July 28, 2020

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/108819

እንዴት እዚህ ደረስን

አሁን ያለንበት አስተሳሰብ ከእውነት ጋር ለመገናኘቱ ሁላችንም ወደራሳችን እንመልከትና እናስብ፡፡ ከዛሬ 30 ዓመት በፊት አሁን ያለው እጅግ የከፋ የዘረኝነትና የጥላቻ አስተሳሰብ አልነበረንም፡፡ አባቶቻችንም አያቶቻችንም ይሄንን አልኖሩትም፡፡ የቀደሙ ሥርዓቶች እየተባለ እንደሚነገረንም የቀደሙ ሥርዓቶች የፈጠሩብን ችግር አደለም አሁን ያለንበት፡፡ ይልቁንስ አሁን ያለንበት የቀደሙ ሥርዓቶች፣ የነፍጠኛው ሥርዓት ሌላም ሌላም እያለ ሲመርዘን የኖረው አሁንም ያለው ሥርዓት ነው የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ ሲዘራብን ኖሮ ዛሬ ይሄው ውጤቱን እያጨድን ያለንው፡፡ አሳዛኙ ነገር በነገሮች ሁሉ ታውረን ለጠላቶቻችን መሣሪያ ሆነን ወዳጆቻችንን ወዳጆች ባይሆኑ እንኳን ምንም የማይመለከታቸው እንደኛው ሚስኪኖችን አረመኔያዊ በሆነ መልኩ ለመግደል አረመኔ የሆነ አስተሳሰብን አዳብረናል፡፡ እሰከ ገዛ ቤተሰባችን ዘልቆ ገብቷል፡፡ ዛሬ ብዙ የሚባል ቤተሰብ በደህናው ቀን በሠላም ትዳር መስረተው ልጅ ወልደው ስንት ከኖሮ በኋላ እነዛው በራሳቸው ተዋደው የተጋቡ ወላጆች በቤት ውስጥ የዘርንነትና ጥላቻው ልክፍት አጥቅቷቸው ቤተሰብ ከመበተናቸውም በላይ ለልጆቻቸውም የከፋ ነገርን እያኖሩ ነው፡፡ ጥላቻው እንዴት እያደገ እንደመጣና ሲሰራ የኖረውን ሴራ ሁሉ ባለማስተዋል ብዙ ቀሪዎችም አደጋ ላይ ናቸው፡፡ የሚሰሙት የጠላቶቻቸውን ሴራ እንጂ እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን አእምሮና ሕሊና አልሆነም፡፡ በአጠቃላይ ለጠላቶቻችን  ሴራ ባሪያ ሆነን ለወዳጆቻችን፣ ሊሚስኪኖችና አንዳች ላልበደሉን ከዚህም አልፈን ለገዛ ቤተሰባችን ጭራቅ እየሆንን ነው፡፡  በደቡብ አፍሪካ የነጮች አፓርታይድ ሥርዓት ዛሬም ድረስ ጥቁሮቹ ጥላቻቸውና አረመኔያዊ ድርጊታቸው የሚታየው በሚስኪን ሌሎች ጥቁሮች ላይ ነው፡፡ በአካልም በአስተሳሰብም ባሪያ ያደረጓቸው ነጮች ዛሬም ጌቶቻቸው ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ያለፉት 30 ዓመት ሲደረግ የኖረው ይሄን የሚመስል ትውልድን ወደ ምንም ወደ ማያስብ ለጠላቶቹ የሚገዛ በጥላቻና ዘረኝነት አእምሮው ፍፁም እንዲመክን ነው፡፡ አሁን በዛ ደረጃ ብዙ ያሳደጉት የማህበረሰብ ክፍል ስላላቸው እንደልብ ይጋልቡታል፡፡ በዚህ 30 ዓመት ያልተዘራ የጥላቻና ዘረኝነት ዘር የለም፡፡ በአንዳንድ ማህበረስብ ዘንድ ግን ከሌሎች ሁሉ ይከፋል፡፡ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ማህበረሰብ የተሰራው ሴራ በአሳዛኝ ሁኔታ ብዙ የሚባል ዛሬ በተለይ በወጣትነትና አዋቂም ሆኖ በምሁረንት ያለ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ የዚህ የጥላቻና ዘረኝነት ልክፍት ጎድቶታል፡፡ እርግጥ ነው ወጣቱ የተነገረው ነው፡፡ ምሁሩ ግን ሆን ብሎ በራሱ በፈጠረው ያመጣው ነው፡፡  ምሁርና ቀለም ቆጠርን የሚሉ የዚሁ ማህበረሰብ ተወላጆች ወነኛ የዚሁ የዘርና ጥላቻ አስተሳሰብ አሰራጮች ናቸው፡፡ ኧረ ተው አባቶቻችሁና አያቶቻችሁ የማያውቁትን የባርነት አስተሳሰብ በትውልዱ አትጫኑ ቢባሉም ጭራሽ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልልቅ ዝናና ወሳኝ ሚና የነበራቸውን ከማህበረሰቡ የወጡ የቀድሞ አባቶችና አያቶችን እንደ ጠላት በመስበክ ለትውልዱ የሚሆን አንድም ምልክት እንዳይኖረው አደረጉት፡፡ ሌሎች ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም የኦሮሞን ማህበረሰብ አጅግ በሚያዋርድ ሁኔታ እንዲህ ነበርክ እንዲህ ነበርክ እያሉ ያልነበረ ታሪክ ጻፉለት፡፡ ደጋግመውም ሰበኩት፡፡ ተበድለህ ተጨቁነህ ይሉታል፡፡ ማን ነበር በዳዩ የሚለውን እንዳያነሳ ታሪካዊ ጠላት አድርገው ነፍጠኛ(አማራ) የሚል ቃል ሰጡት፡፡ በአጠቃላይ በአልነበረ ትርክት ኢትዮጵያን ሲዖል፣ ከድሮ ጀምሮ የሚያውቀውን ነፍጠኛ (አማራ) ጭራቅ አድርገው ሳሉለት፡፡ አሁን እንደፈለጋቸው ይዘውሩታል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡

