በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1778 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,456 የላብራቶሪ ምርመራ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 228 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 35,836 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 620 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 13,536 ደርሷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ

የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 21,456 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
20 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ 228 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ሲል ዕለታዊ መግለጫው አመልክቷል።
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥርም 21ሺህ 678 ሲሆን በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገኙ ደግሞ 248 መሆናቸው ተገልጿል።
እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ 35 ሺ 836 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 620 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
በአጠቃላይ ከበሽታው ማገገማቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 13ሺህ 536 መድረሱን በጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ መግለጫ ላይ ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ከተረጋገጠበት ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ 694 ሺ 093 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጓል።Article share tools
- ያጋሩ