12/12/2012

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ22ሺህ 101 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ፤ 1ሺህ 386 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ይህም በአገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎችን ቁጥር 32ሺህ 722 አድርሶታል።
ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓታት 414 ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።
