በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1,086 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,688 የላብራቶሪ ምርመራ 1,086 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 394 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 26,204 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 479 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,428 ደርሰዋል።
