July 27, 2020

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/108755

ሰበር ዜና °°° ጃል ዳዉድ ኢብሳ ከስልጣን እንዲወርዱ የግንባሩ ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነበት ምክንያቶች ፦ 1ኛ. ከማዕከላዊ ኮሚቴዉ እዉቅና ዉጭ ከህውሃት/ወያኔ ጋር አጋርነት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸዉ ታሪካዊ ስህተት በመሆኑ። 2ኛ. በአንድ በኩል ሰላማዊ ይትግል ስልትን በሌላ በኩል ደግሞ የትጥቅ ትግልን እንዳማራጭ ወስደዉ መንቀሳቀሳቸዉ እና ጫካ ላለዉ ኦነግ ሰራዊት አሁንም አመራር መስጠት መቀጠላቸዉ ትክክል አለመሆኑ። 3ኛ. አባ ቶርቤ በመባል የሚታወቅ እና በከተሞች የጸጥታ ሃይሎችን፣ የመንግስት አመራሮችን፣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያን የሚፈጽመዉን የሽብር ቡድን አሰልጥነዉ እና አስታጥቀዉ የሚያሰማሩት አመራሩ መሆናቸዉ በመረጋገጡ እና ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ተግሳጽ ቢሰጣቸዉም መታራም ባለመቻላዉ ከስልጣን እንዲወርዱ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ዛሬ ሃምሌ 20/2012 ዓ.ም ወስኗል፡፡ መሀል ሚዲያ