By ዘ-ሐበሻ
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/109469
August 13, 2020
የኢትዮጵያውያን የዘር ፍጅት መከላከል ንቅናቄ በአውሮፓ
Ethiopians Genocide Prevention Movement in Europe
መግለጫ
በሃገራችን የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ፣በተፈጠረው ክፍተት በመጠቀም፣ በአንዳንድ ጽንፈኛ ሃይሎች፣ እየተደጋገመ እየተፈጸመ ያለው፣ ማንነትን እና እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በእነዚህ ማንነት እና እምነት ተኮር ጥቃቶች፣ዜጎች ከቤት ነበረታቸው ተፈናቅለዋል፣ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት ሰለባ ከሆኑት በተጨማሪ፣ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች፣ውድ ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደረጓል።
ህግ በማስከበር፣ የዜጎችን በህይወት የመኖር እና የንብረት መብት የመጠበቅ፣ እንዲሁም የማስከበር ሃላፊነት ያለባቸው የመንግስት አካላት፣ ጥቃቶቹን በማስቆም ረገድ ያሳዩት ቸልተኝነት/ደካማ ተነሳሽነት፣ጽንፈኞቹን ለተደጋጋሚ የጅምላ ዘር ፍጅት ተግባራት እንዲቀጥሉ ምክኛት ሆኗል።
ይህን ሁኔታ በሚገባ በመረዳት እና ከመደራጀት በቀር ምርጫ አለመኖሩን በመገንዘብ፣በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት የምንገኝ በተለያዩ የሙያ ዘረፍ ላይ የምንሰራ ኢትዮጵያውያን፣በሃገር ቤት ፍትህ ላጡ ወገኖች፣ጉዳያቸው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት አግኝቶ፣ጥቃት ፈጻሚዎቹ እና የማህበራዊ ሚድያውን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች፣የጅምላ ፍጅትን የሚያበረታቱ ግለሰቦችን፣ በፍትህ ተጠያቂ የማደረግ፣ የፍትህ ለግፍ ሰለባዎች የአውሮፓ ግብረሃይልን፣ መስርተናል።
ከዚህም አላማው በመነሳት፣በሃገራችን እየተፈጸመ ያለውን ማንነት እና እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት፣መረጃ የማሰባሰብ፣የጥቃት አደራሽ ጽንፈኞችን ማንነት በመለየት በህግ ተጠያቂ የሚሆኑበትን መንገድ መስራት፣በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ጅምላ ፍጅት ያስተባበሩ፣የፈጽሙ፣ ፈጻሚዎቹን በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ያበረታቱ ቡድኖች እና ግለሰቦች ዓለም አቀፍ የዝውውር ማእቀብ እንዲጣልባቸው፣ንብረታችው እንዲታገድ፣ለማደረግ።የደረሰውን ጥቃት በአይነት እና በመጠን በመዘገብ፣ተጎጂ ወገኖች ካሳ የሚያገኙበትን ሁኔታ አስተባብሮ የመስራት ስራ ይሰራል።
የፍትህ ለግፍ ሰለባዎች የአውሮፓ ግብረሃይል ወደፊት በሁሉም የአውሮፓ ሃገራት ወኪሎች የሚኖሩት ሲሆን፣በቀጣይነትም ማንኛውም ያገባኛል የሚል ስብዓዊ ፍጥረት ከጎናችን በመቆም፥ በጊዜ፥ በክህሎትና በገንዘብ በመደገፍ ለአላማችን ከግብ መድረስ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ እናቀርባለን።
የፍትህ ለግፍ ሰለባዎች የአውሮፓ ግበረሃይልን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትና የእንስቃሴው አባል መሆን የምትሹ በሚከተሉት አድራሻዎች ልትጽፉልን ትችላላችሁ፤
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!
የፍትህ ለግፍ ሰለባዎች የአውሮፓ ግብረሃይል።
Telephone : +46704731818
+447970350860
E-mail : egpmeu@gmail.com