ምኒሊክ እና ነሐሴ
– ኢዮብ ዘለቀ
–
“የምጥ መጀመሪያ
“ባንድ ወቅት የሸዋ ንጉስ ሳህለስላሴ መቀመጫ በነበረችው አንኮበር አንድ ወሬ ተናፍሶ ኖሮ ድፍን ሸዋን አደረሰው :: ጋብቻ ዘር ተቆጥሮ ሀብት ተመዝኖ ይፈጠም በነበረበት፤ ከጋብቻ ውጪ መተኛት በሚወገዝበት በንጉስ ሳህልስላሴ ቤተመንግሰት ውሰጥ ድርጊቱ መፈጠሙ አገሬውን ጉድ አሰኝቶ የቡና ማጣጫ ሆነ::
–

ነገሩ ወዲህ ነው ፣ግልስቧ ወ /ሮ እጅጋየሁ ይባላሉ በአንኮበሮች ዘንድ እጅግ ከፍትኛ የሆነ ክብር ከሚሰጣቸው ከ አለቃ ምላት ቤት በአገልጋይነት ተቀጥረው ይሰሩ ነበር ይባላል ፣ታዲያ በአንድ ወቅት አኚህ ሴት በህልማቸው ፀሀይ ከ ማህጸናቸው ሲወጣ ያያሉ ማየቱስ ባለከፋ ግና አየሁት ያሉት ህልም ወትሮ ያዩዋቸው ከነበሩ ህልሞች ትንሽ ወጣ ያለ በመሆኑ አንቀልፍ ነሳቸው::ወ/ሮ እጅጋየሁ በመጀመሪያ አካባቢ ይህንን ታላቅ ምስጢር የያዘ ህልም ለማንም ለማካፈል ድፍረቱም ፍላጎቱም አልነበራቸውም ፤ሁላ ላይ ግን ይህንን አቋማቸውን በመቀየር በጣም ይቀርባዋቸው ለነበሩትና እንደሳቸው በዛው በ አለቃ ምላት ቤት አገልጋይ ለነበሩት ጥቂት ሴቶች ለ ማንም እነዳይናገሩ አስጠንቅቀው ያዩትን ህልም ሁሉ ያካፍሉቸዋል:: “አትነገር ብዬ ብነገርው አትናግር ብሎ ነገረው” አይደል የሚለው የሃገሬ ሰው; ታዲያ ከዚህች ቅጽበት አንስቶ ምስጢሩ ምስጢርነቱ አከተመ፤ አነዚህ ሴቶች ቃልበይ ሆኑና መሃላቸውን ዘንግተው ወሬውን ነዙት፤ ወሬውም አንደ አውሎነፈስ አገር አዳረሰ አለቃ ምላት ዘንድ ለመድረስም ጊዜ አልፈጀበትም::
–
“ጉዞ ወደሳህለስላሴ ቤተመንግሰት”
–
አለቃ ምላት ነገር አዋቂ ናቸው ሊያውም ታላላቅ ሚስጢራትን በቀላሉ የሚረዳ ባለ በሩህ አእምሮ ባለቤት፣ አለቃው ወ/ሮ እጅጋየሁ አየሁ ያሉትን ህልም ምስጢር በሚገባ መርምረወል፤ የህልሙን ትርጉምም ተረድተዋል ፤ሁኖም ግን ያለወትሮው የዚህ ህልም ነገር አሳስቡዋቸው ኖሮ አእምሮዋቸው በሃሳብ ተወጠረ ፤ አንዱን ያነሳሉ ይጥላሉ ሌላውንም ያነሳሉ እሱነም ይተዋሉ ። እንዲህ በሃሳብ ሲዋትቱ ነበር ሳይታሰብ ቀኑ መሽቶ የሚነጋው፣ መቼስ ታስቦ ታሰቦ ሜዳ ላይ አየቀረምና በስተመጨረሻ ወደ አንድ ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ” ወ/ሮ አጅጋየሁ ከ ንጉስ ሳህለስላሴ ቤት ተቀጥረው መስራት አለባቸው! “የሚል ነው ውሳኔያቸው ።ሁላም በአለቃ ምላት አማካኝነት ነገሮች ሁላ እንዲቃኑ ተደረጎ ወ/ሮ አጅጋየሁ በንጉስ ሳህላስላሴ ቤተመንግሰት በ አገልጋይነት ተቀጠሩ::
–
“የነሐሴው ጠሐይ
“ለወ/ሮ እጅጋየሁ፤ ህይወት በ ንጉስ ሳህለስላሴ ቤተመንግሰት የምጥ ያህል ከብዷል ፤ ምክንያት ከተባለ ደግሞ ያ ከ አለቃ ምላት ቤተመንግሰት አፍትልኮ የወጣው ወሬ ከሳቸው ቀድሞ በቤተመንግሰቱ በመግባቱ ነው፣ አሁን ነገሮች ሁላ በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው፣ የህልሙ ወሬ ከንጉሱ ባለቤት ከወ/ሮ በዛብሽም ዘንድ ደርሷል እሳቸውም መች የዋዛ ሆኑና ይህ በህልም ታየ የተባለው ጠሀይ ከልጃቸው በአንዱ ሊያውም በጣም ከሚወዱት ከሰይፉ ሳህለስላሴ እንዲወለድ ፈለጉ ይህም ይሆን ዘንድ ወ/ሮ እጅጋየሁ ከ ሰይፉ ጋር አንዲተኙ ጥብቅ ትእዛዝ ይተላለፍባቸዋል::–ሰይፉ ግን ሚሽቱን በጣም ይወድ ነበርና የናቱን ትዛዝ ተቀብሎ ከሌላ ሴት ጋር መተኛትን ህሊናው ፈጥሞ አልቀበል ይለውና በሁለት ሃሰቦች ተወጠረ–በአንድ በኩል የናቱን ቃል ለማክበር ሲል” እሺ “ቢል የሚሽቱ ነገር የራስ ምታት ሁነበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ አንቢ አንዳይል የናቱ ቁጣ ረፍት ነሳው፤ ታዲያ በነዚህ አስቸጋሪ ምርጫዎች ውስጥ ሆኖ በሃሳብ እየባዘነ ሳለ ነው የሀሳብ ጥጉ መፍተሄ ነውና አንዲት ሃሳብ ብልጭ ያለችለት ይህውም እናቱ ወ/ሮ በዛብሽ ሳያውቁ ወንድሙ ሃይለመለኮትን ለምኖ ከወ/ሮ አጅጋየሁ ጋር አንዲተኛ ማድረግ የሚል ነበር::ሃይለመለኮት የወንድሙን ጭንቀት ተረድቶዋልና ሊያሳፍረው አልፍለግም፤ በዚያች ምሽትም ከ ወ/ሮ እጅጋየሁ ጋር ተኛ ምኒለክም ተጠነሰ ያ በጥንት ዘመን ” ምኒሊክ በሚል ስም የሚነግስ ንጉስ ኢትዮጲያን ታላቅ ያድረጋታል” የተባለለት ምኒሊክ ከአንዲት የቤተመንግሰት አገልጋይ መጸነሱ ብዘዎቸን ግራ አጋባ ነገር ግን ትንቢት ነውና መሆን ያለብት ሁላ ሆነ ጠሀይቱም በመላዋ ጦቢያ ፈነጠቀች ምኒለክም በነሐሴ 12 ተወለደ፤ እንኳን ለእምየ ምኒልክ 176ኛ ዓመት የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ ።***********************************************
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