August 22, 2020 – Konjit Sitotaw
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ39 ሺህ አለፉ።
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,776 የላብራቶሪ ምርመራ 1,368 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ25 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 567 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 39,033 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 662 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,480 ደርሷል።