ለመሆኑ ግን ኦሮሞ ነኝ የሚለው የዛሬው ትውልድ ማን ነው? ራሱን ከየት የመጣ አድርጎ ያያል?የኦሮሞ ምሁረስ የሚባሉት እንዴት ነው ነገሮችን እንዲህ እስኪጠፋቸው የሳቱት፡፡ ብዙ መርዘኛ መጻህፍት ተጽፈዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙዎች ታሪክ እያሉ ለእኔም የኦሮሞ ሕዝብ እንዲህ ነው የተደረገው በሚል የላኩልኝ አሉ፡፡ አዝናለሁ፡፡ አንዳንዶቹ በእርግጥም ምሁራ ናቸው፡፡ ጽሁፎቹን ለማየት ሞከርኩ፡፡ እንግዲህ ምሁር ነኝ የሚለው እነዚህን ጽሁፎች ከተቀበለ ብዙም በትፍምርት ያልገፋውማ እውነት ናቸው ብሎ የሚነግሩትን፣ የሚያነባቸውንስ ቢያምን ለምን ማለት አልችልም፡፡ በምሁራን ዘንድ አንድ ጽሁፍ ሲወጣ የራሱ መስፈርት አለው፡፡ እውነትነቱን የሚያረጋግጥ ሌሎች ገለልተኛ የሆኑ ምሁራን እንብበውና ከሌሎች ከሚያውቋቸው የቀደሙ ጽሑፎች አመሳክረው ትክክለኝነቱ ከተመሰከረለት ብቻ ነው፡፡ ዛሬ በዋናነት በኦሮሞ የመርዘኛ ትርክት ሕዝቡን እየመረዙ ያሉ ኦሮሞ ነን የሚሉ ምሁር ነን የሚሉን በአብዛኞቹ ለመመረቂያ የሚሆን እንኳን እንዲህ ያለ በእውነት ላይ የተመሰረተ ሌሎች የመሰከሩላቸው ጽሑፍ ያላቻ አደሉም፡፡ እነ ሕዝቅዬል ገቢሳንና ጸጋዬ አራርሳን ማየት ይቻላል፡፡ እነጀዋርን እንኳን አልፈርድባቸውም፡፡ አንዳንዶች ምሁር ነን የሚሉ ደግሞ በምሁራን መጽሄት የሚያሳትሙትን የግድ ከእውነት መራቅ ስለማይችሉ እውነቱን ይጽፋሉ ሌላ ቦጻ ግን ሄደው ራሳቸው ያሳተሙትን እውነት ሳይሆን ከራሳቸው ፈጥረው ለጥላቻና ዘረኝነት የሚሆናቸውን ይሰብካሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ፕሮፌሰር ሐሰን የመሳሰሉትን እናገኛለን፡፡

