የወያኔው ኩሊ ዐቢይ አሕመድ ጥንካሬን፣ አሸናፊነትንና በአንበሳ የተመሰለውን ክርስቶስን እንዲወክል ተደርጎ ለሽዎች ዘመናት የቆየውን የሀገሪቱን ቅርስ፣ አሻራ፣ መለያና ብሔራዊ ምልክት አንበሳውን አስወግዶ የግብረ ሰዶማውያን ምልክት በሆነው ፒኮክ ወይም ጣዎስ ለመተካት ያደረገውን ነውረኛና አጸያፊ ተግባር ጉዳይ በተመለከተ ባልደራስ ስላነሣሣው የተቃውሞ ፊርማ አሰባሰብ ጉዳይ አቶ እስክንድር በዐሥራት ቴቪ ላይ ሲናገር፦

“……የግድ አንበሳ ይኑር እያልን አይደለም ለሕዝብ አቅርበው ሕዝብ ከፈቀደላቸው እኛም ለመቀበል ዝግጁ ነን….. እሳቸው በሕዝብ የተመረጡ መሪ አይደሉም፡፡ ስለሆነም የመቀየር መብት የላቸውም፡፡ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ግን የአንበሳው ምልክት አልፈልገውም ማለት ይችላል……!” በማለት አደገኛ፣ ድንቁርና የተጣባውና የቅጥረኛ ንግግር ተናግሯል!!!

ሕዝብ ይሁንታውን እንዲሰጥ አስፈላጊ የሚሆንበት ጉዳይ የመንግሥት ምርጫን፣ በሕገመንግስት ይዘት ጉዳይና ባልነበረ እንዲኖርም በሚፈለግ ጉዳይና መሰል ጉዳዮች ነው እንጅ በነበረና ለሽዎች ዓመታት በቆየ እንደ የሀገር ስም፣ ሰንደቅ ዓላማና ብሔራዊ ምልክት የመሳሰሉ ጉዳዮችና ቅርስ አሻራዎች ላይ የነበረውን ከመጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ ከማሻገር ውጭ በጉልበትና በሕገወጥ መንገድ ካልሆነ በስተቀር ማንም ቢሆን በሕዝብ ድምፅም ሆነ በምን የመቀየርና የማጥፋት መብት የለውም!!!

እንዲህማ ቢሆን በዓለም ሀገራት በየጊዜው የሚመጡ መንግሥታት አዳዲስ የሀገር ስም፣ ሰንደቅ ዓላማና ብሔራዊ ምልክት ወይም መለያ እየቀያየሩ ባስቀመጡ ነበር፡፡ የትኛውም ሀገር የሀገሩን ስም፣ ሰንደቅ ዓላማውንና ብሔራዊ ምልክቱን ሕዝብን አስመርጦ ወይም አስወስኖ ያስቀመጠ በዓለማችን ላይ አንድም ሀገር የለም፡፡ በታሪክ ሒደት በአንድ አጋጣሚ በገዥዎች ወይም በአንድ የሆነ አካል እነኝህ ነገሮች ይቀመጡና ወደደም ጠላ ወደ ሕዝብ ይተላለፋሉ ሕዝብም ተቀብሎ ይይዘዋል ወይም የራሱ ያደርገዋል እንጅ!!!

ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያንም ከዓለም የተለየን አይደለንምና እንደ አዲስ ሀገር ወያኔም ሆነ ንኩ ዐቢይ አሕመድ የነበረውን በማጥፋት አዲስ ሰንደቅ ዓላማ፣ አዲስ ብሔራዊ ምልክት፣ አዲስ የሀገር ስም ወዘተረፈ. ሊመርጥ ወይም ሊያስመርጥ አይችልም መብትም የለውም!!!

ማንም ሰው እራሱን የማጥፋት መብት እንደሌለው ሁሉ እራስን ማጥፋት ወንጀል እንደሆነም ሁሉ አንዲት ሀገርም መለያ ምልክቷን፣ አሻራ ቅርሷን የማጥፋት መብት የላትም!!! ካጠፋችም ወንጀል ነው!!! ይሄንን ማድረግ በታሪክ ጥናት ሥራ ላይ፣ በአርኪዮሎጅ ቁፋሮና በሚገኙ የመረጃዎች ንባብና ብያኔ ላይ በርካታ የሚያበላሻቸውና የሚያጠፋቸው ነገሮች አሉና ነው!!! የምለው ገብቷቹሃል???

ስለሆነም የእነ እስክንድር አቀራረብ የተሳሳተና አደገኛም ነው፡፡ ምናልባትም እስክንድር በአገዛዙ የተሰጠው ስውር ተልእኮ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አገዛዙ የሀገሪቱን ሰንደቅም ለመቀየር በሕዝብ አስወስናለሁ!” እያለ ያለበት ሁኔታ ስለሆነ ያለው በዚህ በአንበሳው ምልክት ይቆይ ወይስ ይወገድ?” በሚል የሕዝብ ድምፅ በማሰጠት አላምዶ የሀገሪቱን ሰንደቅና መሰል ጉዳዮች ላይም በሕዝብ ውሳኔ ወይም ምርጫ ይወሰን!” ለማለት እንዲመቸው ለዚያ እያመቻቸን እንደሆነ ነው እኔን የሚገባኝ!!!

መረዳት እንደምትችሉት በኢትዮጵያ ሰንደቅም ሆነ በዚህ በሀገሪቱ ብሔራዊ ምልክት ላይ የሕዝብ ድምፅ ይስጥበት!” ቢባል አገዛዙ እነኝህን የሀገሪቱን እሴቶችና ቅርሶች ለሦስት ዐሥርት ዓመታት በተሳሳተ መንገድ የአማራ እንደሆኑ አድርጎ ስለሰበከና ሕዝቡን ስለመረዘው ከአማራ ውጭ ይሁንታ ሊሰጠው የሚችል ዜጋ ፈጽሞ የለም ባይባልም እጅግ በጣም ጥቂት እንደሆነ መገመት የምትችሉ ይመስለኛል!!!

በመሆኑም ጉዳዩ ወደ ሕዝበ ውሳኔ ቢመራ ሲጀመር ከላይ እንደገለጽኩላቹህ አሠራሩ ስሕተት ነው ስሕተትነቱ እንዳለ ሆኖ ሕዝበ ውሳኔ ቢደረግባቸው እነኝህ ጥንታዊ የሀገሪቱ እሴቶች መቀየራቸው፣ መወገዳቸው፣ መጥፋታቸው ነው ማለት ነው!!! እስክንድር እንዲያውም እያለ ያለው በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ካልፈለገው ሊያስወግደው ይችላል!” ነው እያለ ያለው፡፡

በመሆኑም የእነ እስክንድር የፊርማ ማሰባሰብ ባልኩት መልኩ ካልተስተካከለ በስተቀር እንዳትፈርሙ!!!

ሰንደቅ ዓላማችንንና ብሔራዊ ምልክታችን አንበሳውን በተመለከተ ሰፊ ዘገባ ከፈለጋቹህ ከሰባት ዓመታት በፊት የጻፍኩትን ጽሑፍ ሊንኩ ይሄውላቹህ ማንበብ ትችላላቹህ፦

http://www.goolgule.com/our-falg/

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው