በህይወት የመኖርና የአካል ደህንነት መብት ይከበር!
–
ነሀሴ 7/ 2012 ዓ.ም
–
መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ከአሁን ቀደም የክልልነትና የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከተፈጠሩት ተመሳሳይ ኹነቶች ትምህርት በመውሰድ በሕጋዊ መንገድ መልስ ለሚያገኝ ጥያቄ በሰው ሕይወት እና አካል እንዲሁም በሕዝብም ሆነ በመንግሥት ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ሊያስቀር በሚችል መልኩ ጥያቄዎችን መፍታት ተገቢ ሆኖ ሳለ፣ ተመሳሳይ ጥፋት በሚያስከትል መንገድ ላይ በድጋሚ መገኘቱ፣ በሰብዓዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ ላይ በርካቶች ጥለውት የነበረውን ተስፋ የሚያጨልም እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢሰመጉ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