እኔና ጓደኞቼ

ዛሬ ላይ የኦሮሞ ወጣት ትውልድና ምሁር ነን የሚሉት ብዙዎች ሁራን የተረጋገጡ ታሪካዊ ጭብጦችን ሳይሆን የተሞሉት በእነደነ ተስፋዬ ገ/አብና ሌሎች በሥም የበረከቱ በቅርብ ጊዜ እንደ አሸን የፈሉ ልብወለዳውያን ናቸው፡፡ ሐጫሉ በኦኤም ኤን ቀርቦ ከመጽሐፍ ያነበብኩት እያለ ስለሚኒሊክ ፈረስ ሳይቀር ሲነግረን የነበረው እንዲሁ በሐሰት ከተጻፈና በሕዝብ ላይ መርዝ ለመርጨት ከተዘጋጀ ጽሁረ በእርግጥም ያነበበው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡አንድ አብሮ አደጌም  ከምርም እስካሁንም እንደልባችን የምንወቃቀስ ጓደኛዬም እንዲሁ ሌላ ጽሁፍ ልኮልኝ አንበብኩ፡፡ ይሄ ጓደኛዬ በዚህ ያህል ልከፍት ይያዛል የሚል እምነት አልነበረኝም፡፡ ሆኖም ዘመኑ ነውና ምንም ማርግ አይቻልም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ምሁርና እስከ ሶስተኛ ዲግሪውን የሰራ ነው፡፡ በስነ ልቦና ደግሞ በብዙ ነገር እንገናኛለን፡፡ አብሮ አደግ ከመሆናቸውን አንጻርም ልንካካዳ የማንችላቸው የፈጠጠ እውነቶች ስላሉ ቢያንስ እኔ ጋር ስናወራ እንግባባለን፡፡ ከዛም በላይ በጋራ የሚያሳስበን የኢትዮጵያ አንዳንድ ሌሎች ሰዎች በውል የማይረዱትም ጉዳዮች አሉ፡፡ አንድ ነገር ግን እሱም ቢሆን ጠላት ከዘራበት የኦሮሞነት ዘር ለመዳን አልቻለም፡፡ እርግጥ ነው አንዳንዴ በጣም ስንወያይ ለእሱም ግር የሚለው ነገር አለ፡፡ የኖረበትንም የቀድሞውን ጊዜ ሲያስብ፡፡

ሌሎች ደግሞ አሉ በዚህ በዘርና ጥላቸው ልክፍት የተያዙ ሳይመስለኝና ምንም አስቤያቸውም ሳላውቅ በቅርብ ጊዜ ማንነታቸውን ያወጡና ያስደነገጡኝ፡፡ በእውነት ነው የምላችሁ በእነዚህኞቹ ደንግጬያለሁ፡፡ አውቃለሁ ከኦሮሞ ቤተሰብ እንደተወለዱ፡፡ ግን ከነበረን ቅርርቦሽ አንጻር ስለራሴው ጭምር እንዲህ ያስባሉ ብዬ ጭራሽ ያልገመትኩትን አሁን ነገሮች ሁሉ የተሳኩ ሲመስላቸው ገልጠውታል፡፡ ይሄን ያወቅሁ ሰሞን ለተወሰነ ቀን ብዙ ነገር ወደ ሐሳቤ መጣ፡፡ በአጠቃላይ ግን የሰው ልጅ እንኳንስ ከልጅነት ጀምሮ ሲሰበክ የኖረው፣ በፊት መልካም ተነግሮት እንኳን ቢሆን ቆይቶ ለክፉ ሐሳብ ከተጋለጠና ከተሞላ የሚገዛው የኋለኛውና ክፉው እንደሆነ ታዘብኩ፡፡  አሁን የምገልፃቸው ከላይ ከጠቀስኩት ጓደኛዬ የሚለዩት ስለእኔ ክፉ ማሰባቸው ጭምር ነው፡፡ ከላይ የገለጽኩትና አብሮ አደጌ እርግጥ ነው ምን እንደሚያሰብ ለማወቅ ይከብዳል ሆኖም በዛ ደረጃ ለማሰብ አቅም ያለው አይመስለኝም፡፡ ቤተሰብ ጭምር ይተዋወቃልና፡፡ እነዚህ ለዘመናት ያልገመትኳቸው ጓደኞቼ ግን ከጊዜ በኋላ የተዋወቅን ነን፡፡ እርግጥ ነው የነበረን ቅርርቦሽ በእኔ ግምት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ አንዳንዶቹም (ብዙዎቹ ብል ይሻላል) ብዙ መልካም ነገሮችን የሰራን በብዙ ነገር የተደጋገፍንን፡፡ ለአንዳንዶቹ ግን አጋጣሚ ሊሆን ይችላል እኔ በብዙ የዋልኩላቸው ናቸው፡፡ ሰው በሕይወት ለመኖርና አለመኖር እግዚአብሔር ነው የሚወስነው፡፡ ሆኖም ምክነያት ሰውን ያዘጋጃል፡፡ ከእነዚህ ከምላችሁ አንዱ እንደውም እኔ በዚህ ደረጃ ምክነያት የሆንኩለት እንደሆነ ከረጅም ጊዜ መለያየት በኋላ በአንድ ወቅት ዋልክልኝ ያለውን አንስታውሶ ሲነግረኝ እኔ ማድረግ የሚገባኝ በመሆኑ ብዙም ትኩረት ባልሰጠውም ለእሱ ትልቅ ነገር እንደነበር ነግሮኛል፡፡ እርግጥም ነው ለሰው ሕይወት መትረፍ ምክነያት ከመኖር በላይ ትልቅ ነገር የለም፡፡ በጣም አዝናለሁ ዛሬ ግን በዚህ ደረጃ አደለንም፡፡ ምነው ብዬም ጠይቄው ነበር? አያያሳስብህ አለኝ፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ሰዎች እየታረዱ በአለበት ወቅት ስለነበር ይሄ ካላሳሰበኝ ምን ሊያሳሰብኝ ትፈልግ ይሆን ብዬ ዝም አልኩት፡፡ ሌሎቹ ግን ከዚህም በከፋ ደረጃ ስለሆኑ ብዙም ማለት አልፈልግም፡፡

