by ዘ-ሐበሻ
May 6, 2020
- የኤርትራ መንግሥት፣ የትግራይ መንግሥት፣ የኦሮሚያ መንግስት
- የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች፣ የመቶ ዓመት ስውር የዘር ካርታና የፖለቲካ ሴራ!
- የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች፣ አንድም፣ሁለትም፣ሶስትም ናቸው!!! የመቶ ዓመት የዘር ካርታና የፖለቲካ ሴራ!
- አዲስ አበባ ከተማ ከ1889-2020 እኤአ የኢትዮጵያና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን 131ኛ ዓመቷን ያዘች!!!
የኢትዮጵያ የጅኦ-ፖለቲካዊ ግዛት
በታሪካችን ጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ታሪኮች እስከ ዘመነ መሳፍንት (የስርወ- መንግሥት ዘር ነገሥታት) ቀጥሎ የዐፄዎች ንጉስ ነገስት ዘኢትዮጵያ ታሪክ፣ወደጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ብሎም ህወሓት /ኢህአዴግ፣ ብሎም ኦዴፓ ብልፅግና/ ኢህአዴግ ላይ ደርሰናል፡፡ የኢትዮጵያ ነገሥጣት የመናገሣ ከተማ ከአረብ አገር ወደ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ግብፅ፣ ከግብፅ ወደ ኖብያ….ሜሮኤ፣ አክሱም….ላስታ….በረራ… ጎንደር… ሸዋ…አዲስ አበባ እየተዘዋወረ የኢትዮጵያ ነገሥታት በየዘመናቸው ነግሠዋል፡፡ በዘመነ መሣፍንት ግዜ የተለያዩ የሥርወ- መንግሥት ዘር ነገሥታት የራሳቸው ነገስታት እንደነበራቸውታሪክ ያስረዳል፡፡ በወለጋ የጀቴ፣ የከፋውየቀዳማዊ አባጅፋር አባ መልካ፣ አባ ቆሮ..ሚካኤል ሁለተኛውንጉስ ወሎ ወትግሬ፤ ሣህለ ሥላሴ ንጉሠ ሸዋ፤ ተክለ ሃይማኖት ንጉሠ ጎጃም ወከፋ፤ ኃይለ መለኮት ንጉሠ ሸዋ፤ወልደ ጊርጊስ ንጉሰ ጎንደርበጌምርድ ሰሜን ወዘተ ሆነው ነገሠዋል፡፡ ከዘመነ መሳፍንት በኃላ ተክለጊዮርጊስ፤ ቴዋድሮስ፤ ዮሐንስ፤ ሚኒልክ፣ ኢያሱ፣ ዘውዲቱ፣ ቀኃሥ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነግሠዋል፡፡
ከዛም ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማርያም ወታደራዊ መንግስት፣ ህወሓት/ ኢህአዴግ ፕሬዜዳንት መለስ ዜናዊ፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ዘመነ መንግሥት ላይ ደርሰናል፡፡ በአፄ ሚኒልክና በእቴጌ ጣይቱ ቡጡል አዲስ አበባ ከተማ ከ1889እኤአ የኢትዮጵያና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን 131ኛ ዓመቷን አከበረች!!!
በኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም አንባገነን ወታደራዊ አገዛዝ በኃላ ሽፍታ አንባገነናዊ የሲቪል የጦር አበጋዞች መንግስት በኢትዮጵያ ምድር እንደ ፍልፈል ተፈለፈሉ፣ ከኤርትራ ከአፋአቤት በርሃ በሻቢያው ኢሳያስ አፈወርቂ ተጠነሰሰ፣ ከትግራይ ከደደቢት በርሃ በወያኔው መለስ ዜናዊ ተቀጣጠለ፣ በወለጋ በርሃ በኦነጉ ሌንጮ ለታ ተስፋፋ፡፡ ፊንፍኔ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማነት ተመረጠች፡፡ እንዲሁም ድሬዳዋና ሀረር በኦሮሞ 40/40/20 የአፓርታይድ አገዛዝ ስር ወደቁ፣ በአዲስ አበባም የአፓርታይድ አገዛዝ ለመጫን አንድ ሐሙስ ቀርቶታል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከ1889እኤአ የኢትዮጵያና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን 131ኛ ዓመቷን በአከበረች ማግስት ኢትዮጵያ ‹‹የጥቁር አንበሳ›› ተምሳሌነቷ ትታወቅ እንዳልነበር በ”ፒኮክ” (ጣዖስ)ነት ተምሳሌት እንድትተካ በዶክተር አብይ አህመድ ተፈረደባት!!! የአዲስ አበባ፣ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ አዳማ፣ አዋሳ፣ ህብረ ብሄር የከተማ ህዝብ ነፃነትና መብቱን ለማስከበር ቆርጦ መነሳት አለበት እንላለን፡፡
• “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ህዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሙሉ ክፍት ቦታዎችን በቅጥር ለመሙላት በሚል በ2010 አና 2011 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን በዜሮ አመት ለመቅጠር ባወጣው መስፈርት መሰረት የአዲስ አበባ መታወቂያ ያላቸውን ማወዳደሩ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሉት ከሆነ መስፋርቱን አሟልተን ፍተናውን ተፈትነን ከማለፊያ ውጤት በላይ አስመዝግበን የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ቋንቋ (ኦሮሙኛ!) አትችሉም በማለት ከኛ ውጤት በታች ያመጡ አካላትን ቀጥረው እኛን ሳያካትቱን ቀርተዋል። በተጨማሪም እኛ የአዲስ አበባ ተወላጆች ተገፍተን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መመሪያ መታወቂያ በህገወጥ መንገድ እየተሰራላቸው ከክፈለ ሃገር የሚመጡ አማርኛ ቋንቋ መግባባት የማይችሉ አካላት ቅድሚያ እየተቀጠሩ ይገኛል ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።” (.”አዲስ አበባ ተወልደን ኦሮምኛ አትችሉም ተብለን ከሥራ ተገፍተናል። / የፐብሊክ ሰርቪስ አመልካቾች by ዘ-ሐበሻ/May 4, 2020May 4, 2020)
• አንድ የማከብራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ወያኔ በአማራ ሕዝብ እምቢተኝነትና አይበገሬነት ስለተርበተበተ፣ ይህን ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለመነጠል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው በማለት በቅርቡ የታዘቡትን አጫውተውኛል፡፡ እኚህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረትና ለአገራችን አንድነት ፍጹም ቀናኢ የሆኑ የፖለቲካ ሰው እንደገለጹልኝ፣ ሰው በላው ስብሐት ነጋና ሌሎች የወያኔ መሪዎች የተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ፖለቲከኞችን እየቀረቡ፣ ከአማራ ውጪ ያሉት ሕዝቦች ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ካልፈጠሩና የአማራውን እንቅስቃሴ ካልመከቱት በስተቀር የድሮው ሥርዓት ተመልሶ አስፈሪ መልክ ይዞ እየመጣ ነው በማለት እየቀሰቀሱ ነው፡፡ እነስብሐት ነጋ ጸረ ነፍጠኛ ሲሉ ጸረ አማራ ማለታቸው መሆኑን ማንም ይስተዋል ብለን አናምንም፡፡ ስለሆነም እነዚህ ነብሰ ገዳዮች ጸረ አማራ ግንባር ለመፍጠር ላይ ታች እያሉ ነው!!! (ጸረ ነፍጠኛ ግንባር?! (የነስብሐት ነጋ የጥፋት ድግስ!) – ሙሉቀን ተስፋው/September 28, 2016 )
መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፡፡ ሃገርና ህዝብ ግን ይቀጥላል!!!
