የግብጽና የሱዳን ቅጥረኛው አቶ ሱሌይማን ደደፎ አሁንም በሥልጣን ላይ ነው!!!
አቶ ሱሌይማን ደደፎ ግብጽ በሐሰት ወይም በማምታታት “ዐፄ ምኒልክ ዓባይን ላይገድቡ ተስማምተው ፈርመዋል!” የምትለውን ተቀብሎ እንደፈረሙ አድርጎ በአደባባይ በማስተጋባት፣ ሱዳንም በሐሰት “በዐፄ ምኒልክ ተፈርሞ ተሰጥቶኛል የኔ ነው!” እያለች ካልወሰድኩ የምትለውን የሀገራችንን መሬት ፈርመው እንደሰጡ አድርጎ በአደባባይ በማስተጋባት ሰውየው ግብጽንና ሱዳንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሠራ ባንዳ መሆኑን ግልጽ አድርጎና በሀገር ክህደት ወንጀል ላይ ያለ ወንጀለኛ መሆኑን እራሱን አጋልጦ ባለበት በአሁኑ ሰዓትም ሀገራችንን ወክሎ ያውም በዓረባዊ ሀገር አሁንም በአንባሳደርነት ከሚሠራበት ሥራ አልተነሣም!!!
ይሄ ምንን ያሳያል??? እያንዳንዱ የአገዛዙ ባለሥልጣንም እንደ ሱሌይማን ደደፎ አለመናገሩ ነው እንጅ እንደ እሱ ሁሉ በፈጠራ ዐፄ ምኒልክ ዐባይን ላለመገደብ እንደፈረሙና ለሱዳንም መሬት የሰጡ አድርገው በሐሰት በመክሰስ ግብጽንና ሱዳንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሠሩ ባንዶች መሆናቸውን ነው የሚያሳየው ወይም የሚያረጋግጠው!!!
ከእነኝህ የአገዛዙ ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ አንብበው መረዳት የማይችሉ ደናቁርት ስለሆኑ የተቀሩትም የግብጽና የሱዳን ባንዶች ስለሆኑ ግብጽንና ሱዳንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሠሩ ስለሆኑ ነው እንጅ ዐፄ ምንሊክ የፈረሙት የተፈረመውን ውል በመመልከት ማረጋገጥ ይቻላል እንግሊዝ የግብጽና የሱዳን ቅኝገዥ ሆና እስካለች ጊዜ ድረስ የእንግሊዝን መንግሥት ሳያስፈቅዱ የዓባይን ወንዝ ሙሉ ለሙሉ ደፍኖ ወይም ገድቦ ላለማስቀረት ነው እንጅ በየትኛውም ጊዜ ቢሆን የድርሻችንን በከፊ ወይም በአብዛኛው ገድቦ ላለመጠቀም ፈጽሞ አልፈረሙም!!! ያም ስምምነት ቢሆን እንግሊዝ “የሱዳንና የግብጽ መንግሥት ነኝ!” ብላ ስትገዛ የነበረችበት የቅኝ ግዛት አሥተዳደሯ ባከተመለት ጊዜ አብሮ አክትሞለታል!!!
በዚሁ 1902ዓ.ም. በተፈረመው ስምምነት አንቀጽ አንድ ላይና ከውሉ ጋር ተያይዞ በቀረበው ካርታ ላይ በሐሳብ መስመር ዲግሪዎች በሚገባ ተገልጦ በግልጽ ተሰምሮና ተመልክቶ የተስማሙት የድንበር ስምምነት የሚያረጋግጠውም የካርታ ሥራ ባለሞያዎችን መጠየቅ ትችላላቹህ ሀገራችን ከሱዳን ግዛት ላይ ወደ እኛ መምጣት ያለበት በርካታ መሬት ያላት መሆኑን ነው እንጅ ከእኛ ወደ ሱዳን የሚሔድ መሬት መኖሩን አያረጋግጥም!!! ወያኔ/ኢሕአዴግ ግን ይሄንን ስምምነት በመጥቀስ ዐፄ ምኒልክ ለሱዳን የሰጡት መሬት ያለ በማስመሰል በትጥቅ ትግሉ ወቅት ሱዳን ለዋለችለት ውለታ ቃል ገብቶላት የነበረውን ሰፊ መሬት ለመስጠት ስለሚፈልግ በገበሬው ጥረት ሊሳካ አልቻለም እንጅ እንደምታዩት ሰፊ የሀገራችንን ግዛት ለሱዳን ለማስረከብ ሲጥር ቆይቷል አሁንም እየጣረም ይገኛል!!! እናም እውነቱ ይሄ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው የወያኔ አህዮች እነ ሱሌይማን ደደፎም ዐፄ ምኒልክን ባልዋሉበት በማዋል ለሱዳን መሬት የሰጡና ዐባይን ላለመገደብ ፈርመዋል የሚሉት!!!
ይሄንን ስል ብዙዎቻቹህ እየተገነባ ያለው የዓባይ ግድብ ለኃይል ማመንጫነት ብቻ እንጅ ለመስኖ ልማት አለመሆኑን ባለማስተዋል “እንዴ ምን ማለትህ ነው? የምትወነጅለው አገዛዙ አይደለም ወይ ዓባይን እየገደበ ያለው?” ብላቹህ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ አገዛዙ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደሰማቹህትና ከግብጽና ከሱዳን ጋርም የተስማማው ወይም የተፈራረመው “ግድቡ ለኃይል ማመንጫ ብቻ የሚያገለግልና ከግድቡ ውኃ ጠብታ ውኃ እንኳ ለመስኖ አገልግሎት የማይነካ መሆኑን በፊርማ አረጋግጦ ተስማምቶ ነው ግድቡን እየገነባ ያለው!!!
“ይሄ ሁሉ ውዝግብ ታዲያ ምንድን ነው?” ያላቹህ እንደሆነ ውዝግቡ በውኃ አሞላል አለመግባባት የተፈጠረ ማለትም ውኃው ኃይል አመንጭቶ የሚለቀቅላቸው ቢሆንም “ለጊዜውም ቢሆን ውኃው በግድቡ መያዙ ጥቅማችንን ይነካልና ግድቡ በረጅም ጊዜ ቀስ ብሎ ጥቂት ጥቂት ውኃ እያስቀራቹህ ይሞላ!” በሚል እብሪት ያወረው ጥጋብ ነው እንጅ “ውኃው ከነአካቴው ይቀርብናል!” ብለው በመሥጋታቸው የተፈጠረ አለመግባባት አይደለም!!!
ስለሆነም አገዛዙ ዐፄ ምኒልክን “የዓባይን ውኃ ላለመገደብ ፈርመዋል፣ ለሱዳን መሬት ሰጥተዋል!” እያሉ ባልዋሉበት የሚያውሏቸውና ከዐፄ ምኒልክ በፊት ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ በጣሊያን አስወርረው ያስገነጠሉትን ሀገር ዐፄ ምኒልክ እንዳስገነጠሉት፣ ለ99 ዓመት ለፈረንሳይ በኮንትራት ተሰጥታ የነበረችውንና የኮንትራት ጊዜው ባለቀ ጊዜም ፈረንሳይ “ተረከቡኝ!” በምትልበት ጊዜ ሀገሪቱ በወቅቱ በነበረባት ከባድ የገንዘብ እጥረት ወይም የኢኮኖሚ መዳከም ምክንያት “ጅቡቲን ለማሥተዳደር ለጅቡቲ ሊበጀት የሚችል ገንዘብ የለንም ቀውስ ውስጥ እንገባለን!” በሚል ሥጋት በዐፄ ኃይለሥላሴ ውሳኔ በዚያው የቀረችውን ጅቡቲን ዐፄ ምኒልክ ለፈረንሳይ ሸጠው የሰጧት የሚያስመስሉት ለሱዳንና ግብጽ ባላቸው ባንዳነት ሀገራችን ወደፊት በዓባይ ወንዝ ላይ ለመስኖ ልማት የሚሆን ግድብ እንዳትሠራ ለማሰር፣ የሀገራችንን መሬት ለሱዳን ለማስረከብና…. በማሰብ ነው!!! በመሆኑም የሱሌይማን ደደፎ አስተሳሰብ የሁሉም የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት አስተሳሰብም እንጅ የሱሌይማን ደደፎ ብቻ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ሰውየው በዚህ የሀገር ክህደት ወንጀሉ እርምጃ ያልተወሰደበት ወይም ከሹመቱ ያልተሻረው!!! እርምጃ ይወሰድበታል ብላቹህም አትጠብቁ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