ለምን?

እንግዲህ የሆነው እንዲህ ነው፡፡ እኔ ስለኦሮሞ ፖለቲካ አብዝተው ከሚጽፉ ነኝ፡፡ ዋና መሠረቴም ትውልዱን በተመረዘ ታሪክ እየመረዘው ነው በሚል ነው፡፡ ይሄን የምጽፈው ከማንነቴ ጋር አያይዤ ሳይሆን በትክክልም ስለሁኔታውና የተሰራውን ሴራ ሁሉ ስለምገነዘብ በከፍተኛ ቁጭት ነው፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ነኝ የሚለው ብዙ ትውልድ አባቶቹን እንዲጠላና እንዲያዋርድ ሆኖ ስለተሰራበት እርግማን ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ሞገስና ክብር የሚሆኑትን የማንነቱት መገለጫዎች የሆኑ የአባቶቹን ታሪክ ነው አዋርዶ ለወራዶች ሐሳብ ራሱን ባሪያ ያደረገው፡፡ አሁን እንደፈለጋቸው ይዘውሩታል፡፡ አሁን ከገባበት አጣብቂኝ ለውጣ ቢል እንኳን በምን አእምሮ፡፡ ማንም ከሜዳ መጥቶ በጥቂት ቃላት ወደሚፈልገው ይነዳዋል፡፡ ምን ምሁር ቢሆን ከዚህ ሊያመልጥ አልቻለም፡፡ ይሄ የሳዝነኛል፡፡

ሰሞኑን በተለያዩ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የዚህ አስተሳሰብ ባርነት ሰለባ የሆኑ ገና ምንም የማያውቁ ወጣቶች ቤተሰባቸውነ ሲነገራቸው በኖረው የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ ራሳቸውን ለአደገኛ ወንጀል አጋልጠው አይተናል፡፡ ምን አልባትም አንዳንዶቹ የዓመታት እስር ሁሉ ሊጠብቃቸው ይችላል፡፡ አሁንም ይብቃና እስኪ እራሳችንን እናስብ የሚል ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክነያቱም በዘመናት የተገነባ አዝተሳሰብ በአንድ ጀምበር ይወጣ እንኳን ቢባል አስቸጋሪ የሆናል፡፡ በዚህ ላይ ዋና የአስተሳሰብ መርዝ የሚዘሩት የገዛ ቤተሰቡን ጨምሮ አዋቂ ናቸው ብሎ የሚያምናቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እንግዲህ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እየተባለ ትውልዱን ወደ ከፋ የዘረኝነትና ጥላቻ አዘቅት የተወሰደበት መንገድ ብዙ ዓመት ሆኖት ዛሬ ራሱን የቻለ አዋቂ ሰውን አሳድጓል፡፡