የኢትዮጵያ ሃገረ-መንግሥት/ ሥርዓተ-መንግሥት፡- አንደኛ መገለጫው የፀና ህጋዊ ኩታ ገጠም መሬት ግዛት፣ ክልል፣ ድንበርና ወሰንተኛ አጎራባች ሃገራቶች ያለው ሲሆን ፣ሁለተኛ መገለጫው የፀና ቆሚ ህዝብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የትየለሌ ቅምቅም አያት የዘር ግንድ ያለው ሲሆን ሦስተኛው መገለጫው ደግሞ ተለዋዋጭ መንግሥታዊ አስተዳደር እንደ ክረምትና በጋ የሚፋረቁበት መንግሥት ያለው ነው፡፡ ሃገረ-መንግሥት አገዛዝ ለብቻው ጠቅልሎ የያዘው በትረ ሥልጣን ያለአንዳች ተቀናቃኝ ኃይል የመጠቀም ህጋዊ ፍቃድ ያለው ያደርገዋል፡፡ ሥርዓተ-መንግሥት አገዛዝ ሉዓላዊነቱ በሌሎች ሃገራቶች የተረጋገጠለትና በዓለም አቀፍ ሥርዓት የተመሠከረለት ያደርገዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ሻብያ ኤርትራን ከገነጠለ በኃላ የፌዴራላዊ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኢትዮጵያ ወሰን በሰሜን ኤርትራን፣ በሰሜን ምስራቅ ጅቡቲን፣ በምስራቅ ሱማሌን፣ በደቡብ ኬንያን፣ ደቡብ ሱዳን ደቡብ ምእራብ፣ ሱዳን በሰሜን ምዕራብ አዋሳኝ ጎረቤት አገራት ሆኑ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ክልሎች ወሰንና ድንበር ሊኖራቸው አይገባም እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከቦታ ቦታ በሃገሪቱ ውስጥ ተዘዋውሮ እንዲሰራ፣ ኃብት እንዲያፈራ መብቱ መጠበቅ አለበት እንላለን፡፡ ክልሎች በቌንቌ ተካለውና ድንበር ከተካለሉ ንዋሪውን አንዱን ‹‹መጤ›› አንዱን ‹‹ነባር›› ማለት የመጣው የክልሎች አወቃቀር በኃላ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ከጀመረ ወዲህ የሃገሪቱ የጅኦ-ፖለቲካዊ ግዛቶች በተለያዩ አስተዳደር ክልሎች በየዘመነ መንግሥቱ ለውጥ ተካሄዶባቸዋል፡፡ የአስተዳደር ክልሎች ክፍፍል መሠረትና ዋነኛ መሥፈርት የኢኮኖሚ ሁኔታና የጆግራፊ ባህሪያት ፣ የአስተዳደር ብቃትን፣ ከጎረቤት አገሮች ያለው ድንበር ፣ የፖለቲካ ፣ የመከላከያና የፀጥታ ሁኔታን፣ የቌንቌና ባህል፣ የብሄረስብ ስብጥርና የህዝብ ብዛት ከመልካ ምድሩ አቀማመት ጋር ለእርሻ የመስኖ ልማት አመችነት፣ ለሸንኮራ አገዳ ለስኳር ፋብሪካዎች ግብአት፣ የቡና ተክል፣ የሰሊጥ የቦለቄ የስንዴ፣ የገብስ፣ ኩታ ገጠም መሬቶች፣ የኢንዱስትሪ ዞኖች፣ የአግሮ ኢንዱስትሪ ዞኖች፣ ወዘተ በአስራአንዱ የወንዝ ተፋሰስ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታንና የስራ ዕድል ፈጠራን ጠቀሜታን ታሳቢ ያደረገ የጅኦ- ፖለቲካል ግዛቶች ማካለል ሳይንሳዊ የእድገት ጎዳና የምርት እድገት በመጨመር በምግብ ራሳችንን እንድንችል የሚያደርግ የአስተዳደር ዘይቤ ነው እንላለን፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግና ብልፅግና/ኢህአዴግ ላለፈው 29 ዓመታት በቌንቌ በዘር የተከፋፈለ አስተዳደር ያስገኘው ጥቅምና ጉዳት በጥናት ቀርቦ መገምገም ይኖርበታል እንለለን፡፡ የፌዴራል ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያ ወሰንና ግዛት በስተቀር ክልላዊ መንግሥቶች የራሳቸው ድንበርና ወሰን ሊኖራቸው አይገባም እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስቶች የማያባራ ጦርነት ዋና ምክንያት በድንበር ግጭት የተነሳ ነው፡፡ በሃገሪቱ በመንግሥት ውስጥ ዛሬ አስር መንግሥት፣ ነገ መቶ መንግስቶች መፈጠር የድንበር ግጭቱን ያባብሰዋል እንላለን፡፡ ክልሎች እራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር፣ በመንግሥታዊ አስተዳደራዊ መዋቅሮች ህዝብ ማገልገል፣ በየቌንቌ መማር፣ መዳኘት፣ በሚዲያ አገልግሎቶች መጠቀም፣ ባህላቸውን ማዳበር፣ ወዘተ የመሳሰሉት መብቶቻቸው ይጠበቅላቸዋል፡፡
