Image may contain: 1 person, sitting

አስቴር በዳኔ ስለ ልደቱ አያሌዉ !
**************************
ልደቱ አያሌው አይችልም ፤

ልደቱ አያሌው አቅም የለውም ፤

ልደቱ አያሌው ጥበብ የለውም ፤

ልደቱ አያሌው እድለኛ አይደለም ።
.
.
.
.
ማስመሰል አይችልም ።
ቲፎዞ የማሰባሰብ አቅም የለውም ።
የኢትዮጵያን ህዝብ እንዲወደውና እንዲቀበለው የሚያግባባበት ፤ የውሸት ደራማ ሰርቶ እንዲደግፈው፤ እንዲጮህለት፣ እንዲከተለው የሚያደርግበት ጥበብ የለውም ።

ለዚህች የዘመናት የፖለቲካ ህምተኛ የሆነችን ሀገር ፈውስ የሚሆን ሀሳብ ለማመንጨት ዘመኑን ሰጥቶ ቢታገልም ተቀባይነት አግኝቶ አያውቅም ።

የሱ ደጋፊዎች በሳል የሆኑ ሰዎች ቢሆኑም ቅሉ የሚደግፉት በጓዳ እንጂ በአደባባይ ስለማይወጡለት ሁሌ ብቻውን ቆሞ ሲሟገት ይታያል።

ራሱን የሚሰዋለት፣ ድንጋይ ኮልኩሎ መንገድ የሚዘጋለት ደጋፊ የሌለው እድለቢስ ሰው (ፖለቲከኛ) ነው።

ሁሉም ተቃዋሚዎቹ ስሙን ለማጥፋት ተግተው ይሰራሉ፣ የሚያመነጫቸውን የፖለቲካ ሃሳቦች ግን እያደነቁ እንድም ሳይቀር እየሰረቁት ለብሰው ያጌጡበታል።

በብልጣብልጥ አቀራረባቸው የሱን ሃሳብ የራሳቸው በማስመሰል አቅርበው ተወዳጅነትን ይሸምቱበታል። እሱ ግን እንደተጠላ እንደተወገዘ ይኖራል።

ልደቱ አያሌው ሲኖር ሳይሆን ሲሞት የሚወደስ ዓይነት ሰው ነው። ሁልጊዜ እውነትን ብቻ እርቃኗን ሳይቀባባ ሲናገራት እንደክርስቶስ “ስቀለው፣ ስቀለው!” የሚል ድምፅ ነው የሚከተለው። *የልደቱን ግን ለየት የሚያደርገው መሰቀያውን መስቀል ራሱ ማዘጋጀቱ ነው ።*

እንደሚያስጠላው እንደሚያስወግዘው ቢያውቅም አብሯቸው የሚማከራቸውን ሰዎችና አመቺ ጊዜ አይመርጥም። ለሱ እውነት ሆኖ ከተሰማው በቃ ከማድረግ ወደኃላ አይልም። የደጋፊዎቹን የልብ ትርታ ተከትሎ አይሄድም።

አስደንጋጭ እውነቶችን ፍርጥ አድርጎ ይናገራል።
ምን እንደሚያመጣበት እያወቀ ሁሉ ከመናገር ወደኃላ አይልም። እኔ ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ፤ አንዳንዴ ደሞ በጣም ያናድደኛል! ግን ተሟግቼ ላሸንፈው አልችልም ።

የሚነሳቸው ነጥቦች አሳማኝ ናቸው። ተቀባይነት አያገኙም እንጂ። **የሀገራችን የፖለቲካ ትንሳኤ ሊመጣ ያልቻለው የልደቱ አያሌው አይነት ሰዎችን ገፍትሮ ዳር የሚያስቀር በመሆኑ ነው።**

በሰሞኑ እንኳን በዚህ አውራ ጉንፋን ዓለሙን በፍርሀት ሸብቦ የፖለቲካ ጨዋታው ቀዝቅዞ ወደ መቃብር ሲሄድ ቀስቅሶ ያስነሳው ልደቱ አያሌው ነው።

“በዘመናት መሀከል አቋሙ አንድ ነው።” የማይለዋወጥ ማንነት ባለቤት ነው። **ከሀገር አንድነት ውጪ አፍራሽ አቋም የለውም።* ግን ከሱ ይልቅ ሀገር የሚያፈርስ አቋም ያላቸው እልፍ ጭፍን ተከታይ ስላላቸው ከነ ወንጀላቸው ደረታቸውን ነፍተው ሲደነፉ የሚናገራቸው የለም።

“እሱ ላይ ግን ድንጋይ የማይወረውር የለም፤” ባጠቃላይ ጥሩ መጫወት እንጂ የጎል አድል የለውም። እድለቢሱ ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው ።

በ ር ታ !