DW : ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰበብ ከግብፅ ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብ እልባት ባያገኝም ግድቡን በመጪዉ ክረምት መሙላት እንደምትጀምር የዉሐ ሚንስቴር አስታወቁ።
ኢትዮጵያ ግድቡን የምትሞላበትን ጊዜ እንድታራዝም ግብፅና ሁለቱን ወገኖች እናደራድራለን የሚሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ግፊት እያደረጉ መሆናቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የኢትዮጵያ የዉኃ፣መስኖና ኃይል ማመንጪያ ሚንስትር ስለሺ በቀለ እንዳሉት ግን ግድቡ ከመጪዉ ኃምሌ ጀምሮ ዉኃ ይሞላል።
አንድ ባለሙያ እንዳሉት ደግሞ ዘንድሮ የሚሞላዉ ወኃ ሁለት ተርባይኖች ማንቀሳቀስ ይችላል።