2 ነሐሴ 2020

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በኢትዮጵያ የ10 ተጨማሪ ሰዎች ሕይወት በወረርሽኙ አለፈ
  2. በሙከራ ላይ ያሉት ክትባቶች ከምን ደርሰው ይሆን?
  3. በአማራ ክልል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አስገዳጅ ሆነ
  4. በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 265 ደረሰ
  5. ሜክሲኮ ከፍተኛ የሞት ቁጥር በማስመዝገብ ሦስተኛዋ አገር ሆነች
  6. ሆንግ ኮንግ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫዋን ለአንድ ዓመት አራዘመች
  7. የዚምባብዌ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ
  8. ዛምብያ በአገር ውስጥ የሚካሄዱ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በድጋሚ አቋረጠች
  9. አፍሪካውያን የጣሉትን የእንቅስቃሴ ገደብ እንዳያነሱ ዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ
  10. የአውሮፓ ህብረት አልጄሪያን ወደ አውሮፓ መጓዝ ከሚችሉ አገራት ዝርዝር ሰረዘ
ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ ግራፊክስ

BBCCopyright: BBC

በዛሬው ዕለት 7ሺህ 607 የላብራቶሪ ምርመራ ተከናውኖ 707 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 18 ሺህ 706 መድረሱን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ ዕለታዊ መግለጫ አመላክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ አገሪቱ መዝግባው የማታውቀው 28 ሟቾችን የመዘገበች ሲሆን አገሪቷ እስካሁን በቫይረሱ ያጣቻቸውን ሰዎች ቁጥር 310 አድርሶታል።

በባለፉት 24 ሰዓታት 406 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 601 መሆኑንም መግለጫው አስፍሯል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 437 ሺህ 319 የላብራቶሪ ምርመራዎችን አከናውናለች።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የማህበረሰብ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ሆኗል።

በመሆኑም ወረርሽኙን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር “ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ” በትናንትናው ዕለት የብሄራዊ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በይፋ አስጀምረዋል።

ዘመቻው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በማድረግ ማህበረሰቡ የመከላከያ መንገዶችን በኃላፊነትና በንቃት እንዲተገብር የሚያስችል እና ሰፊ ምርመራ በማድረግ የወረርሽኙን ሁኔታ ይበልጥ በማወቅ ቀጣይ ሁኔታዎችን ለመወሰን የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

“ማንም” የሚል ስያሜ የተስጠው ዘመቻ ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን በነሃሴ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት 200 ሺህ ሰዎችን የመመርመር ዕቅድ ተይዟል።