• በቀኃሥ ዘመን አትዮጰያ 12 ጠቅላይ ግዛቶች፣ 60 ወረዳዎችና 339 ምስለኔዎች ተከፋፍላ ትተዳደር ነበር፡፡ በመቀጠልም ሃገሪቱ በ12 ጠቅላይ ግዛቶች፣ 101 አውራጃዎችና በ577 ወረዳዎች ተከፋፍላ ነበር፡፡ ኤርትራ፣ ትግራይ፣ በጌምድር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ወለጋ፣ ሸዋ፣ ኢሉባቡር፣ ከፋ አርሲ፣ ጎሞጎፋ፣ ሲዳሞ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ ነበር፡፡ በ1889 እኤአ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና መዲና ሆና በእቴጌ ጣይቱና በንጉስ ነገስት ዳግማዊ ሚኒሊክ ተቆረቆረች፡፡ በ1991 ሻብያና ወያኔ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡ መንግስቱ ኃ/ማርያም ዝንባዌ ተሰደደ፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ በ1993 እኤአ ኤርትራ ከኢትዮጵያ አስገነጠለ፡፡ በ1994 በኢትዮጵያ አዲስ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፌዴራላዊ የዘውጌ መንግስት ተመሠረተ፡፡››1አዲስ አበባ ከተማ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን ለ131ኛ አመታት አገልግላለች፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ የሃገሪቱን በዘጠኝ ክልላዊ መንግስቶች በሸነሸናት ጊዜ የአዲስ አበባ መዲና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በማድረግ የኢትዮጵያና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት መዲና በህዝብ ልብ ውስጥ መልህቁን እንደጣለ አለ፡፡
• በወታደራዊ ደርግ ዘመን፣ ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም አስተዳደር ኢትዮጵያን በ5 የራስ ገዝና 25 የአስተዳደር አካባቢዎች ተሸንሽና ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ለኤርትራ፣ለትግራይ፣ ለአሰብ፣ ለኦጋዴንንና ለድሬዳዋ የራስ ገዝ አስተዳደር ተሰጥቶቸው ነበር፡፡ የድሬዳዋ ከተማ ህዝብ ከዚህ ወርቃማ መብቱ ወርዶ በህወሓት/ ኢህአዴግ የአፓርታይድ አስተዳደር ስር መውደቆ ነፃነት በልመና አይገኝምና ለመብቱ ሳተናውን ይዞ የባርነት ሠንሰለቱን በጣጥሶ ከመታገል ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳደር ህዝብም በአፍንጫውን ይዘው እንደ ፈረስ ልጎም ለጉመው የድሬዳዋን 40/40/ 20 የአፓርታይዱ ሥርአትን ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ መታገል አለበት እንላለን፡፡ ከአማካን ሰው ዝቅ ያሉ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልፅግና ካድሬዎችን አስተዳደራችሁ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን አይመጥንም ልንላቸው ይገባል፡፡ በኮሮና ቨይረስ ሰበብ ለአምስት ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ህዝብ በኦዴፓ ብልፅግና አስፈፃሚነት የታቀደው የፖለቲካ ሴራን ለመፈፀም ይሞከራል፡፡
• በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን መለስ ዜናዊ፣ በህወሓት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት፣ የኢትዮጵያ አስተዳደር በአስራአራት ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳደር መንግስት ተሸነሸነች፡፡ ቀጥሎም ህወሓት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በዘጠኝ ክልላዊ መንግሥቶች አማራ ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ሃረሪ፣ ብሎ ደለደለ፡፡ ህወሓት በጥናት ላይ የተመሰረተ ክልላዊ መንግሥት አላዋቀረም እንዲሁም ክልል የሆኑበትን መስፈርት ፣ ብሄር ብሄረስብና ህዝቦች ያሉበትን መስፈርትና መመዘኛ አላስቀመጡም የህዝብ ብዛት፣ በቌንቌ፣ ታሪክ፣ መኖሪያ ግዛት፣ ባህል ወዘተ የክልል መስፈርት በግልጽ አልሰፈሩም፡፡ በስምንቱ ክልሎች ላይ መስፈርቱ በቌንቌ ላይ የተመሠረተ ሲሆን በደቡብ ክልል በህብረ-ብሄርነት ላይ የተመሠረተ ነዉ፡፡ የክልሎቹ አከላለል