ይሄ ለውጥ የተሰኘው የወያኔ/ኢሕአዴግ ድራማ ተጠናቆ ወያኔ ተዋናይ ምስለኔዎቿን እነ ኩሊ ዐቢይ አሕመድን ገለል አድርጋ መልሳ ጉብ ስትል በወያኔ ላይ ጥይት አጩኸው ወያኔን አሳደው መቀሌ እንዲወሸቅ ያደረጉ ይመስል ወያኔ ተሸንፎ መቀሌ ገብቷል፣ ከዚህ በኋላ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ወያኔ ተመልሶ ሥልጣን ላይ አይወጣም….!” ምንንትስ እያሉ ይቀደዱ የነበሩ ፖለቲከኛ ነኝ፣ ተንታኝ ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ…..!” የሚሉ ዘገምተኞችን በሉ አያቹህ አይደለ? ሴራን ፖለቲካን የመተንተን የመረዳት አቅማቹህ እዚህ ድረስ ነው፡፡ ሲነገራቹህ እንኳ የማይገባቹህ ድንጋዮች ናቹህና ከዚህ በኋላ አቅማቹህን አውቃቹህ በራሳቹህ ፈቃድ እራሳቹህን ከፖለቲካው፣ ከትንታኔው፣ ከጋዜጠኝነቱ…. አግልሉ! ፣ አሁኑኑ ሹልክ ሹልክ እያላቹህ ጥፉ!!!” ማለትና ማሾፍ መቀለድ ነው የናፈቀኝ!!!

* ዘገምተኞቹ እንደሚሉት ለአማራ ሕዝብ ተቆርቁሮ፣ ነፍሱን አስይዞና ወያኔን ጉርቦ ለጉርቦ ተናንቆ ወያኔን ከቤተመንግሥት ያባረረው ብአዴን ከሆነ እንዴትና በምንስ ምክንያት ነው ታዲያ ዘገምተኞቹ ብአዴንን እዚህ ግባ የሚባል አቅም በሌለው ኦሕዴድ መጫወቻና መቀለጃ አሻንጉሊት ሊሆን ቻለ!” ብለው የሚያስቡት???

* ብአዴን ወያኔን ያባረረበት ጠንካራ አቅም የት ሔዶ ነው ከዚያ በኋላ የኦሕዴድ መጫወቻ ሊሆን የቻለው???

* ነው ወይስ ብአዴን የታገለው ወያኔን አባሮ ኦሕዴድን ለመሾም ወይም ለመተካት ነበር እንጅ የተገፋውን የአማራን ሕዝብ የሚገባውን ያህል ተጠቃሚ ለማድረግና ካለበት የህልውና አደጋ ለመታደግ አልነበረም ማለት ነው???

* ለአማራ ከሆነስ ብአዴንን እንደምታዩት ሌላ የፍዳና የመከራ ዘመን ምእራፍ በአማራ ሕዝብ ላይ ከፈተ እንጅ የትኛውን የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ሲመልስና ሲያስመልስ፣ አማራን ከየትኛው የግፍ ጥቃት ሲታደግ አያቹህት???

* ኦሕዴድን ገዥ ለማድረግ ከሆነ ብአዴን የታገለው ደግሞ ለባርነት ባርነት፣ ለሎሌነት ሎሌነትማ ፈጣሪውን ጌታውን ወያኔን አስወግዶ ኦሕዴድን ማንገሥ ለምን አስፈለገው ታዲያ???

* ብአዴን ምንም ዓይነት ጥይት ማጮህ ሳያስፈልገው ያንን ያህል ወያኔን ከማዕከላዊ መንግሥት ሥልጣን የማባረር የማስወገድ አቅም ካለውስ እንዴት ሥልጣኑን እኔ ልያዝ!” ሳይል ሊቀርና ኦሕዴድ ጠቅልሎ እንዲይዝ ሊያደርግ ቻለ???

* ብአዴን ከስሙ እንደምንረዳው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ነኝ!” ቢልም በተግባር ግን እንደ ወያኔና ኦሕዴድ የሚዋደቅለት የኔ የሚለው ሕዝብ ስለሌለው ነው ወይ ሥልጣን ለመያዝ ሳይፈልግ ሊቀር የቻለው???

* ኦሕዴድስ በብአዴን ተጋድሎ ሥልጣን የያዘ ከሆነና ወያኔን ተክቶ መንግሥት መሆን የሚፈልግ ቢሆን የተቻለውን ያህል ጥረት እያደረገ በኢትዮጵያ ሕዝብ ለመወደድ ለመፈቀር ጥረት ያደርግ ነበረ እንጅ እንደምታዩት በሕዝብ ላይ ይሄንን ሁሉ ግፍና አድልኦ እየፈጸመ በኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጠላት ጥረት ያደርግ ነበረ ወይ???

* ለመሆኑ ለምን ይመስላቹሃል ኦሕዴድ ወይም ብልጽግና ብሎ ለራሱ ስም አውጥቶ ብልጽግና የኦሮሞ ፓርቲ መሆኑን የተናገረው ኦሕዴድ ወይም ብልግና ቀደም ሲል ሕዝብን ለማታለልና ለማጃጃል የወሸከተውን አማላይ ቃልና የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ገደል ከቶ በሕዝብ ላይ ግፍ እየፈጸመ ሕዝብን የሚያስመርረው ለምን ይመስላቹሃል???

እኔ ልመልስላቹህ መልሱን??? መልሱ፦ ወያኔ የድራማው ዘመን ሲያበቃ መምጣቱና ወደቦታው መመለሱ ስለማይቀር በሚመጣበት ጊዜ ሕዝቡ ሳያጉረመርም በጸጋ እንዲቀበለው ለማዘጋጀት ነው አሁን ወያኔን ለማስናፈቅ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህስ ወያኔ ይሻለናል!” እንዲል ለማድረግ ኦሕዴድ ሆን ብሎ ይሄንን ሁሉ ግፍ በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ሕዝብን እያስመረረ ያለው፡፡ ሌላ ምንም ምክንያት የለም!!!

አለ!” የምትሉት ሌላ ምክንያት አለ እንዴ እነ ዘገምተኞ???

ይሄ ብአዴን ከወያኔ ጋር፣ ኦሕዴድ ደግሞ ከወያኔ ጋር የተጣሉና የሚቆራቆሱ የሚያስመስሉት ነገር ድራማውን የእውነት ለማስመሰልና ሕዝብን ለማጃጃል የሚተወን ትወና ነው! ይሄ ሁሉ ትወና ውሸት መሆኑን ነገ ድራማው ሲጠናቀቅ ታዩታላቹህ!!!

እንጅ ወያኔ በስንት መራራ ትግል ስልሳ ሽህ ወገኖቸን ሠውቸ የያዝኩት ሥልጣን ነው ሥልጣን ከፈለጋቹህ ታግላቹህ ኑ!” እያለ በአፅመ ርስትነት ሙጭጭ አድርጎ የያዘውን ሥልጣን እንዲህ በቀላሉ አንዲት ጥይት ያጮኸበት ሳይኖር ጥሎ፣ ለቆ ወይም አስረክቦ የሚፈረጥጥ ይመስላቹሃል እነ ጅሎ???

አየ እነ ዘገምተኞ! ብቻ በዚያ ጊዜ ያገናኘንና የምትሆኑትን ያሳየኝ፣ የምትሉትንም ያሰማኝ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው