August 22, 2020

አከራካሪው የፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ጽሁፍ የብሔራዊ መግባባት ውይይትን አቅጣጫና የመድረኩን ንግግር ወደ ሌላ አቅጣጫ ቀይሮታል።

”ሚኒሊክ ነፍጠኛ ነው” ለሚለው የፕሮፈሰር መራራ ንግግር የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድና አቶ ማሙሸት አማረ አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል! ቪድዮውን ዝቅ ብለው ያገኙታል

”የዶክተር መራራ ንግግር ለሌላ ዙር እልቂት የሚጋብዝ ነው”አቶ ማሙሸት አማረ–”አጼ ሚኒሊክ ነፍጠኛ ነበሩ” ለሚለው የመራራ ጉዲና ንግግር የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል!

”ዶክተር መራራ አንድም ነጥብ ማቅረብ የማይችሉበትን የአኖሌ ሃውልትን ከአጼ ሚኒሊክ ጋር አገናኝተው ያቀረቡት ሃሳብ በጥላቻ እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ እስከ ዛሬ ድረስ በፖለቲካ አስተሳሰባችው እና በፕሮግራማቸው ሲጠቀሙበት የነበረ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህ ንግግር አሁንም ለሌላ ዙር የኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እልቂት የሚጋብዝ ነው። ከዚህ የጨለመ አስተሳሰብ የማንወጣበትን ውይይት በመቅረቡ በመጀመሪያ ደረጃ አዝኛለሁ።

በአለም አደባባይ ”ኢትዮጵያ ዳውን ዳውን” ብሎ የወጣ ህዝብ እኮ እነ ፕሮፈሰር መራራ በሚቆሰቁሱት እሳት እንደሆነ ይገባናል። በአለም ላይ ሃገሬ ትፍረስ ብሎ በሌላ ሃገር ላይ የወጣ ህዝብ እኔ ሰምቼ አላውቅም፣ ወደፊትም ይኖራል ብየ አላስብም።” ብለዋል

”ማስለቀሻ ከፈለግን ሁላችንም ጋር አለ”አቶ ጣሂር መሃመድ

”ሚኒሊክ ነፍጠኛ ነው” ለሚለው የፕሮፈሰር መራራ  ንግግር የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ የሚከተለውን አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል!”

የኦሮሞን መስፋፋት ሌላ ስም እንስጠው ካልተባለ በስተቀር ወደ ጎንደርም ሆነ ወደ ተለያየ ቦታዎች ሲሄዱ እርስዎ የጠቀሱትን ከአርሲ የባሰ ውድመት አድርሶ እንደነበር እንደ እርስዎ አይነት ሰው ሃቁን ክዶ መነሳቱ ተገቢ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ የሚባለው ሃገር መኖሩ ነው ያገናኘን።

እዚህ ጋር ግልጽ መሆን ያለበት ሁሉም አካል ማስለቀሻ ካስፈለገው ቅድም እንዳልኩት በሜዲቫል ጊዜም ሆነ ከዚያ በፊት የተፈጸሙ ነገሮችን እያነሳ ሁሉም አካል ማታገያ እና ማስለቀሻ አድርጓቸው ሊያስነሳቸው ይችላል! ስለዚህ ከሚኒሊክ የተነሳው የታሪክ አተራረክዎ እምብዛም አሁን ለምንፈልገው የብሄራዊ ውይይት ቀራራቢ አይሆንም” ብለዋል!

Source – ESAT