በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተካሄደ 18 ሺህ 851 የናሙና ምርመራ 1472 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

የጤና ሚንስትር እና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም በሰጡት መግለጫ መሠረት፤ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 42 ሺህ 143 ደርሷል።

በአንድ ቀን 14 ተጨማሪ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 692 መድረሱ ተገልጿል።

ተጨማሪ 267 ሰዎች ከበሽታው አገግመው፤ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 262 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 775 ሺህ 908 ናሙና ላይ ምርመራ ተካሂዷል።

አሐዝ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ18 ሺህ 851 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 472 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

August 24, 2020Konjit Sitotaw

Image