April 26, 2020Konjit Sitotaw

የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ ነበራቸው። አቶ ንጉሱ በዚሁ ቆይታቸው ከለውጡ በፊትና ከለውጡ በኋላ የነበሩና ያሉ አገራዊ ጉዳዮችን በስፋት አብራርተዋል።

በውስጥ የነበረው መናጥ እና በውጭ ያለው ግፊት ተመጋግቦ ለውጥ አምጥቷል፤ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ዜጎች አንድም በጫካ፣ ሁለትም አገራቸውን ጥለው ሄደው ሥርዓቱንና መንግሥትን እንዲፋለሙና እንዲፈታተኑ ያደረገ ሁኔታ ነበረ፤ ቀደም ሲል የነበረው የፌዴራል ሥርዓቱ እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓት አልነበረም፤ አድሏዊም ነው፤ በእውነተኛ የፌዴራል ሥርዓት ሶማሌ ራሱን ያስተዳድር፤ ሞግዚትና መገረፍ ይቅርለት ማለት ነው። አፋር ራሱን ያስተዳድር መቀማት መነጠቅ ይቅርለት ማለት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድሩ ማለት ነው። ይሄንንስ እኛ ስንል አልነበረም ወይ ካሉ፤ መልሱ እርሱ የስም ሆኖ ነው የተገኘው የሚል ነው፤ በፌዴራል ሥርዓቱ ውስጥ የፌዴራል ሥርዓቱ አድሏዊ ነው ብሎ መነሳትና መናገር በራሱ ነውር ነበረ፤ ለውጡ ማንኛውንም ነገር ሰው ይናገር በሀሳብ ነጻነትና ልዕልና እንመን፤ ከንግግር በኋላ እንግባባ የሚል ነው። ስለዚህ አሁን የምናየውም ሰው የፈለገውን ይናገራል፤ የፈለገውን ነገር ያደርጋል፤ ይሄ ደግሞ የለውጡ ቱሩፋት ነው፤ አሁን የጎደሉንን የምናሟላበት፣ ያሳካናቸውን ደግሞ አጠናክረን የምንቀጥልበት፤ ካለፈው ስህተታችን የምንማርበት፣ ጥሩውን የምናስቀጥልበት፤ ግን ደግሞ ሥርዓት አፍርሰን፣ አገር አፍርሰን ከዜሮ ጀምረን የማንሄድበት ለውጥ እውን ሆኗል፤ ለውጡን የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው ብለው የሚሉ ጠርዘኞች የአሐዳዊ ሥርዓት ባለቤት ናቸው የሚሏቸውን ወገኖች ለአንዴና ለመጨረሻ ጠላት አድርገው ስለሳሉ፤ ቀብረናቸዋልም ስላሉና ስላስባሉ ሁሉንም ሃይል ሊያሰልፍልን ይችላል ብለውም ስላሰቡ እስከወዲያኛው እንግፋ በሚል ነው፤ የአማራ ህዝብ ጥያቄ የነበሩ ጥያቄዎችን ሌላ መልክ በመስጠት፣ ጥያቄዎቹን በማድበስበስ፣ ጥያቄዎቹ እንዲዳፈኑ በማድረግ፤ ይልቁንም የህዝቡ ጥያቄ ሳይሆን የትምክህት ሃይሎች ጥያቄዎች ናቸው በማለት እና ሌላ መልክ በመስጠት ጥያቄዎቹ እንዲዳፈኑ የማድረግ ሚናና ተልዕኮ የነበራቸው በግልጽ የሚታወቁ ሚዲያዎች ነበሩ፤ ህዝብን ደግሞ ጠላትና ወዳጅ አድርጎ የሳለና ይሄንን አስተሳሰብ የያዙ አካላት እልፍ ሲሉና ማስረጃችሁ ምንድን ነው ሲባሉ ብሔር መሰረት አድርገው ሰው ይቆጥራሉ፤ ጥርሳቸውን የነቀሉት ብሔር መሰረት አድርገው ሰው ቆጥረው የቤትና የውጭ ልጅ አድርገው በመለያየት ስለሆነ አይታይባቸውም፤ በክልል፣ በጎጥ፣ በቀጠና፣ በብሔርና በሃይማኖት ግጭቶች እና መከፋፈሎች ነበሩ። እነዚህ ያደሩ ሂሳቦች መዘጋት አለባቸው። እነዚህን ያደሩ ሂሳቦች ደግሞ በመሣሪያ መዝጋት አይቻልም። ጭጭ ማሰኘት ግን ይቻላል። ፀጥታ ማስከበር ይቻላል እንጂ ሰላም ማረጋገጥ አይቻልም። ፀጥታን ማስከበር እና ሰላምን ማረጋገጥ ይለያያሉ፤ ሰዎችን ያፈናቀሉ፣ ሀብት ንብረት ያወደሙ፣ አካል ያጎደሉና የሰው ህይወት ያጠፉ፣ በተለይ ማንነትን መሰረት አድርገው ግጭት በመፍጠር የሰው ህይወት ያጠፉ የተለያዩ አካላት በሺዎች የሚቆጠሩ ተጠይቀዋል። አሁንም እስር ቤት ይገኛሉ። ከአቶ ንጉሡ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሊንኩን ተጭነው ያገኙታልhttps://www.press.et/Ama/?p=31151
የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ – እዚህ ላይ ይጫኑ