
በአሜሪካ በቨርጂናያ ሰቴት በአለክሳንድርያ ከተማ በሚገኝ የኢትዮጵያውያን ኪዳነ ምህረት ቤተክርሰቲያን የኮቪድ-19 ሥርጭት መከሰቱ ተሰምቶል፡፡
–
በኦገስት 14፣ 15 እና 16 በነበረው የፀሎት ፕሮግራም ቁጥራቸው ከፍ ያለ ምዕመናን ስለመጋለጣቸው ጥቆማ ደርሶናል፡፡ ከተጋለጡት መካከል እስካሁን የሚታወቀው 7 ሰዎች በሆስፒታል የህክምና እርዳታ እያገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ መሀል 3ቱ በጠና ታመው በ Intensive Care Unit (ICU) እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡
፡–
በነዚህ ቀናት ተጋልጠው የኮቨድ-19 ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል እስካሁን ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል::
ሆኖም የአካባቢው የጤና ቢሮ ክትትል አድርጎ እሰከሚያስታውቅ ድረስ ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ አይቻልም፡፡በዚህ አጋጣሚ ለታመሙት በሰላም ቶሎ እንዲያገግሙ እየተመኘሁ፣ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በቤተክርስቲያኑ የነበራችሁ ሰዎች ወደ አለክሳንደሪያ የጤና ቢሮ እየደወላችሁ ምርመራ እንድታደርጉ ይመከራል፡፡
–
በዚህ ጉዳይ ስልኩን ጨምሮ የአለክሳንደሪያ የጤና ቢሮ ያሠራጨው በራሪ ወረቀት ከታች የተያያዘ ሲሆን፣ መረጃው ለሁለም እንዲደርስ ይመከራል፡፡በየትም ቦታ ብንሆን የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል የጤና ባለሙያዎችና መንግሥት የሚሠጡትን ምክር ባለመሰልቸት በመቀበል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
–
ማህበረሰባችን በጣም የተሰሳረ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረግን ኮቪድ-19 በቀላሉ ሊሠራጭ እንደሚችል ያሰጋል::
For Immediate Release: August 21, 2020

The Alexandria Health Department (AHD) has determined that there may have been a COVID-19 exposure at Kidane Mehret Church (75 S. Bragg St.). Anyone who entered the building or was on the church grounds on August 14, 15, 16 or 17 may have been exposed to the virus and should immediately stay home and away from others for 14 days from their last visit to the church, and monitor for symptoms.
Potential symptoms may include fever, cough, shortness of breath, sore throat, headache, chills, muscle pain, or new loss of taste or smell. Anyone with chest pain or shortness of breath should call or text 911 immediately.
Anyone who develops symptoms should immediately call a healthcare provider to be tested for COVID-19. Those who do not have a doctor or insurance can call any of the providers on this list of healthcare facilities.
AHD urges anyone who visited Kidane Mehret Church on August 14, 15, 16 or 17 to call 703.309.8276 for further guidance. Visitors to the church on those days should avoid having guests visit them, not share items like towels and plates, stay at least 6 feet away from others, and wear a mask when around people who have not had the same exposure.
Kidane Mehret Church is currently working with AHD to take the necessary steps to protect their church community.