አትክልትና ፍራፍሬ

በፈረንጆቹ 1918 የተከሰው ስፓኒሽ ፍሉ የተባለው ወረርሽኝ በወቅቱ ከነበረው የዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛውን ማለትም ከ500 ሚሊዮን የሚሆኑትን ሲያጠቃ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን በመግደል በተመዘገበ ታሪክ ውስጥ በጣም ከፍተኛው መቅሰፍት ነበር።

በዚያ ዘመን ከወረርሽኙ ጋር በሚፈጠር ዕድል የእባብ ዘይት ሻጮች በከፍተኛ ሥራ ላይ ነበሩ፤ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ማስታወቂያዎችን ይጠቀሙ ነበር። ማስታወቂያዎቻቸው በጋዜጣ ላይ በመደበኛነት ይወጡ የነበረ ሲሆን አስፈሪ ርዕሶችም ነበሯቸው።

ወዳለንበት 2020 ስንመለስም ብዙ አልተለወጠም። ምንም እንኳን ኮቪ-19 ከስፓኒሽ ፍሉ ከመቶ ዓመታት ሳይንሳዊ ግኝቶች በኋላ ቢከሰትም አሁንም አጠያያቂ በሆኑ መድኃኒቶችና ባህላዊ መፍትሔዎች እንደተከበበ ነው።

አሁን ግን ዋነኛው ማጠንጠኛ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም “ማጎልበት” የሚል ነው።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚያሰራጩት ያልተረጋገጡ መረጃዎች መካከል እንደማንኛውም ጊዜ ሁሉ የአመጋገብ ምክሮች በብዛት ይሰጣሉ። በፀረ-ተህዋሲያን እና በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን እንድንወስድ እየተበረታታን ነው።

የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳትዎን ማጎልበት

ክኒኖች፣ በብዛት የሚነግራለቸው ምርጥ ምግቦች ወይም የጤና አጠባበቅ ልምዶች በአቋራጭ ለጤነኛ የበሽታ መቋቋም ሥርዓት ያግዛሉ የሚለው አስተሳሰብ ያለተጨበጠ ነገር ነው ይላሉ ባለሙያዎች።

አክለውም በእውነቱ በሽታን የመከላከል አቅምን “ከፍ ማድረግ” የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ትርጉም የለውም።

“በሽታን ለመከላከል ሦስት ነገሮች አሉ” ሲሉ የዬል ኢሙኖሎጂስት [የሰውነት በሽታን የመከላከል ሥርዓትን የሚያጠና ዘርፍ] የሆኑት አኪኮ ኢዋሳኪ ይገልጻሉ።

“በመጀመሪያ ላይ በሽታን ለመከላከል ቆዳችንና የአየር መተላለፊ አካላችን አሉ። እነዚህ ለበሽታው እንቅፋት ይሆናሉ። ሆኖም ቫይረሱ እነዚህን መከላከያዎች ካለፈ በኋላ ተፈጥሮአዊው በሽታ መከላከያን ይነሳል” በዚህም ማንቂያውን ከፍ የሚያደርጉና ማንኛውንም መጤ ነገር መዋጋት የሚጀምሩ ኬሚካሎችንና ሴሎች ይካተታሉ።

“ይህም በቂ ካልሆነ ሌላኛው በሽታን የመቋቋም ሥርዓታችን ወደ ሥራ ይገባል” ይላሉ። ይህም ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት የሚወስድባቸው ሴሎችንና ፕሮቲኖችን ያካትታል።

አብዛኞቹ ኢንፌክሽኖች በሽታ የመከላከል አቅምን ያነቃቃሉ። ሌላኛው መንገድ ደግሞ ክትባት ነው። አካልን በሕይወት ባሉ ወይም በሞቱ ረቂቅ ተህዋስያን ወይም ለእነሱ ክፍሎች በማጋለጥ ሰውነት ትክክለኛው በሽታ ሲመጣ እንዲለያቸው ማድረግ ነው።

