲሆን ዛሬ ሚያዚያ 17/2012 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ከቤቱ ወደ እንደወጣ በአስቸኳይ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትህዛዝ ወጥቶ በኮልፌ ወረዳ 25 ፖሊስ መምሪያ በጊዚያዊነት እንደታሰረ ነግሮኛል። የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ የታሰረበት ምክንያት ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 05 የድሆችን ቤት ፈረሳን አስመልክቶ ለምን ተገኘህ ለምን ድምጻቸውን ለህዝብ ታደርሳለህ እንደተባለ ገልጾልኛል። እስንክንድ ነጋ በአሁኑ ሰዓት በእስር እንደሚቆይ ተነግሮት የእጅ ስልኩን እንደቀሙት እና ወደ ማሰሪያ ክፍል እየገባ መሆኑን ገልጿል።