July 20, 2020
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/108485
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2020/07/0CB8CAE7_1_dwdownload-1.mp3
በትግራይ ሊደረግ የታቀደዉን ምርጫ ለማደናቀፍ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የኤርትራ መንግሥትና ሌሎች ሃይሎች በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ ነዉ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። በትግራይ ተወላጅ ባለሃብቶች እና አጠቃላይ የክልሉ ኤኮኖሚ ላይ አሻጥር እየተፈፀመ ነዉ። 1. 0CB8CAE7_1_dwdownload (1)
00:28 02:40 Pause
በትግራይ ሊደረግ የታቀደዉን ምርጫ ለማደናቀፍ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የኤርትራ መንግሥትና ሌሎች ሃይሎች በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ ነዉ ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ገለፁ። ም/ል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን በኩል ባስተላለፉት መልክት በተለይም በክልሉ ድንበር እና አዋሳኝ አካባቢዎች ምርጫዉን ለማደናቀፍ የታቀዱ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነዉ ብለዋል። ከዚህ ዉጭ በትግራዊ ተወላጅ ባለሃብቶች ላይ እና አጠቃላይ የክልሉ ኤኮኖሚ አሻጥር እየተፈፀመ ነዉ ያሉት ምክትል መስተዳድሩ መንገድ የመዝጋት እንቅስቃሴን ጨምሮ የትምህርት ተቋማትን ስራ የማደናቀፍ ተግባር እየተከወነ ነዉ ሲሉ ደብረፂዮን ከሰዋል።
ሚሊዮን ሃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ \
DW