ዕለታዊ መግለጫ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 21 ሺ 326 ናሙናዎች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 1336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ።

የጤና ሚንስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጡት መግለጫ እንደተመለከተው፤ 28 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። ይህም የሟቾችን ቁጥር 600 አድርሶታል።

370 ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ ከህመሙ ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ እስካሁን ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን ወደ 13 ሺ 308 ከፍ አድርጎታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ በበሽታው የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 34 ሺህ 058 ሆኗል።

በአጠቃላይ የቫይረሱ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር ደግሞ 672 ሺ 637 ደርሷል።