የሰውን በሽታ የመከላከል ሥርዓት “ከፍ ማድረግ” የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ምናልባትም እነዚህን ምላሾች የበለጠ ንቁ ወይም ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርግ ይሆናል።

አትክልትና

የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ሥርዓት

የጉንፋን ምልክቶችን ይውሰዱ የሰውነት ህመም፣ ትኩሳት፣ የጭንቅላት መክበድ፣ . . . ። እነዚህ ሁሉ በቫይረሱ የተከሰቱ አይደሉም። ይልቁንም አካልዎ በተፈጥሮአዊ መንገድ የሚያነቃቃቸው የበሽታ መከላከል ምላሽ ክፍሎች ናቸው።

ከአፍንጫ የሚወጣው ፈሳሽ በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለማስወገድ ይረዳል። ትኩሳቱ በሽታው እንዳይባዛ የሚቸገርበትን ሞቃት አካባቢ እንዲኖር ይረዳል።

ህመም እና አጠቃላይ ህመሙ የሚያስከትሉት ስሜት የሰውነት የበሽታ ተከላካይ ሴሎች ምን መሥራት እንዳለባቸውና ወዴት መሄድ እንዳለባቸው የሚነግራቸው ነው። ምልክቶቹ እንቅስቃሴ እንድንቀንስና ሰውነታችን እንዲሻለው ለአዕምሯችን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።

ሌላውን የበሽታ መከላከያ ገፅታ የመላመድ በሽታ ተከላካይ ሥርዓት ነው። ለምሳሌ አለርጂዎች የሚከሰቱት ሰውነት አይስማማኝም ብሎ በሚያስበው ነገር ላይ የሚሰጠው ምላሽ ነው።

ነገር ግን የተወሰኑ የበሽታ ተከላካይ ህዋሳትን የሚያጎለብቱ ምርቶች “አጎልብተው” ባይሆንም የበሽታ መከላከያ ምላሽን ጠቃሚ በሆነ መንገድ ሊያሻሽሉ ይችላሉ ብለን እንገምታለን።

“ችግሩ ብዙዎቹ ማስረጃ የላቸውም” ብለዋል ኢዋሳኪ፡፡ ስለዚህ በምን ላይ የተመሠረተ ነው?

ጤናማ ከሆኑ ከቫይታሚን ዲ ውጭ ያሉ ተጨማሪ ነገሮችን ይርሱ።

የቫይታሚኖች ሚና

ብዙ መልቲቫይታሚኖች “የበሽታ መከላከል” ድጋፍ ይሰጣሉ ወይም “ጤናማ የበሽታ መከላከያ ተግባርን ጠብቆ ለማቆየት” ይረዳሉ ቢሉም ቢቢሲ ከአራት ዓመት በፊት እንደዘገበው ተጨማሪ ቫይታሚኖች ጤናማ ሰዎች ላይ አይሰሩም፤ አንዳንዶቹም ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቫይታሚን ሲን ይውሰዱ። ሆኖም የቪታሚን ሲን ጉንፋንን እና ሌሎች የመተንፈሻ አካላትን በሽታ ለመቋቋም እንድንችል በማገዝ ትልቅ ሚና እንዳለው የሚየሳይ ትንሽ ማስረጃ ብቻ ነው።

ኮችሬን የተባለ ታዋቂ ድርጅት በፈረንጆቹ 2013 ባደረገው ምርምር አዋቂዎች ላይ “ከፍተኛ መጠን ያለው የቫይታሚን ሲ የበሽታ ምልክቶች መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከተሰጠ በተለመደው የጉንፋን ምልክቶች ቆይታ ወይም ክብደት ላይ ምንም ለውጥ የማያመጣ መሆኑን ነው።”