አንዱን ከአንዱ የሚያበላልጥና የበፊት የመሬት ይዞታውን መንጠቅ፣ የህዝብ ፍቃድ ያልተጠየቀበት፣ የአንድ ቌንቌ ተናጋሪን በሁለት ክልሎች መሸንሸን፣ በአንድ ክልል ቌንቌ ተናጋሪ ያልሆኑት ንዋሪዎች መብትና ግዴታ በህገመንግስትና በህግ ያለመቀመጡ፣ በአንድ ሃገር አንዱ ዜጋ አንዱ መጤ ተብሎ የመኖር የዴሞክራሲና መብት ገፈፋ ላለፉት 27 አመታት ተስተውለዋል፡፡ ለህወሓት ኢህአዴግ መውደቅ የሃገሪቱን ዜጎች አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ የማድረግ ኢዴሞክራሲያዊ አስራር ነበር፡፡ በሃገሪቱ ባሉ 80 በላይ ቌንቌ ተናጋሪዎች ዘጠኙን ብቻ ክልላዊ መንግሥ አድርጎ በህገ-መንግሥቱና በህብረ ብሄር ፊዴራሊዝም እየማለና እየተገዘተ የፖለቲካ ስልጣኑን የሚኒስትር፣ ዲፕሎማት፣ የጀነራል መኮንን ስልጣን በሙሉ በህወሓት ካድሬዎች ተቆጣጥሮ ለ27 አመታት ኃብትና ንብረት ዘረፈ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ድርጅት አራቱ ህወሓት፣ በሹፊርነት ዋነኛዎች ተዋናዬች ሲሆኑ በወያላነት ደግሞ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን የድርሻቸውን ሃብት ዘርፈዋል ኢስብአዊ ድርጊት ፈፅመዋል፡፡ እንዲሁም አምስቱ አጋር ክልሎች ሱማሌ፣ አፋር፣ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉልና፣ ሃረሪ አጋር ድርጅቶች ተብለው በየክልላቸው ለ27 አመታት በፈላጭ ቆራጭነት አስተዳድረዋል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በረቀቀ ዘዴ በክልሎች ማህል የልተመጣጠነ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖርና የተዛባ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር አድርጎል፡፡ በየክልላቸው በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ወያኔ ፈላጭ ቆራጭ አንባገነን መሪ በመሆን ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውንና ማህበራዊ ጉዳዩን በመዳፉ በመጨበጥ የህዝብ ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ረግጦል፣ በአይን አውጣ ስግብግብነት አገር ዘርፎል፣ አስተዳደሩ አድሎዊና በሙስና ሌብነት የተጨማለቀ የቦዘኔዎች ስብስብ ለመሆን በቅቶል፡፡ የህወሓት የህዝብ ልጅነት ወደ ጨካኝ ህገ አራዊትነት በተሸጋገረበት ጊዜ በኦሮሞ ህዝባዊ እንቢተኝነትና በአማራ ህዝባዊ አመፅ የሥልጣን መንበሩን ተነጥቆ ህወሓት ለፍርድ ሳይቀርብ መቀሌ ለመመሸግ ተገደደ፡፡
• በብልፅግና/ኢህአዴግ ዘመን ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ መቶ ክልላዊ መንግሥቶች አማራ ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ሃረሪ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ከንባታ፣ ) ጌዲኦ፣ ከፊቾ፣ ወዘተ ኦዲፒ/ ብልፅግና የፌዴራል ሥርዓቱን በማስቀጠል ህገ-መንግስቱን እስከቀጠለበት ድረስ የክልል መንግሥቶች እንደ አሸን ይፈላሉ፡፡
የሻብያ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ወያኔ መለስ ዜናዊ፣ኦነግ ሌንጮ ለታ የኢትዮጵያ ቅኝ ገዥነት የውሸት ትርክትን በማመንጨት በጠመንጃ አፈሙዝ በህዝቡ ዘንድ ያልነበረን የማንነት ጥያቄን በኃይል በመጫን፣ የስነልቦና ጥቃት በህብረተሰቡ ላይ በማድረስ፣ በኃይል በመጠቀም ተቃዋሚያቸውን በማጥፋት የኤርትራዊነት፣ የትግራዋይነትና የኦሮማይነት የማንነት መታወቂያ በመስጠት የንግድ ድርጅታቸውን የፈጠሩ ጦር አበጋዞች ናቸው፡፡ ሻብያ፣ ወያኔና ኦነግ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመቶ ዓመት የቤት ስራ እንደሰጡንና በፊት በሃገሪቱ በስተ ሰሜን የነበረ ጦርነት ወደ መኃል አገር ጦርነቱን በመዘወር በኤርትራና ትግራይ የሠላም ቀጠና በቀሪው ኢትዮጵያ የማያባራ የዘር ጦርነትና የውክልና ጦርነት ተክለውብናል፡፡
የወያኔ የዘር ካርታ፣(ከ1983 አስከ 2012) 27 ዓመት ሞላው!
