ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
በቀለ ሻረው ማን ነው??

ከትግል ጓዶቹ እንደተነገረው፤……
በቀለ ሻረው በጎጀም ክፋለ ሐገር በ ባሀርዳር አወራጃ በሜጫ ወረዳ ይዶንጋ ማርያም ወይንም ልዩ ሰሟ ባችማ ተራራ ተብላ በምትጠራ መንደር ተወለደ። በቀለ ለቤተሠቦቹ የመጀመሪ ልጅ ነበር። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ የመጀመርያ ደርጃ ትምህርቱን በመርአዊ ከተማ፤ ስድስትና ሰባተን ወደ ዳንግላ ከተማ በመሄድ ከተማረ በኋላ፤ ትምህርቱን ለመቀጠል ባህርዳር በመሄድ የ 9ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ ነው የኢሕአፓን ወጣት ክንፍ ኢሕአወሊን የተቀላቀለው።
በቀለ ሻረው በድርጅታዊ ስራው ንቁ ተሳትፎ ስለነበረው ከጓዶቹ ጋር ወደ ዘጊ በሂደበትበት ጊዜ በመኢሶን ካድሬወች ተጠቁመወና ለእስር ተዳርገው ወደ ባህርዳር ከተወሰዱ በኋላ፤ በ ደርግ አራጅ መቶ አለቃ አለሙ እሸቱ ከመገደል አምልጦ፤ በ 1970 ሁለት አመት ተፈርዶበት ከቆየ በኋላ፤ ከአምስት ጓዶቹ ጋር አብሮ ከእስር አመልጦና ከሳምንት በኋላ በከፍተኛ የወታደሮችና የካድሬዎች ፍለጋና አሰሳ በይልማና ዴንሳ ወረዳ እነደገና ተይዞ ለ 7 ዓመት ለእስራት ተዳርጓል። እስራት ሲፈታ አካባቢው መቀመጥ የበለጠ አሰቸጋሬና ለበለጠ አደጋ የተጋለጠ በመሆኑ በኋላም ከጓዶቹ ጋር በመሆን ኢሕአሠን ተቀላቅሏል።
በጣም ተግባቢ፤ ተጫዋችና ደግ፤ ቀልድኛ፤ ላመነበት በአላማ ው የፀና፤ ለድርጅቱ ታማኝ ወታደርና ቆራጥ የነበረወ በቀለ ሻረው ከሚለይባቸውና ከሜታወቅባቸው ሁለት ነገሮች በክራር መጫወት ባለው ተሰጥኦና በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው ከነበሩ ከአባቱ አቶ ሻረወ አደመ በተማረው ኢላማ ተኩስ ነበር።
በቀለ ሻረው እነ ጋይምና አበራሽ በርታ በ 1983 ወያኔ ከመግባቱ በፊት ከ ኢሕአሠ ተልከው የከተማውን የህቡዕ ትግል ለማካሄድ ወደ ከተማ ከመግባታቸው በፊት፤ በ 1982 የከተማ ስራ ለመስራትና ለማጠናከር ከነ ወንዱ ሲራክ ጋር ወደ ከተማ ከገቡት ጓዶች አንዱ ነበር።
በቀለ ሻረው በሰራዊቱ ውስጥ በተለያዩ የሰራዊቱ የሃላፊነት እርከኖች የበኩሉን አስተዋፆ በቆራጥነት ሲያበረክት ቆይቶ እነደብተርራው በኋላም እነ አበራሽ በርታ በጠላት እጅ በወደቁበት ጊዜ፤ እነ ጋይም በተሰዉበት ጊዜ፤ ህክምናውን ሳይጨርስ ከሱዳን ተመልሶ የድርጅቱን የህቡዕ መስመር ታግሎ ያስቀጠለ ጀግና ወጣት ነበር።
በቀለ ሻረው ፤ በ 1985 በ አዲስ አበባ ጋይምን በመጠቆም በወያኔ አስከብቦ ያስመታውንና ሌሎች ጓዶችም ላይ ከወያኔ ጋር በማበር የጠቆመ አብራሃም ጌጡ የተባለ ከሃዲ በሀርዳር ውስጥ እንዲወገድ ያደረገና የጓዶቹን ደም የተበቀለ ጀግና ወጣት ነበር።
በኋላም በቀለ ሻረው ሱዳን አገር ለህክምና ሄዶና ህክምናውን ሳይጨርስ ተመልሶ የድርጅቱን መስመር ለማስቀጠል ሲታገል በጠና ታሞ ተደብቆ እንደተኛ ወያኔዎች አባቱን፤ ወንድሙንና እናቱን በማሰር፤ በኋላም ወንድሙ ላይ አሰቃቂ ስዬል በመፈፀም፤ አባቱንም አሰቃቂ ስዬል ዕንዲፈፀምባቸው አድርገው በመግደል ያለበትን ቦታ አስከብበው ከተያዜ በኋላ ለእስር ተዳርጎ እስር ቤት ውስጥ በጀግነት አልፏል።
ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!