July 24, 2020
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/108684
ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓም
emails: batelibido7@gmail.com Or menedo7@gmail.com
Phone (720)507-0976
አትዮጵያ: ደቡብ ክልል : ጉራጌ ዞን: መስቃን እና ማረቆ ወረዳዎች ወንጀሉ የተፈጸመበት ጊዜ: ከመስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም – ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓም ድረስ
ኤግዚቢት1: የኢዮጵያ እና የጉራጌ ዞን ካርታዎች በከንቱ ስለፈሰሰው የማረቆ ብሔረሰብ ደም ዝም አንበል !

መግቢያ
ባሳለፍነው ሰኔ ወር በታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሕልፈት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ስለ ተከሰተው የንጹሃን ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ንብረት ውድመት በመቃወም በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውን መንግስት የሕግ የበላይነትን እንዲያከብር እየጠየቁ ይገኛሉ ። የወገን ጉዳት የራስ ነውና ስለ ንጹሐን ዜጎች ደም መፍሰስ ተቆርቋሪ ሆነው ኢትዮጵያውያን እንዲህ በአንድነት መቆማቸው የሚጠበቅ እንጂ ትንግርት ነገር አይደለም :: ይህ እውነታ የሚያስተላልፍልን ጠጣር መልዕክት ቢኖር ስለተገፉት ግድ እንዲለን መመዘኛው እግዚአብሔር እኩል አርጎ የፈጠረውን ‘ሰብአዊነት’ ማክበር እንጂ ሌላ አለመሆኑን ነው :: ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ እንደ አለመታደል ሆኖ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታም ሲገደሉ የራሴ ከሚሉት ብሄረሰብ ፣ሀይማኖት ወይም የፖለቲካ ድርጅት አባል ውጪ ስለሌሎች ተቆርቆሮ የሚሟገትላቸውን ሰው ማግኘት ጭንቅ ነው :: ከመስከረም ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ሰኔ 4 2012 ዓም ድረስ ባለው ጊዜ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በማረቆ ብሔረሰብ ላይ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ያ ሁሉ ጥቃት ሲፈጸምባቸው አንድም የሚጮህላቸው ወገን አለመገኘቱ እጅግ ያማል ። እስካሁን መረጃው በደረሰን መሰረት ከመስከረም ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ሰኔ 4 2012 ዓም ድረስ ባለው ጊዜ በማረቆ ብሔረሰብ ላይ የደረሰው ጥቃት እንደሚከተለው በአጭሩ ይቀርባል ።
የአኬልዳማው ጅማሬ
