August 24, 2020 – Konjit Sitotaw
ዶክተር ስዩም መስፍን ስዩምየሰላም ሚንስትር ድኤታው ያስተላለፉት መልዕክት–የሙታኖች ጩኸት
–
ያለፈዉ ዘመን የሰፈር ፖለቲከኞች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው፣ የፖለቲካ ሀሁ የሚጀምሩበት “X ጨቋኝ፣ ነፍጠኛ፣ ትምከተኛ ነው” “Y ነፍጠኛ ነዉ/ጨፍጫፊ ነው’’ የሚባሉ ሀረጎች ጠፉ ሲባል ዳግም አገርሽተዋል፡፡ ይሄን ጉዳይ አሁን ላይ በተደጋጋሚ ማስተጋባት በንጹሀን ላይ የተፈጸዉ ጥቃቱ ትክክል ነዉ፣ ምክንያት አለዉ፣ይቀጥል እንደማለት ነው፡፡ እነኝን ያረጁ ያፈጁ ትርክቶች አሁንላይ ማነሳት ለምን ተፈለገ?
–
የዚህ እሳቤ አቀንቃኞች/ሙታኖች እዚግባ የሚባል አማራጭ፣ ችግር ፈች ሀሳብ የላቸዉም፡፡ ከ60 አመት በኋላ ዘመኑን የዋጀ የመታገያ አጀንዳ ማመንጨት አልቻሉም፡፡ የበታችነት የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ ተዘፍቀዉ፣ እድሜ ልካቸዉን የአናሳ ፖለቲካ ያራምዳሉ፡፡ እንወክለዋለን የሚሉትን ማህበረሰብ የሚመጥን ሀሳብ የላቸውም፡፡ እነ ደጃች ደረሶ ዱኪ፣ደጃች ባልቻ፣ ፊትአዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባመላ)፣ራስ አበበ አረጋይ፣ ራስ ጎበና፣ ፊትአዉራሪ ገበየሁ የለፉበትን፣ ዋጋ የከፈሉበትን የማይመጥን እሳቤ ያራምዳሉ፡፡
–

የየእልት ተግባራቸዉም ያለፈውን በመክሰስ፣ በመሰረተ-ቢስ ትርክት ማልቀስና ማስለቀስ፣ በሴራ-ፖለቲካ መጠመድ ቀደምት አባቶቻችን የሰሩትን ማጠልሸት፣ ከተቻለም ማፈራረስና ማዉደም ከሆነ ቆይቷል፡፡ ትግላቸዉ ሁሌም ካላፈዉ ታሪክ፣ ህዝብ፣ መሪዎች፣ የስላጣኔ አሻራዎች ጋር ነዉ፡፡ ወደዃላ እንጅ ወደፊት አይታያቸውም፡፡ የወደፊት እይታ ቢኖራቸዉም እንደ አህያ ከ3 ሜትር አይዘልም፡፡
–
ስለ ሰላም፣ ስለ ብሄራዊ መግባባት፣ ስለ ሰብአዊነት፣ ስለልማትና ብልጽግና ቢወራ አይገባቸውም፡፡ ሁሌም ማጋጨት፣ መከፋፈል፣ ደም ማፋሰስ ይቀናቸዋል፣ ይቀላቸዋል፡፡ ምክንያቱም ስጋቸዉም፣ ነፍሳቸዉም፣ መንፈሳቸዉም ምንጩ፣ እድገቱ እና ህብረቱ ከብርሀን ጋር ሳይሆን ከጨላማ ነው፡፡ ሲለቀቁ ያዙኝ ልቀቁኝ ያበዛሉ፣ ለያዥ ለገናዥ ያስቸግራሉ፤ ጠበቅ ተደርገዉ ሲያዙም፣ የዴሞክራሲ ያለህ ብለዉ ይጮሀሉ፡፡ በሁለት በትር አይማቱ፣ በሁለት ዳኛ አይሟገቱ!
–
እመኑኝ የሴራ ፖለቲካ አራማጆች፣ የዉሸት ትርክት ቅልቦች፤ እጃቸዉ በንጹሀን ደም የተጨማለቀ ሰፈርተኞች እድሜያቸዉ አጭር ነዉ፡፡ ልክ እንደ ታረደ በሬ (J-evile) ነፍሳቸዉ እስኪወጣ የሚጣጣሩ፣ የሚንፈራገጡ በቁማቸዉ የሞቱ ሙታኖች ናቸው፡፡ በመከሩት ምክር፣ በሸመቁት ጦር ይጠፋሉ፣ ይጠፋፋሉ፡፡ እነሱ ይራገፈሉ፤ እኛም ወደፊት እንገሰግሳለን፡፡ የወደፊቱን ጉዞአችንን የመግታት አቅም ፍጹም የላቸውም፡፡