June 20, 2020

“ሀገረ ትግራይ እንዳይመሰረት እንቅፋት የሚሆነን ህውሓት ነው” የትግራይ ነፃነት ፓርቲ

“ሀገረ ትግራይ እንዳይመሰረት እንቅፋት የሚሆነን ህውሓት ነው” የትግራይ ነፃነት ፓርቲ

DW : “ኢትዮጵያ የትግራይ ብሔራዊ ህልውናና የተጋሩ ብሔራዊ ማንነት የምትቀበል አይደለችም” የሚለው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤው አመራሮቹን መርጧል። የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ደጀን መዝገበ “የትግራይ ብሔራዊ ህልውናና ብሔራዊ ማንነት በተሟላ መልኩ እውን መሆን የሚችለው ትግራይ አገር ሲሆን ነው” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።በቅርቡ በትግራይ ክልል የተመሰረተው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ የተባለው የፖለቲካ ድርጅት የመጀመሪያ ጠቅላይ ጉባኤው አካሂዶ ፕሮግራሙ በማፅደቅ አመራሮቹ መርጧል፡፡ ፓርቲው ትግራይ ክልልን በሰላማዊ ትግል ከኢትዮጵያ ለመነጠልና ሉዓላዊት ሀገር ለማድረግ እንደሚታገል አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀሰው ይህ ፓርቲ በትግራይ ይካሄዳል በተባለው ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ እንዳለም ገልፅዋል፡፡ Audio Player00:0004:43Use Up/Down