ባደጉት አገራት ያሉ ሰዎች ቫይታሚን ሲን ከምግባቸው ያገኛሉ። ይህም ጠቃሚ ነው ቢባልም በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ ቪታሚን ከፍተኛ መጠን መገኘት የኩላሊት ጠጠርን ያስከትላል።

“ጉድለት ከሌለዎት በስተቀር የቫይታሚን ምግቦች ለበሽታ መከላከያ ሥርዓትዎ ጠቃሚ አይደሉም” ብለዋል ኢዋዋኪ።

በርካታ ጥናቶች ዝቅተኛ የቫይታሚን ዲ መጠንን ከመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች እና ከፍ ካለባቸው ከባድ ምልክቶች ጋር ያያይዙታል።

በእርግጥ ብዙ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ቫይታሚን ዲን በንቃት መገንዘብ ይችላሉ። እናም ምንም እንኳን በትክክል ምስጢር ሆኖ የሚቆይ ቢሆንም በነበረም ሆነ በተላላፊ በሽታ ምላሽ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታሰባል።

የቪታሚን ዲ እጥረት በብዙ አገራት (ሃብታም አገራትን ጨምሮ) ወረርሽኝ ነው። ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ በዓለም ዙሪያ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቂ ቫይታሚን ዲ እንዳላገኙ ይገመታል።

ኮሮናቫይረስን ለመከላከል

እራስን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ይረዳሉ በሚል በርካታ በተጨባጭ መረጃ ያልተደገፉ ነገሮች በስፋት ይሰማሉ። ነገር ግን እርስዎን የሚከላከል አንድ መንገድ አለ፤ ከሌሎች ሰዎች መራቅ።

ፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶችን ማከማቸት አያስፈልግም።

ነጭ የደም ሴሎች መርዛማ የኦክስጂን ውህዶችን ይለቃሉ። እነዚህም ባለ ሁለት መልክ ናቸው። በአንድ በኩል፣ ባክቴሪያዎችንና ቫይረሶችን እንዳይበዙም ያግዳቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ጤናማ ሴሎችን በመግደል ካንሰርና እርጅና እንዲከሰት እንዲሁም የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ሊያጠፉና ሊጎዱ ይችላሉ።

ይህ እንዳይከሰት ለማስቆም ሰውነት በፀረ-ተህዋሲያን ላይ የተመሠረተ ነው። እነዚህ የማይታዘዙ የኦክስጂን ውህዶችን ለመቆጣጠርና ሴሎቻችንን ደህና ለማድረግ ይረዳሉ። እናም እነዚህን ከምግቦቻችን ውስጥ እናገኛለን።

በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም ዓይነት መድኃኒትም ሆነ ቅመም ከኮቪድ-19 ሊከላከለን እንደሚችል የሚያመለክት ምንም መረጃ የለም።

ስለዚህ ምን አንደሚሠራ ተረጋግጧል?

ኢዋዋኪ እንደሚሉት አብዛኛዎቹ ታሪኮች በአንፃራዊነት የፈጠራ ሲሆኑ የተሳሳተ የደኅንነት ስሜት ይሰጥዎታል። “የማስጠነቅቀው ነገር ቢኖር ሰዎች የደኅንነት ስሜት ሲሰማቸው ወደ ውጭ በመሄድ በድግሶች ላይ እንዳይሳተፉ ነው” ይላሉ።

የበሽታ መከላከያ ሥርዓትን የሚያጎለብቱ ዘዴዎች አሉ። የሚያማልሉ ወይም ታሽገው የሚሸጡ አይደሉም። ገንዘብዎንም አይጠይቁም፤ በቂ እንቅልፍ ያግኙ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡና ጭንቀትን ለማስወገድ ይሞክሩ።

ይህ ካልተሳካ ለተወሰኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን መከላከያ የሚሆን አንድ እርግጠኛ መንገድ አለ፤ ክትባት። ነገር ግን እስካሁን ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የተገኘ ነገር የለም