12:43 17 ነሐሴ 2020

ግራፊክስ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 19 ሺህ 747 ናሙና ምርመራ 1 ሺህ 460 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለትም በቫይረሱ የ16 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የሟቾቹን ቁጥር 544 አድርሶታል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 165 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 12 ሺህ 524 ሰዎች አገግመዋል።

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 31 ሺህ 336 ደርሷል።

የቫይረሱ ሥርጭት እየጨመረ ሲሆን ሥርጭቱን ለመግታት “ምክንያት አልሆንም” የሚል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተለያዩ ዘመቻዎች እየተደረጉ ነው።

መጭውን የቡሄ በዓልም ልጆች በቤታቸው ሆነው እንዲያከብሩ ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።

Article share tools