ማሳሰቢያ ለእምነት ተቋማት

ለሙሰሊሙ፡– ሰሞኑን የሆነውና በጥቀምትም ሆኖ የነበረውም በሰዎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ የኦሮሞ እስላማውያንና የሌሎች አጋሮቻቸው የጋራ ሽብር እንደሆነ ለማታውቁ በማታውቁት ነገር ጉዳዩን ከኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮች ጋር ባታያይዙት እላለሁ፡፡ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን ኃይማኖታዊ መልክ ያለው የአክራሪ ቡድን እንጂ የኢትዮጵያን ሙስሊም ማህበረሰብ የሚወክል እምነት አለው የሚል ግምት የለንም፡፡ በትላንትናው እለት በድር ኢትዮጵያ የተባለ አካለ በሙስሊሙ ላይ ዘመቻ ተጀምሯል ሲል ያወጣው መግለጫ ስህተት ከመሆኑም በላይ አሸባሪዎች በግልጽ አሸባሪነታቸው ታውቆ እርምጃ እንዳይወሰድ ከለላ የሆነ መስሏል፡፡ የኦሮሞ እስላማዊ ቡድን ሲባል እንኳንስ የኢትዮጵያን ሙስሊም ይሄው ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ያሉ የኦሮሞ ሙስሊሞችንም ይወክላል አላልንም፡፡ የማናውቀውን አላወራንም፡፡ ይህ ጉዳይ ለረዥም ዘመን መንግስት ግልጽ ሊያወጣው ያልቻለ ግን አሳምሮ የሚያውቀው ነው፡፡ ከሱማሌ ክልል ድንበር ተፈናቀሉ በሚል ወደ ከተሞች አምጥቶ ማስፈርና ቄሮ በሚል እያደራጁ ትልልቅ ወንጀሎችንና የመንግሰትንም መዋቅር ጭመር ለመስበር ታስቦ እንደተሰራ ሁሉ አውቀን ነበር፡፡ በወቅቱ ብዙ ሰው የመሰለው ተራ የዲሞግራፊ ለውጥ መስሎት ነበር፡፡ ጉዳዩ ከዚህ በላይ የሆነ ሴራና በተለይም ደግሞ በአረቦች የሚታገዝ ጭምር እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ ስለዚህ ይህ ጉዳይ ከኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮች ጋር አንዳችም የማያገናኘውና በአገርና ሕዝብ ላይ ከሌሎች ጋር በመሆን የሚያሰሬ አደገኛ ቡድን እንደሆነ አውቀው ጉዳዩን በጋራ ማውገዝና እስልምናንም መሠደቢያ እያደረገ ያለውን አሸባሪ ቡድን መውገዝ ሲገባ ጭራሽ በእለስምና ሥም ከለላ መስጠት ከስህተትም በላይ ነው እንላለን፡፡ ይህ አሸባሪ ቡድን ኦሮሞን የሙጥኝ ብሎ በኦሮሞነት እየተከለለ ነው ዛሬ የደረሰበት የደረሰው፡፡ ብዙ ኦሮሞም ይሄን መረዳት አልቻለም፡፡