እንደ አትዮዽያ አቆጣጠር መስከረም 3 እና በኅዳር 5 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመስቃንና ማረቆ ወረዳዎች በተፈጠረው የእርስ በርስ ግጭት ከሁለቱም ብሄረሰቦች ለዘመናት ያፈሩት ንብረት በቅጽበት እንደ ወደመባቸውና ወደ 40 ሺሕ የሚጠጉ /እናቶች አባቶች ሕጻናት ወጣቶች/ ከተወለዱበት ቄዬ መፈናቀላቸውና ከ100 በላይ የሚጠጉ ወገኖቻኖቻችን ክቡር ሕይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ማጣታቸው የሚታወስ ነው ። በዛኔው ግጭት ከነ- ነፍሳቸው ተቃጠለው ክቡር ሕይወታቸው አልፉዋል። የ85 ዓመት አዛውንት ተገለው ሬሳቸው ተጎትቱዋል። የኦርቶዶክስ አማኝ ተገሎ ከስንት ቀን ፍለጋ በኋላ በድብቅ ከተቀበረበት የእስላሞች መቃብር ተገኝቶ ቤተሰቦቹ ከመቃብር አውጥተው በኦርቶዶክስ መቃብር ቀብረውታል። ከ15 በላይ ሴቶች በተፈናቃዮች ጣቢያ ልጅ እንደወለዱ ሰምተናል ። ሽማግሌዎች ሳይቀሩ መኖሪያ ቤታቸው በነበሩበት ባስለቃሽ ጭስ እንዲዘረሩ ተደርገው በልዩ ኃይል ወህኒ ውስጥ ተወርውረው ከ2ዓመት በላይ ያለ ክስና ያለ ፍርድ በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ ። ቤተ ሰቦቤተሰቦቻቸው ሁሉ በስደት ተበታትነዋል። የ75 ዓመት የደከሙ አሮጊት ገበያ ሲሄዱ ሆነ ተብሎ በጋሪ ተጭተው ሕይወታቸው አልፉዋል ። የ16 ዓመት ኮረዳ ሕጻን ልጅ ተሸክማ ውሃ እየቀዳች በጥይት ተመታ ሕይወትዋ አልፉዋል ። በርካታ ወጣቶች ተማሪዎች ጭምር በመከላከያ በጥይት በድንገት ተመተው ተገለዋል ። የ5 ዓመት ህጻን ሳይቀር ቆሼ ከተማ ውስጥ በመከላከያ ጥይት ተገሉዋል ።
ይኸው መፍሔ ያልትበጀለት ግጭት ባሳለፍነው ግንቦት ወር 2012 ዓም ዳግም ተቀስቅሶ ከመስቃንም ከማረቆም የሆኑ ወገኖቻችን ሃብት ንብረታቸው እየተቃለጠለና እየወደመባቸው ከትውልድ ሰፈራቸው መፈናቀላቸው ሳይበቃ ከ22 በላይ የሚጠጉ ምስኪን ወገኖቻችን በጥይት ብቻ ሳይሆን በጎራዴ እየተሰየፉ በአሰቃቂ ሁኔታ ክቡር ሕይወታቸውን አጥተዋል ። እንሴኖ ከተማ ውስጥ አዛውንት በቤታቸው በነበሩበት ታርደዋል። የ20 ዓመት ወጣት ቡታጅራ ተገድሎ ሬሳው እንሴኖ ቄራ ተወርውሩዋል። ከሰሜን ዲዳ ቀበሌ አካባቢ ወደ እንሴኖ ገበያ ሲመጡ ሁለት ገበሬዎች በጦር ተውግተው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተዋል። ባቲ ሌጃኖ ቀበሌ ውስጥ አስታራቂ ያገር ሽማናግሌ በመኖሪያ ቤታቸው ባሉበት በጠራራ ጸሐይ በሚስታቸው ፊት ታርደዋል; ያም ሳይበቃ አንደኛው የልጅ ልጃቸው የገዛ ወንድሙ የሆነውን ሌላኛውን የልጅ ልጃቸውን በተመሳሳይ ቀን አዛው ሰፈር ገድሎታል። የአእምሮ ህመምተኛ የሆነው ወጣት በቲ ፉጦ ቀበሌ ውስጥ እቤቱ በተቀመጠበት ተገሉዋል ።
ታዲያ ድርጊቱ የተፈጸመው ሶሪያ፤ ባግዳድ ወይም ሌላ አገር በጭራሽ አይደለም ። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር በ150ኪሜ ርቀት : በቡታጅራና በዝዋይ ከተሞች መሃል 23 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ አሁንም እየተፈጸመ ያለ አኬልዳማዊ ክስተት ነው! ኸረ ለመሆኑ ማነው የሚፈጽመው? ማንስ ላይ ? መልሱ አይሲስ፣ ኣልቃይዳ ፣አልሻባብ ወይም ሌላ የውጭ ወራሪ በፍጹም አይደለም ! እህስ ማነው ብትሉ ? “የገደለው ባልሽ ..የሞተው ወንድምሽ..ሐዘንሽ ቅጥ አጣ..ከቤትሽ አልወጣ !!” ዓይነት ነው ነገሩ!
ይህ እጅግ አሰቃቂ ወንጀል የማሕበራዊ ሚዲያ ወሬ ወይም የፌስ ቡክ “FAKE NEWS” ፈጽሞ አይደለም። እውነተኛና የተፈጸመ ነው። ነገሩ ፀሐይ የሞቀው ቢሆንም አገር ግን ትኩረት ሰጥቶ ያላወቀው ያደባባይ ሚስጥር አረ ስንቱ? አሁንም ውጥረቱ በአካባቢው ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ። ምንም እንኳ በየጊዜው የሚከሰቱትን በነዚህ ጊዜያት ተከሰቱትን ወይም የሚከሰቱትን ግጭቶች የመንግስት ወይም የዓለም አቀፍ የዜና ወታሮች የሚጠበቅባቸውን ያህል ወቅቱን ጠብቀው በዝርዝር ባይዘግቡትም! ግጭቱ ከተከሰተበት ከመስከረም 3 ዓም ጀምሮ እስክ አለፈው ግንቦት ወር 2012 ዓም ድረስ ያለውን ግጭት በተለያዩ ሚዲያዎች በመጠኑም ቢሆን በቅቱ ስለተዘገበ ‘Meskan and Marko Conflict’ በማለት ከዩቱብ ማግኘት ይቻላል ። በሰው ልጆች እኩልነት የሚያምን ማንም አካል ወይም ኢትዮዽያዊ ዜጋ እነዚህን መረጃዎች እንደመነሻ በመጠቀም ከጥቃቱ ሰለባዎች ወይም ከገለልተኛ ወገን ጠይቆ ወይም መርምሮ መረጃውን በማጣራት ሙሉ እውነቱ ላይ ሊደርስበት ይችላል ።

ተጠያቂዎች እነ ማናቸው?
ትልቁ ጥያቄ እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የተሞላበት አሰቃቂ ወንጀል በሰው ልጆች ላይ አስፈጻሚውስ ማነው ? የሚለው ሲሆን መልሱ ሁለቱም ወገን ተጎጂዎች በተደጋጋሚ በሚዲያ ሲናገሩ እንደተደመጠው ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፌደራል ድረስ በየተዋረዱ ሕዝቡን እንወክላለን ብለው የቀመጡ አመራሮች መሆናቸውን ነው የሚነግረን ። ይህን ስሞታ እውነት መሆኑን የሚያስረዳን ለ18 ዓመታት የተጠየቀ የማረቆን ሕዝብ አንድ ጥያቄ ሕገ-መንግስት የሚፈቅደው ከሆነ በቁርጠኝነት መመለስ የማይፈቅድም ከሆን የማይሆንበትን አግባብ ለሕዝብ ማስረዳት እየተቻለ አብረው ለዘመናት በሰላም የኖሩትን ወንድማማች ሕዝቦችን በማገጋጨት ማን ሊያተርፍ ይችላል? በተለይም ላለፉት 2 ዓመታት ግጭቱ ተባብሶ የቀጠለ ቢሆንም መንግስት መፍታት ለምን እንደተሳነው ግልጽ አይደለም ። በሰው ልጆች ደም የሚነግዱ የወንጀሉ ፊታውራሪዎች በሕግ አለመጠየቃቸው ሳያንስ ይባስ ብሎ ካለ ከልካይ የጥፋት ተልዕኮአቸውን በከፋ ሁኔታ እያቀነባበሩት ይገኛሉ ። ሌላው ቀርቶ ለተጎዱት ማረቆዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንኳ ያላቀረቡት የደቡብ ባለ ስልጣናት የዘመናት የማረቆን ሕዝብ ጥያቄ ቆዩ ጠብቁ ብሎ ከ 18 ዓመት በላይ ከማስጠበቅና ግጭት ሲከሰት አስከሬን ሰብሳቢ ፖሊስ ከመላክ ያለፈ ስራ እየሰሩ አለመሆኑ በታሪክም በሕግም የሚጠየቁበት ጊዜ እሩቅ እንዳይሆን የገፈቱ ቀማሽ የሆነው የማረቆ ሕዝብ ይጠብቃል ። እጅግ ግራ የሚያጋባው መከላከያ ሰራዊት ሰፍሮ ባለበት አካባቢ በጠራራ ፀሀይ ያለወንጀላቸው እየተገደሉ ያሉት የማረቆ ብሔረሰብ ተወላጆች ኢትዮጵያውንና ከሁሉም በላይ የሰው ልጆች ሆነው ሳለ መንግስት ባለበት ሀገር ለዚህ አስከፊ እልቂት ትኩረት መነፈጉ እንደ ኢትዮጵያዊ እጅግ የሚያሳዝን ነው ::
ማጠቃለያ
የደቡብ ብልጽግና አመራሮች ለጠሚ ዶ/ር አብይ በሐሰት መረጃ ማሳሳታቸውን በአስቸኳይ ያቁሙ !
ጠሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለደቡብ ክልል ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት እየሞከሩት ያደረጉት ጥረት እስካሁን ያልተሳካላቸው ለውሳኔ የሚመሰረቱበትን መረጃ ወይም ማስረጃ የሚያገኙት ከሕዝቡ በቀጥታ ወይም ክገለልተኛ ወገኖች ሳይሆን ችግሩን ከፈጠሩት አመራሮች በሚሰጣቸው ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ላይ ተመርኩዘው በመሆኑ ነው ። በለውጡ ዘመንም በዋናነት የሕዋሃት አጀንዳ አስፈጻሚ የሆኑት የደቡብ ክልል አመራሮች በራሳቸው የዞን-ክልል የመሆን ጥያቄ ተጠምደው ለዜጎች ሕይወት ደንታ ቢስነታቸውን አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ። ለዚህ ማሳያው በተግባር ሳይደመሩ ለፖለቲካ ፍጆታና ለስልታዊ ጠቀሜታ ሲባል ብቻ ተደምረናል እያሉ የለውጡን አመራር እስከዛሬ ድረስ ማታለል በመቻላቸው የሕዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሕዝብን እያጠቁና አገር እያተራመሱ አንዳቸውም በሕግ አግባብ አለመጠየቃቸው ነው። ።:: የደቡብ ሚዲያዎችም አሁንም የሚያወሩት ነገሮችን ገልብጠው ነው ። ምክንያቱም ለውጡ የደቡብን አመራር ካላይ እስከታች ስላልዳሰሰው ። የመስከረም ሶስቱን ወንጀለኞ ለሕግ ቢያቀርቡና የሕዝብን ጥያቄ ሳይንቁ ቢመልሱ ኖሮ ግጭቱ ሕዳር 4, 2011 ዓ.ም ዳግመኛ ተቀስቅሶ ያ ሁሉ ሕይወት ባልተቀጠፈ ንብረትም ባልወደመ ነበር :: በደቡብ ክልል የማረቆ ብሔረሰብን የዘር ማጥፋት በማነቀባበር ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፌደራል ድረስ በጥቅም ሰንሰለት የተያያዘው ቡድን በተለይም የጉራጌ ዞን አመራር ከ18 አመት በላይ ያስቆጠረውን የማረቆን ብሔረሰብ ህገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ ከመፍታትና ግጭቱን ከማርገብ ይልቅ ይበልጥ እንዲባባስና እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል ::
አሁንም ቢሆን ቀጠናውን የሚዘውሩና በሕዝብ ጀርባ ላይ እየሸረቡ ከፊት ለፊት ግን ራሳቸውን የለውጡ አራማጅ በማስመሰል ለጠ ሚ/ሩ የተሳሳተ መረጃ የሚያቀብሉ የማረቆን ብሔረሰብ የዘር ማጥፋት ያቀነባበሩ በዋናነት የሚከተሉት ናቸው :
- አቶ እርስቱ ይርዳው የክልሉ ም/ ር/መስተዳድር /የዶር ካ/ሱ ኢላላ ግርፍ ካድሬ
- አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ አሁን የወጣቶችና ስፖርት /ደቡብ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረ /የዶር ካ/ሱ ኢላላ ግርፍ ካድሬ
- አቶ ሁሴን ዳሪ የሕዝብ ተወካዮች ምቤት አባል//የዶር ካ/ሱ ኢላላ ግርፍ ካድሬ
- አቶ መሃመድ ጀማል የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ/ የአቶ እርስቱ ይርዳው ግርፍ ካድሬ
- አቶ ሚፍታ ሸምሱ/ወንጀሉን በግንባር የሚመራ ከአብዲ ኢሌ ጋር ልምድ ያካበተ ያካባቢው ከፍተኛ ካድሬ
- አቶ ዘይኑ ጀማል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበረ/ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ
- አቶ አህመዲን ደድገባ /የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ/የአቶ እርስቱ ይርዳው ግርፍ ካድሬ
