አገዛዙ ለሕዝብ ጥቅም ሲሆን “በኢሕአዴግ መቃብር ላይ ነው ይሄ የሚሆነው!” በማለት ሕገመንግሥቱን መለኮታዊ ቃል አስመስሎ ፈጽሞ እንደማይሻሻል በእብሪትና በድንፋታ ይናገራል እንጅ ለራሱ ጥቅም ሲሆንማኮ ከበፊት ጀምሮ ሕገመንግሥቱ ላይ የሰፈረውን ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌን የማሻሻያ መንገድ ሳይከተልና ለሕዝብ በይፋ ሳያስታውቅ ለበርካታ ጊዜ ሕገመንግሥቱን “አሻሽያለሁ!” በማለት እንደፈለገ እንደሚመቸው ሲያደርግ ቆይቷል እኮ!!!
ለምሳሌ በቅርብ ትውስ ካሉኝ ሁለቱን ብጠቅስ፦
1ኛ. የሕዝብና ቤት ቆጠራን ማራዘም የሚቻልበትን አንቀጽ አስገብቷል፣
2ኛ. በbiological engineering ተፌጥሯዊ ባሕርያቸው የተቀየሩ እንስሳትና ዕፅዋት ወደ ሀገር ማስገባት የሚከለክለው አንቀጽ ተቀይሮ እንዲገቡና ለምርምር ሥራ እንዲውሉ በሚል ተሻሽሏል፡፡ እነኝህን የመሳሰሉ በርካታ የሕገመንግሥት ማሻሻያ አነቀጾች ለበርካታ ጊዜያት ተደርገዋል!!!
አሁን የማይደብቀው ነገር ገጥሞት ነው የተቸገረው እንጅ ሕገመንግሥቱ ያለመፍቀዱ ነገር ችግር ሆኖበት ወይም ለሕግ የበላይነት ተጨንቆ አይደለም “ምን ይደረግ?” እያለ ያለው!!!
በመሆኑም እንዲያው ሲያስመስል እንጅ ፓርሊያመንት ተብየውም፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተብየውም፣ የክልል መንግሥታት ተብየዎችም የራሱ አሻንጉሊቶች በመሆናቸው አጭበርብሮ የያዘው የሥልጣን ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ምርጫን ማራዘም የሚችልበትን የሕገመንግሥት ማሻሻያ አድርጎ የሥልጣን ዘመኑን ማራዘሙ አይቀርም!!! የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን የወያኔ/ኢሕአዴግ የአጋንንት ቡድን በዐመፅ ካልተገላገልከው በስተቀር መላቀቂያ ያለው እንዳይመስልህ!!!
እዚህ ላይ ግን ክልሎች የሚሏቸውን በተመለከተ ሕገመንግሥቱ “ሁሉም የክልል ምክርቤቶች በአብላጫ ድምፅ ሲያጸድቁት!” ስለሚልና ወያኔና የፌዴራሉ መንግሥት ተብየው የተጣሉ ስለሚያስመስሉና በዚህም ምክንያት የትግራይ ክልል ተብየውም ካላጸደቀው በስተቀር ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌውን ማሻሻል ስለማይቻል በዚህም ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚገቡ የወያኔ/ኢሕአዴግ ድራማ መጋለጡ አይቀርም!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው