በአዲስ አበባ የሚገኝ ስነ ጥበብ ትምህርት ቤት

Pከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 የዕድሜ ባለጸጋ በጣሊያን ወረራ ወቅት አርበኛ ነበርኩ ይላሉ from BBCVideo

ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 የዕድሜ ባለጸጋ በጣሊያን ወረራ ወቅት አርበኛ ነበርኩ ይላሉ

BBC 19 ሀምሌ 2020

“በኮሮናቫይረስ ላይ ኅብረተሰቡን እያሳመጽኩ ነው”፡ ትዕግስት ሲሳይ from

Play video ከየካቲት እስከ ሰኔ ድረሰ በረራ በመከልከሉ 1 ቢሊዮን ዶላር አጥተናል from BBCPlay video ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 የዕድሜ ባለጸጋ በጣሊያን ወረራ ወቅት አርበኛ ነበርኩ ይላሉ from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በኢትዮጵያ በአንድ ቀን በ704 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶ ከፍተኛው የህሙማን ቁጥር ተመዘገበ
  2. ፕሪሚየር ሊግን የተቀላቀለው የሊድስ ዩናይትድ ደጋፊዎች ክልከላዎችን ጥሰው አደባባይ ወጡ
  3. የአሜሪካው ፕሬዝዳናት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ዜጎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን እንዲያደርጉ አላዝም አሉ
  4. የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ታላላቅ አገራት የኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ተባብረው አልሰሩም ሲሉ ወቀሱ
  5. አሜሪካ በየዕለቱ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች መመዝገቧን ቀጥላለች
  6. የሆስፒታል ባለቤቱ ሀሰተኛ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶች በመስጠት በቁጥጥር ስር ዋለ
  7. የማላዊ ፕሬዝዳንት ህዝባቸውን ስለኮቪድ-19 ጾምና ፀሎት እንዲያደርግ ጠየቁ
  8. ቺሊ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የሚለዩ አነፍናፊ ውሻዎችን እያሰለጠነች ነው
  9. የአሜሪካ ኩባንያ ያመረተው የኮቪድ- 19 ክትባት የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ ደረሰ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 11:5911:59በኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛው የኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ተመዘገበቢቢሲ አማርኛBBCCopyright: BBCበኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ መገኘቱ በይፋ ከታወቀ ወዲህ እስካሁን በአንድ ቀን በተደረጉ ምርመራዎች ሁሉ ከተገኘው ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ተመዘገበ።ባለፉት 24 ሰዓታት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው 7334 ናሙናዎች ላይ በተደረገው ምርመራ ቫይረሱ በ704 ሰዎች ላይ ሲገኝ ይህም እስካሁን በአገሪቱ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከተገኘው እጅግ ከፍተኛው ነው።ቫይረሱ መገኘቱ ከተረጋገጠባቸው ሰዎች መካከል ከፍተኛው ወይም 551ዱ በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ የተገኙ መሆናቸው ተገልጿል።በተጨማሪም ከትግራይ 39፣ ከኦሮሚያ 30፣ ከጋምቤላ 26፣ ከአማራ 21፣ ከሲዳማ 11፣ ከድሬዳዋ 10 እና ከሌሎችም ክልሎች ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጡት በሽታውን የተመለከተ ያለፉት 24 ሰዓታት ሪፖርት ላይ እንዳመለከቱት አስከ ዛሬ በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 207 ሆኗል። ሪፖርቱ ጨምሮም 196 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን አመልክቶ አጠቃላይ በአገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አሃዝ 5137 ሲደርስ፤ ሦስት ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል ከእነሱም መካከል በሁለቱ ላይ ቫይረሱ የተገኘው አስከሬን ላይ በተደረገ ምርመራ ነው። እስከ ዛሬ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ለሞት የተዳረጉት ሰዎች አጠቃላይ ቁጥርም 170 ሆኗል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ እስካሁን ለ331 ሺህ 266 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ቫይረሱ በ10 ሺህ 207 ሰዎች ላይ የተገኘ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ አገግመዋል