- ኮማንደር ጉራማይሌ /የክልሉ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ
በመሆኑም መፍትሄው በዘገየ ቁጥር ችግሩ እጅግ እየተወሳሰበና ከዚህ የከፋ እልቂትም እንደሚያስከትል ለመረዳት ነቢይ መሆንን አይጠይቅም :: የማረቆ ብሔረሰብ ለኢትዮጵያውያንና ለመንግስት የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ :: በመሆኑም ለማረቆ ብሄረሰቦች ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ የሚያስፈልገው ስልጣንን ማራዘሚያ የካድሬዎች የሀሰት ጥገናዊ ምላሽ ሳይሆን ቆራጥ ህገ-መንግስታዊ ምላሽ ነው :: ወንጀለኞች በአፋጣኝ ለሕግ ሊቀርቡና የተጎዱ ወገኖች ሊካሱ ይገባል። የኢትዮጵያ መንግስት ለማረቆ ብሔረሰብ ሕገመንግስታዊ ምላስ በአፋጣኝ ባይሰጥ ከዚህ በሗላ ለሚከሰተው ማንኛውም ጉዳትና የህዝቦች እልቂት ሀላፊነት የሚወስዱት ወንጀሉን በቀጥታ ፈጻሚዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር መንግስት ከታሪክ ተወቃሽነት አልፎ ከህግ ተጠያቂነት አያመልጥም :: የመስቃንና ማረቆ ወንድማማች ህዝቦች ደም እግዚአብሔር ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ታሪክ አንድ ቀን ሳይፋረዱት እንዲሁ ከንቱ ሆኖ አይቀርም ።
አባሪ1: ባለፉት 2 ዓመታት ስለ መስቃንና ማረቆ ግጭት በበርካታ የዜና አውታሮች ከተዘገቡት ውስጥ በከፊል በሚከተሉት ቪዲዮዎች ይገኛሉ :
1. Arts TV World July 24 2020: https://youtu.be/IId1objkaSs
2. Ethio360 Media, June 27, 2020 : https://youtu.be/ySAvDsSeT7c
3. Ethio360 Media, June 1 2020: https://youtu.be/cN7B78_aKd8
4. OMN:Feb5,2020:https://www.facebook.com/OromiaMedia/videos/2 480835805566304/?sfnsn=mo&d=n&vh=e
5. STV News, Oct 3, 2019:https://youtu.be/u5CGWye9FMk
6. Esat News, July 17, 2019: https://youtu.be/ZG4O1QyJ4SU
7. VOA News, April 5, 2019: https://youtu.be/RbB3006oAZ0
8. EBC News, Dec 3, 2018:https://youtu.be/7qD1o-Oqtnw
9. Mulu Tube, Dec 2, 2018: https://youtu.be/YB-Y6-vZaQA
10. Fana News, Nove 26 2018: https://youtu.be/SWHTAv5rnL0
11. ESAT News, Nov 20, 2018: https://youtu.be/iAuXolmUbTg
12. Hibir Radio Nov 20;2018: https://youtu.be/9Bk2_CCh4rs
13. EBC News, Nov 18, 2018: https://youtu.be/wQDgt0mI3gM
14. DW News, Nov 18, 2018: https://youtu.be/bwjMOzqJRTw
15. Zehabesha Nov 16,2018: https://youtu.be/0JrwDnM4ZGg
16. BBN News, Sept 21, 2018: https://youtu.be/MIw6pRDRv4g
17. ETV News, Sep 20, 2018: https://youtu.be/6n61cv_7KU0
አባሪ 2: በመስቃና ማረቆ ግጭት ባለፉት ከመስከረም 3 ቀን 2011 ዓም – ሰኔ 4 ቀን 2012 ዓም ድረስ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት የማረቆ ብሔረሰብ ሟቾች ስም ዝርዝር በከፊል