አቶ ቀጀላ የኦነግ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ10 ቀናት አንስቶ በመንግስት የጸጥታ አካላት ሲጠበቁ ስለነበር አስቀድሞም እንደማይሳተፉ የተገመተ በመሆኑ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን ገልጸዋል። ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ «ከእውነት የራቀ» ሲሉ አስተባብለዋል።

ዳዉድ ኢብሳ ተነስተዋል መባሉን ኦነግ አስተባበለ | ኢትዮጵያ | DW | 27.07.2020
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ያለ ግንባሩ ሊቀመንበር ያካሄደው ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁን አስታወቀ ።፡ስብሰባው ከሳምንት በፊት በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የአባላቱ መታሰርና የግንባሩ የወደ ፊት ስራዎች ላይ ለመምከር የተጠራ መሆኑን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። አቶ ቀጀላ የኦነግ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ10 ቀናት አንስቶ በመንግስት የፀጥታ አካላት ሲጠበቁ ስለነበር አስቀድሞም እንደማይሳተፉ የተገመተ በመሆኑ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን ገልጸዋል። ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ «ከእውነት የራቀ» ሲሉ አስተባብለዋል።አቶ ቀጄላ አሁን የአመራር ለውጥ ለማድረግ ፓርቲው ምንም እቅድ እንደሌለውም ገልጸዋል።አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ ማየት አልቻልንም ያሉት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስልካቸውም ከባለፈው አርብ ጀምሮ መዘጋቱን አረጋግጠዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