የሞጣ መስኪድ መቃጠል ጉዳይንም እንዲሁ የዚህ አደገኛ የሆነ ቡድን ሲጠቀምበት ነበር፡፡ በእርግጥ ነው በመስኪዱ መቃጠል ብዙዎች አውግዘዋል፡፡ በአግባቡ፡፡ አንዳንዶች ግን የመስኪዱን መቃጠል እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው አደገኛ ሴራቸውን ሲሸርቡበት ነበር፡፡ ሞጣ አንድ መስኪድ እንደተቃጠለ ብንሰማም አራት ነው የሚል ከሌሎች ሲነገር ሰምተናል፡፡ አነዱስ ቢሆን ለምን የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ስናይ እጅግ ብዙ ቃጠሎና ውድመት ደርሶባታል፡፡ ከዛ በላይ ግን ምዕመኖቿ እጅግ አሳቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ብዙ ሌላም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ አንዴ አደለም፡፡ በተደጋጋሚ፡፡ በዚሁ ሁሉ መከራ ተከታዮቿን ለአመጽ አላስነሳችም፡፡ የሞጣውን መስኪድ ቃጠሎ ግን አመጽ ለማስነሳት እንደጥሩ አጋጣሚ ቀጥረው ብዙ የሙስሊም እምነት ዋና መሪዎች ሳይቀሩ ሲጠቀሙበት እንደነበር ታዝበናል፡፡ በዛን ወቅት የኦሮሞ እስላማዊው ቡድን የእስላም ቄሮ ምን ትጠብቃለህ ሲል ሰምተናል፡፡ የዛን መስኪድ መቃጠል ሁሉም አውግዞታል፡፡ ሁለተኛም እንደዛ ያለ ችግር ላይገጥም የተሻለ መተማመን አለ፡፡ ለመሆኑ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ሁለተኛ እንዳይደርስ ምን ዋስትና አለ? በሞጣ ሰው አልሞተም፣ በሞጣ ሴረኞች እንደሚያራግቡትም አደለም የሆነው፡፡ ምን ዓልባትም ከዛ መስኪድ ቃጠሎ ጀርባ ሴረኞቹ እንዳሉም ፍንጮች አሉ፡፡ እንግዲህ ለሕሊና ያደረ እየሆኑ ያሉትን እውነቶች ተመልክቶ አስተማሪም ገሳጭም መልዕከት ማስተላለፍ ያለበት ለአጥፊዎች ነበር እንጂ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አደረሱብን ስለሚሏቸው አሸባሪዎች ባልሆነ፡፡ ሰሞኑን አንድ የእስልምና እምነት መሪ የሆኑ ግለሰብ ስለጀዋር መፈታት እንዳለበት ሲያስጠነቀቁን ተመልክተናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ስለ አለቁት ዜጎች ግን ምን ገዷቸው፡፡ ይልቁንም ደስ  ባይላቸው፡፡

በመሆኑም እንዲህ ያለ ከሕሊና የወጣ ሴራዊ ተልዕኮ ያላችሁ የእስልምና መሪዎች እራሳችሁን ለዩ፡፡ ማንም በእስልምና ላይ ጣቱን አልቀሰረም፡፡ እስልምና ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በእናንተ አይደለም፡፡ ይህች አገር ኢትዮጵያ ማንንም በእምነቱ የተነሳ እንዳታሳደድ ከጅምሩ እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ዛሬ እስላም ሁሉ መዲናዬ የሚላት መካ ያሳደደቻቸውን ወገኖች ተቀብላ ይሄው ለዘመናት እስልምናም ክርስቲናውም አብረው የኖሩት፡፡ ይሄ በሌሎች አገር አልሆነም፡፡ ወይ እስላሙ ክርስቲያኑን ያጠፋዋል ወይ ክርስቲያኑ እስላሙን፡፡  ኢትዮጵያ ከሌሎች አገራት በተለየም የአይሁድ እምነት ተከታዮችንም አቅፋ የያዘች ነች፡፡ እርግጥ ነው የኦሪት እምነትከክርስትናውም የቆየ ታሪክ አለው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ ካሉ አብያተክርስቲያናት የሚለያት አንዱ የኦሪትን ሕግጋጥ ከክርስትናው ጋር አዋሕዳ እስካሁንም መቀጠሏ ነው፡፡  ስለዚህ እስልምናን እናንተ ያመጣችሁት አደለም፡፡ ይልቁንስ እስላም ሆኖ በኢትዮጵያዊነቱ እየኮራ ለሌሎች ማሳወቅ ሲገባው የጽንፈኞቹ አተያይ የአረባዊነት ሕልም ነው፡፡ የእስላማዊ ኦሮሞ ቡድንም ዓላማ ኢትዮጵያን ከአረባውያን ጋር ለማፍረስ ነው፡፡ ይሄን ካላወቃችሁ እወቁ ግን ከእስልምና ጋር እያጀባችሁ ለአሸባሪዎች ከለላ አትሁኑ፡፡

