ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ ክፍል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ የእጅ ስልክ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ቊጥጥር እንደሚገኝ ዐስታወቀ። ……………. አቶ እስክንድር ኮሮናን ለመከላከል የወጣውን አካላዊ መራራቅ (ማኅበራዊ መራራቅ) ደንብ ሳይጥሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ስልካቸውን እንደወሰደባቸው አምነስቲ ጽፏል።
AmnestyEasternAfrica ✔ @AmnestyEARO
Addis police seized @eskinder_nega‘s phone without court authorization for violating social distancing rules. He fears for his digital security; they’ve unlocked it & have full access. They must immediately return it & stop using #COVID19 as an excuse to infringe upon his rights.
Twitter Ads info and privacy 156 people are talking about this
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ ክፍል በትዊተር ማኅበራዊ መገናኛ ይፋዊ ገጹ ላይ ዛሬ ያሰፈረው ጽሑፍ፦ አቶ እስክንድር ነጋ «ለዲጂታል ደህንነታቸው» ሥጋት ገብቷቸዋል ይላል። ፖሊስ የእጅ ስልካቸውን ከፍቶ ሙሉ ለሙሉ እንደፈለገ ማድረግ መቻሉን መግለጣቸውንም ጠቅሷል። …………….. ፖሊስ ስልኩን በአፋጣኝ ለባለቤቱ እንዲመልስ አምነስቲ አሳስቧል። ፖሊስ ኮቪድ 19ኝን ሰበብ አድርጎ የሰብአዊ መብታቸውን ከመጣስም ይቆጠብ ሲል ዓለም አቀፍ ድርጅቱ አስጠንቅቋል። …. Source – DW Amharic