በኢትዮጵያ ግዛት የወያኔ የዘርና ቌንቌ ተኮር ካርታ፣ ከተነደፈና ተግባራዊ ከሆነ (ከ1983 አስከ 2012) 27 ዓመት ሞላው! የኤርትራ መንግሥት፣ የትግራይ መንግሥት፣ የኦሮሚያ መንግስት፤ ሻብያ፣ ወያኔ፣ ኦነግ ጦር አበጋዞች መንግሥት ህገመንግሥት ተርጉመው በማጸደቅ ብሄሮች መብት ራስን ማስተዳደር እስከመገንጠል የሚል አንቀፅ አፀደቁ፡፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሥር የሚገኙ ክልላዊ መንግሥቶችም (1) አማራ ፣ (2) ትግራይ፣ (3) ኦሮሚያ፣ (4) ጋምቤላ፣ (5) ደቡብ፣ (6) አፋር፣ (7) ሱማሌ፣ (8) ቤኒሻንጉል ጉሙዝና (9) ሃረሪ፣ (10)ሲደማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት (11) ወላይታ (12) ጉራጌ (13) ስልጤ (14) ከንባታ (15) ጌዲኦ (16) ከፊቾ (17) ወዘተ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከአስር ትናንሽ ክልላዊ መንግስትነት ወደ መቶ ትናንሽነት እንድትሸነሸን ተፈርዶባታል፣ ከዛም ህዝቡን በማያባራ የድንበር ጦርነትና የውክልና ጦርነት ውስጥ ይከቱታል፡፡ ይህ በዚህ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ህዝብ መጭው ዘመን የሞት፣ የእስራትና የስደት ይሆናል እንላለን፡፡
የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች በኤርትራም፣ በትግራይና፣ በኦሮሞ ስም አስሬ ቢምሉም ቢገዘቱም፣ የህዝቡ እጣ ፈንታ ሞት፣ እስራትና ስደት በቀር የተረፈው ነገር የለም፡፡ የጦር አበጋዞቹና በስልጣን ሱስ በሰከሩ፣ አድርባይ ምሁራን በዴሞክራሲ ስም፣ በፌዴሮሽን ስም፣ በህገ-መንግሥት ስም በህዝብ ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፡፡ የሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ የጦር አበጋዞች ከህዝብ በዘረፉት ኃብትና ንብረት ተንደላቀው ይኖራሉ፡፡ ሻብያ ኤርትራን ገንጥሎ የቻለውን ሁሉ ዘርፎ ሄዶል፡፡ ወያኔ ዘርፎ ትግራይ ገብቶል፣ ኦነግም ዘርፎ ወለጋ መሽጎል፣ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልጽግናም የመቶውን አመት ስውር የፖለቲካ ሴራ ለማስፈፀም ላይ ታች ይላል፡፡ የፖለቲካው ሴራ ሲተነተን እንኮን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለክልላቸውም ህዝብ እንደማይበጁ እውነተኛ ማስረጃውን እንሆ እንላለን፡-
የጦር አበጋዞች የክልላዊ መንግስታት የዘር ካርታ
የወያኔ የዘር ካርታ፣(ከ1983 አስከ 2012) 27 ዓመት ሞላው!