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፡- የሆነውን ማውገዝና ስለተጎዱት ወገኖች መጸለይና አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ያለፈ ግን በቤተክርስቲያኗ ባልተለመደ ሁኔታ በአደባባይ ሰልፍና የአደባባይ ጸሎት በሚል እየተካሄዱ ያሉ ዝግጅቶች ትልቅ ስህተት እንደሆነ ለማሳሰብ አወዳለሁ፡፡ አንተ ማን ነህና ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ማንም ልሁን የምለው ጉዳይ ግን እውነትነት እንዳለውና እንደሌለው መርምሩ፡፡ በቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ በአደባባይ ለመታየት በሚመስል ሁኔታ የሚደረግ ተግባር ሐይማኖታዊ መሠረት አለው የሚል እምነት የለኝም፡፡ በእርግጥ ነው ሁሉንም ያካተቱ ሰልፎች በሚደረጉበት የሐይማኖት አባቶች ተገኝተው መካሪና ገሻጭ መልዕክቶችን ቢያስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ቤተክርስቲያኗ በምታዘጋጀው የሰልፍና የጸሎት መሪሐ ግብር አይነት ዝግጅት እጅግ ስህተት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን በአደባባይ ሰልፍና ተቃውሞ አደለም እዚህ የደረሰቸው፡፡ ጸሎት ከሆነም በራሷ መቅደሶች እንጂ በየደባባዩ ለእይታ ታስቦ አደለም መሆን ያበት፡፡ ከዚህ ይልቅ ቤተክርስቲያኒቱ በአላት መዋቅሮች የኢትዮጵያ መንግስትንም ይሆን ሌሎች መንግስታትን እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ እየደረሰባት የላውን ጥቃት ሕጋዊ አግባብ ባለው ሁኔታ ማሳወቅና ማሳሰብ ነው፡፡ ይሄ አካሄድ ትክክለኛ ተቋዊ አካሄድ ሲሆን ማንም እየተነሳ በአደባባይ የቤተክርስቲያን ሰልፍና የጸሎት መርሀ ግብር በሚል የቤተክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ፍልስፍናዎችን መበረዝና ሌላ እንግዳ ልማድ ማምጣት አደገኛ ስህትት ነው የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ እየተለመደ የመጣ ከአውደምህረት ውጭ የሆነ መርሀግብር በሚል እየተደረገ ያለ አሰራር ተከታዮቿን የባዕዳንን እምነት ማለማመድ ሆኖ ነው የማየው፡፡

ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ ያልነበሩ አሁን አሁን እንደ ትክክለኛ ነገር እየተቆጠሩ የመጡ ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቆመው ለማስቀደስና ሌሎች ስርዓቶችን ለመከታተል ለማይችሉ ካልሆነ   ወንበር የለም፡፡ አሁን አሁን ግን የቤተክርስቲያኒቱ መቅደሳት ጥቅጥቅ ባለ ወንበሮች ተሞልተው ከቤተ መቅደስነት ይለቅ የሥብሰባ አዳራሽ መስለው እናያቸዋለን፡፡ ሰዎች የሚሰግዱበት ሥፍራ እንኳን የለም፡፡ ይሄ አሁን አሁን እንደ ዘመናዊነት መጥቶ ጭራሽ ወንበሩ ጥቅጥቅ ብሎ ካልሞላ የቤተክርስቲያኒቱን መሥፈርት እንዳላሟላ እየታየ ነው፡፡ ቤተመቅደስ የምንሄደው ቆመን ልንጸልይና ከዛም በላይ ልንሰግድ እንጂ ልንቀመጥ አይደለም፡፡ መቀመጥ ቢያስፈልገን እንኳን ወለሉ ላይ መቀመጥ ነው፡፡ ይሄ ጥንት በሁሉም አብያተክርስቲያናት አልነበረም፡፡  ቆይቶ ግን ዘመናዊነት መስሏቸው ወንበር ቤተመቅደሳቸውን የሙሉ ተከታዮችን ሙልጭ አድርገው ከቤተመቅደሳቸው አውጥተዋል፡፡ የምንቆመው ሰማይና ምድርን በፈጠረ አምላክ ፊት መሆኑ ተዘንግቶን፡፡ ይቀጥላል፣ አሁን አሁን ደግሞ በእርግጥም ቤተመቅደሱ እንደመሰብሰቢያ አደራሽነትም እየገለገለ ነው፡፡ በቤተመቅደስ ውጭ  ከቅዳሴ፣ ዜማና ቅዳዜን ተንተርሶ ከሚሰጡ ትምህርቶች ውጬ ረዘም ያለ ስብከት እንኳን የሚሰጠው ከቤተመቅደስ ውጭ በተሰራ ደጀ ሠላም ነው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሐየር ማስተዋሉን ይስጠን! ኢትየጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