No photo description available.
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የመንግስት ባለስልጣናት ከጥላቻ ንግግራቸው እንዲታቀቡ ባልደራስ አስጠነቀቀ::

ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ላይ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እና በብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ በሆኑት አካላት ከሕግ ውጪ እየተካሄደብን ያለው የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጉደፍ እንዲታረም የቀረበ አቤቱታ፤
ፓርቲያችን “ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ” በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ የተሻለ የፖለቲካ አማራጭ ለህዝብ በማቅረብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ሆኖም የፓርቲያችን ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አላግባብ በ24/10/2012 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ በብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና በመንግስት ባለስልጣናት እራሱን “ባለአደራ” ብሎ የሚጠራው ፓርቲ እየተባላ የፓርቲውን መልካም ስም የማጥፋት፣ አባላትን የማሸማቀቅ ተግባር እና የጥላቻ ንግግሮች በስፋት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሆነው ኢ.ቢ.ሲ. እና የፓርቲያቸው ልሳን በሆኑት ፋና፣ ዋልታ ሚዲያዎች እየተካሄደብን ይገኛል፡፡

ይህ ተግባር በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊኖር የሚገባውን መልካም ግንኙነት ከማበላሸቱም በላይ በሕዝቦች መካከል ከፍተኛ ጥላቻና አለመተማመን በመፍጠር የአገራችንን ሚዲያ ወዳልተፈለገ ጽንፍ የሚወስድ ማስተዋል የጎደለው እንቅስቃሴ ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት ፕሮፓጋንዳም እና ቅድመ ፍረጃም፣ አላግባብ ታስረው የሚገኙት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ያለተጽእኖ እውነተኛ ፍትህ ያገኛሉ የሚል እምነት ፓርቲያችን እንዳይኖረው አድርጎናል፡፡
ስለሆነም ፓርቲያችን “ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ” በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሆነው ኢ.ቢ.ሲ. እና የፓርቲው ልሳን በሆኑት ፋና፣ ዋልታ ሚዲያዎች ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሄደብን ያለውን የጥላቻ እና ፍትህን የሚያዛባ ፕሮፓጋንዳ ብሮድካስት ባለስልጣኑ መርምሮ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የእርምት እርምጃ እንዲወስድ እና ለጠፋው የፓርቲያችን ስም በተመጣጣኝ የአየር ሰዓት ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

Image may contain: text
No photo description available.