Covid types

Getty ImagesCopyright: Getty Images

በዩኬ መዲና ለንደን የሚገኘው ኪንግስ ኮሌጅ ውስጥ የሚሠሩ ተመራማሪዎች ስድስት የኮቪድ-19 አይነቶችን መለየታቸውን ይፋ አደረጉ።

ጥናቱ የተሠራው በበሽታው የተያዙ ሰዎች የሚያሳዩትን ምልክቶች መነሻ በማድረግ ነው።

ስድስቱ የኮቪድ-19 አይነቶች በሽታው ምን ያህል የከፋ እንደሆነና ታማሚው ምን አይነት የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልገው ይጠቁማሉ ተብሏል።

እነዚህም

1.እንደ ጉንፋን ያለና ትኩሳት የሌለው፡- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ የጡንቻ ህመም፣ ሳል፣ የጉሮሮ መድረቅና የደረት ህመም ሲሆኑ ትኩሳት ግን የለውም።

2.እንደ ጉንፋን ያለና ትኩሳት ያለው:- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ ሳል፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ የድምፅ መዘጋት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ትኩሳትን ያካትታሉ።

3.ጋስትሮኢንቴንስታይናል:- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ የደረት ህመም ሲሆኑ ሳል ግን የለውም።

4.ጽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ድካም:- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ ተቅማጥና የደረት ህመም ሲሆኑ ሳል ግን የለውም።

5.ጽኑ ሁለተኛ ደረጃ ግራ መጋባት:- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የድምፅ መዘጋት፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ የደረት ህመም፣ ድካም፣ ግራ የመጋባት ስሜት እንዲሁም የጡንቻ ህመም ናቸው።

6.ጽኑ ሦስተኛ ደረጃ የሆድና የጉሮሮ ህመም፡- ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ ማሽተት ማቆም፣ የምግብ ፍልጎት መቀነስ፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ የድምፅ መዘጋት፣ የጉሮሮ መድረቅ፣ የደረት ህመም፣ ድካም፣ መወዛገብ፣ የጡንቻ ህመም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ተቅማጥ እና የሆድ ህመምን ያካትታሉ።