
የፒኮክ ምስልነት አዲስ ወግ
ግን አንበሳው የት ሄደ? ለምን?
===================
የዛሬው ማንነትን የመቀየሩ ፍዳ የተያያዘ ከእሩቅ ምስራቋ የብዙ ቋንቋወች እና ባህሎች ባለቤት ከሆነችው በርማ (ማይማር) ከተባለቸው ሀገር ጋር ነው። ፒኮክ የተባለችው ወፍ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯን በግሌ አላውቅም። ባጭሩ ብትኖርም ብዙ የጎላ ቦታ በባህላችን አልተሰጣትም ማለት ነው። እናም የእኛ ምልክት (ተምሳሌነቷ) ቅጅ ካልሆነ አይዋሀደንም ማለትም ይሆናል። መነጋገር ጥሩ ነው ግን ቆዳን በየግዜው እየገለበጡ ማንነትን ማጥፋት መሞከሩ ፋይዳ ቢስ ነው። የሚገርመው ማንነታችንን ጡት ቆራጭ ያደረጉን ዛሬ ተራቸው ሲደርስ ሌላ ማንነት ሊሰጡን ሲዳክሩ ማየት ችግራቸው ሊገባ አይችልም። በበኩሌ ማንነት የሚቀየር አይደለም።
ለማጠልሸት ግን (ሰድቦ ለሰዳቢ) ይባላል አይደል ማድረግ ይቻላል። ያ ሲሆን ደግሞ ብሄራዊ የእድገት ጎዳናን ከመከተል እና የእድገት ጎዳናን ለመቀየስ ለብሄራዊ ውይይት ከማብቃት ይልቅ የብሽሽቁን ጎዳና መምረጥ ነው ባይ ነኝ። “ነብር ዝንጉሩርነቱን፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን” እንድንል መለወጥ ከባድ ይመስለኛል።
አባቶች ብዙ አለምን ያስደመመ ሰርተው አልፈዋል። ከቋንቋ ፊደላት እስከ የእኛ የሆነ የቁጥር ስሌት እስከመስጠት አይነት የት የሌለ ጥበብ ማለት ነው። በነሱ ማፈር የጀመሩት ማፈሪያወች የተቆረጠ ጡት ሀውልት ሰርተው ከሰጡን በኋላ ሌላ ማንነት ፍለጋ እሩቅ ምስራቅ ድረስ ሲዳክሩ ሰነባብተዋል። ግጥጥሞሽ ባይሆንም የበርማ ሰንደቅ አላማ ምናልባት ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት በኋላ የተሰጣት ይመስለኛል ቢጫ ከላይ አረንጓዴ መሀል ቀዩ ከታች መሀል ላይ ነጭ ኮከብ የተለጠፈበት ነው። በርማወች የሩቅ ምስራቅ ሰወች ባይሆኑ ኖሮ እንደትልቅነታችን ጎትተን ከኛው በጨመርናቸው እና ከፒኮክ ምልክታቸው እስከ በእንግሊዝ የተሰጠ ባንዲራቸው እንጠቀልል ነበር። ግን እነሱና እኛን ምንም የሚያገናኝ ምልክት እንኳን በሌለበት የነሱን ብሄራዊ ምስል (ብርቅርቅ ወፋቸውን) መውሰዱ ምን ፋይዳ ይኖረዋል ትላላችሁ።
በበኩሌ የልቅ የሚያስማማንን ማድረግ፣ ያን የኦሮሞ ብልጽግና ኦፒዴኦ በነበረበት ዘመን የገተረውን የጡት ምስል ማፍረስ እና ደግ ደጉን መከተሉ ይሻላል። እኛ የሦስት ሽህ አመታት ግዙፍ ታሪክ ያለን። በነጻነት ኖረን ባእድን ያንበረከክን እንጅ ለማንም ያልሰገድን ሕዝብ ነን። ይህ የሚያስጠላው ካለ ያባቶቹ ስራ ነው ህቅ ቢለውም ይቀበል።፡እውነት ነው ኢትዮጵያ የአንበሳ ተምሳሌት ናት። ምስላችን ከአባቶቻችን ስራ እና ተግባር ተዛማጅ ነበር የምታፍሩ እናውቃለን ሁሉንም ብትቀይሩት ምኞታችሁ ነው። ግን ብዙሀኑ ማንነትን በደም እና አጥንት ዋጋ ከፍሎ የተወረሰ ስለሆነ ቻሉት። የመግዛት እድልን በደንቡ እንደነ ኃብተጊወርጊስ፣ ጎበና እና ሚኒሊክ ተጠቀሙበት።