July 29, 2020

DW – ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ በተገደለ ማግስት በተቀሰቀሰዉ ሁከትና ረብሻ ተጠርጥረዉ የታሰሩት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፖለቲከኛ ጀዋር መሐመድ በየፊናቸዉ የተጠረጠሩበትን ክስ ዉድቅ አደረጉ። ሁለቱ ፖለቲከኞች በየፊናቸዉ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ቀጠሮ ችሎት እንደነገሩት ሰላማዊ ፖለቲካን ከማራመድ ዉጪ የሰሩት ጥፋት የለም። አቶ እስክንድር የችሎቱ ሒደት ለሁሉም መገናኛ ዘዴዎች ክፍት እንዲሆን ሲጠይቁ፣ አቶ ጀዋር መሐመድ ደግሞ አሳሪዎቻቸዉን በፖለቲካዉ ሜዳ ማሸነፍ ስለማይችሉ እኔን አስረዉ ከምርጫ ለማግለል የወጠኑት ሴራ ነዉ ማለታቸዉን ጠበቆቻቸዉ በየበኩላቸዉ አስታዉቀዋል።ፍርድ ቤቱ የአቶ እስክንድርን ጉዳይ ነሐሴ አንድ፣የአቶ ጀዋርን ደግሞ ነሐሴ አምስት 2012 ለመመልከት ቀጥሯል። Audio Player00:00