በኢትዮጵያ የክልል መንግሥት ድንበሮች/ ወሰኞች፣ (Regional state borders) የኦሮሚያ ክልል 9 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአማራ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የትግራይ ክልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የአፋር ከልል 6 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የሱማሌ ከልል 5 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የደቡብ ከልል 4 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የጋምቤላ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉት፣ የሃረሪ ከልል 3 አዋሳኝ ድንበርተኞች አሉዋቸው፡፡ በኢትጵያ የክልል ብሄራዊ መንግሥታት የመስፋፋት ፖሊሰ፣ ሃገሪቱን ወደ ማያባራ የድንበርና የወሰን ግጭት እንደሚዳርጋት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡
የትግሬ ሆነ፣ የአማራ ሆነ፣ የኦሮሞ ሆነ የደቡብ ሆነ በአንድ ዘር የተዋቀረ አስተዳደር ሌሎችን ያገላል፡፡ ዘረኛ ዘረኛ ነው!!!ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ ነው፡፡ ከትግራይነት ዘር ወርዶ ወደ አውራጃ አድዋ፣ ሽሬ፣ አክሱም ሲባባሉ እንሰማለን፡፡ ከአማራነት ዘር ወርዶ ወደ ክፍለ ሀገርና አውራጃ ወርዶ ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ወሎ፣ ሸዌ ሲባባሉ እናውቃለን፡፡ ከኦሮሙማ ወርዶ በአውራጃነት ወለጋ፣ ቦረና፣ አንቦ፣ አርሲ፣ ሀረር ወዘተ መንደር ለመንደር ውረድ እንውረድ ፖለቲካ ካድሬዎች ሲባባሉ እናውቃለን፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ሥራ ውስጥ መግባት የለባቸውም፣ ፓለቲካ ፓርቲዎች በዘር፣ በሃይማኖት መደራጀት የለባቸውም እንላለን፡፡(Political parties organized with ethnic tags are not political parties. They are as one of civic and religious organizations or activists dealing with ethnic issues and are not political parties. It is the most dangerous and destabilizing agent organizing political party along ethnic and religious identities. It is a breeding ground for extremism for exploiting ethnic or religion issues for power and selfish economic motifs of politicians in the name of the tagged ethnic or religious group. Ethiopian constitution allows for parties to organize with ethnic tags, but does not allow religion tags. https://www.proposal-for-a-new-administrative-restructuring-of-Ethiopia.pdf)
በዘመነ አብይ አህመድ የኦህዴድ/ኦዴፓ የብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ በወረሰው ህገ-መንግሥት በኢትዮጵያ በአስሩ ክልላዊ መንግሥቶች አማራ ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ሃረሪ፣ ሲዳማ ውስጥ የሚፈነዳ ህዝባዊ አመፅ ክልል የመሆን ጥያቄ ከወረዳ ወደ አውራጃ፣ ከአውራጃ ወደ ዞን፣ ከዞን ወደ ክልላዊ መንግሥትነት ጥያቄ እንደ ሰደድ እሳት ይቀጣጠላል፣ ሃገራችን አሁን ካለችበት ከአስር ትናንሽ ክልላዊ መንግስትነት ወደ መቶ ትናንሽ ክልላዊ መንግስትነት ትቀየራለች፡፡ ለማጠቃለል፡-
• የ2013 ዓ/ም በኢትዮጵያ ህዝብ ዋና መሰረታዊ ጥያቄና አጀንዳ የሆነውን ህገመንግስትን የማሻሻል ጥያቄ አይቀሬነት ነው፡፡ ህገመንግሥቱ በራሱ ጊዜ የሰጠው ድንጊያ በመሆን ለገጠመን ችግር መፍትሄ መስጠት አልቻለም እንላለን፡፡
• በዘርና በኃይማኖት የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህግ መታገድ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ የክልል መንግሥቶች ድንበርና ወሰን አከላለል በማስወገድ የማያባራ ጦርነትና የውክልና ጦርነት መከላከል እንችላለን፡፡
• የፋይናንሻል የባንክ ዘርፍ በዘርና ቌንቌ መደራጀታቸው ሊታገድ ይገባል እንላለን፡፡
• በሃገራችን የህግ ሉዓላዊነት ይከበር፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደረጉ ህወሓት/ኢአዴግ ለፍርድ ይቅረቡ፣ ህወሓት /ኢፈርትና ሜቴክ ሃገር የዘረፉ ለፍርድ ሳይቀርቡ በሃገራችን ህግና ደንብ ማስቀረብ አይቻልም፡፡ ህግ ማስከበር የማይችል መንግሥ ህዝብ መግዛት አይችልም እንላለን፡፡
(5/6/2020)

