አምነስቲ ኢንተርናሽል ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ላይ ያወጣው ቪድዮ ስህተት መሆኑን ገልጾ ይቅርታ ጠየቀ
ድርጅቱ ከአራት ቀናት በፊት “The Fight for Justice” የሚል ኢትዮጵያ ላይ ያተኮረ አንድ ቪድዮ አጋርቶ ነበር። የቪድዮውን ወውጣት ተከትሎ በይዘቱ ዙርያ በርካታ አስተያየቶች ተሰንዝረው የነበረ ሲሆን አምነስቲም አስተያየቶቹን ተቀብሎ “በስህተት ስላወጣነው የሚድያ ስራ ይቅርታ እንጠይቃለን ብሎል።

ይህን ተከትሎ ግን በርካታ ሚድያዎች፣ የመንግስት ሀላፊዎች እና ተንታኞች አምነስቲ ይቅርታውን የጠየቀው ግንቦት 29 ቀን ባወጣውና “Beyond Law Enforcement” በሚለው ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዳሰሰበት ሪፖርት ዙርያ እንደሆነ ዛሬ ሲዘግቡ እና ሲፅፉ ታይቷል። አምነስቲ ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ አሳውቋል።–በመሆኑም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትላንት በቲውተር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ ቪድዮ አሉታዊ ተፅኖ የነበረው ከስህተት ጋር የወጣ ነው በማለት ይቅርታ ጠይቋል፡፡
Amnesty International has always supported the human rights of all Ethiopians. We remain conscious of Ethiopia’s complex and evolving political climate. Our comms team recognizes the negative impact of our recent media output and apologises for posting it in error.
1.4K 1.1K people are Tweeting about this
“በትናንትናው እለት ስህተታችንን አምነን ያወጣነው መረጃ ከአራት ቀን በፊት ይዘን በቀረብነው ቪድዮ ዙርያ ነው። ከዛ ውጪ ግንቦት ወር ላይ ይዘን በወጣነው ሪፖርት ዙርያ አሁንም እንተማመናለን” ብላ ለኢትዮጵያ ቼክ መልስ የሰጠችው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ የሆነችው ካትሪን ምጌንዲ ናት።