logo

ሐምሌ 28, 2020

Source: https://amharic.voanews.com/a/olf-chairman-7-28-2020/5521015.html
https://gdb.voanews.com/236D40D3-BDEB-477A-9D73-035E0C1B480E_cx0_cy5_cw0_w800_h450.jpg

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ

አዲስ አበባ — የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በመንግሥት ፀጥታ ኃይል ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ከተከለከሉ ከ10 ቀናት በላይ እንደሆናቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከኦነግ ደምብና ከእርሳቸው እውቅና ውጭ የሆነ ስብሰባም በጉለሌው ፅህፈት ቤታቸው መካሄዱን ገልፀዋል።

ስብሰባውን የመሩት አቶ አራርሳ ቢቂላ ስብሰባው የአቶ ዳውድን ሊቀመንበርነት ለመቀማት አይደለም ብለዋል።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ለምን ቤት ውስጥ እንደታጎሩ ለመጠየቅ ወደ ፌዴራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ዳውድ ኢብሳ “ቁም እሥር ላይ ነኝ” አሉ

by ቪኦኤ