April 28, 2020

(ኢፕድ) – ‹‹የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካል የሆነው የኮርቻ ግድብ ግንባታ ከማጠናቀቂያ ሥራ በስተቀር ሙሉ ለሙሉ አልቋል” ሲሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ፡፡

Image may contain: 1 person, sitting and eyeglasses

ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር ክፍሌ በተለይ ለአዲስ ዘመን ትናንት እንደገለጹት፤ የኮርቻ ቅርፅ ያለው ግድብ (ሳድል ዳሙ) የዋና ግድብ አካል ሲሆን፣ አስፈላጊነቱ የሚፈለገውን 74 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር ውሃ ለመያዝ ነው፡፡ እሱ ካልተገነባ ውሃ መያዝ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የዚህ የሳድል ዳም ግንባታም በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን አንዳንድ የማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ ቀርተውታል፡፡

‹‹የሳድል ዳሙ ሥራ ካልተጠናቀቀ ተፈላጊውን ውሃ መያዝና የሚፈለገውን ኃይል ማመንጨት አይቻልም ማለት ነው›› ያሉት ኢንጂነር ክፍሌ፣

‹‹ሳድል ዳሙ ጥራቱንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባ በመሆኑ ትልቁ ሥራው የሆነውን ውሃ እንዳይሰርግ የማድረግ ተግባሩን ያከናውናል›› ብለዋል፡፡

እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ፤ ሳድል ዳም እንደሚታወቀው በድንጋይ ሙሊት ከተካሄደ በኋላ ውሃ የሚተኛበት ነው፡፡ በኮንክሪት የሚሞላው ወደ አምስት ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ 50 ሜትር ከፍታ ያለው ነው፡፡ ወደ 14 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የድንጋይ ሙሊት የወሰደ ነው:: የዚህ ዓይነቱ ግድብ ነባር ቴክኖሎጂ በመሆኑም በዓለም ላይ በሺዎች ተሰርተው ይገኛሉ ፡፡

የተረጋገጠ ቴክኖሎጂም ስለሆነ በጥራት ደረጃ ምንም የሚነሳበት ጥያቄ የለም፡፡ ‹‹ትልቁ የኮንክሪት ግድባችን 645 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ ውሃ የሚተኛበት እስከ 640 ሜትር ድረስ ያለው ነው፡፡ ይህም 640 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ማለት ነው፡፡ የግድቡ ከፍታ እንደሚታወቀው 145 ሜትር ነው፡፡ ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=31231