
ግንቦት 04, 2020
ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ተከልከሎ የቆየው በእንስሳት እና በእጽዋት ላይ የሚካሄድ የዘረመል ለውጥ (ቅይስ) አካል GMO ምርምር ከአስር ዓመት በፊት ተጀምሯል፡፡ ይሁንና ጉዳዩ በባለሙያዎች እንኳን ሳይቀር አከራካሪ ሆኗል፡፡ በዚህ ጉዳይም ላይ የባለሞያ የሆኑትን በኢትዮጵያ ግብርና ኢኒስቲትዩት የግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ አስተባባሪ ዶ/ር ታደሰ ዳባን እና በፊንላድ ሂልስንኪ ዩኒቨርስቲ የድህረ ዶክትሬት ተመራማሪ የሆኑትን ዶ/ር ክፍለማሪያም የኋላን አነጋግረናል፡፡