August 25, 2020 – Konjit Sitotaw
በጥናቱ ከተሳተፉ 10 ኢትዮጵያዊን ሰባቱ ማለትም 69 በመቶ የሚሆኑት ህገ መንግሥቱ እንዲሻሻል ይፈልጋሉ ።
–
አፍሮ ባሮ ሜትር የተሰኘው ትኩረቱን በህግ እና ፌደራሊዝም ጉዳዮች ያደረገው የጥናት እና ምርምር ተቋም ከፍሪደም ሀውስ ጋር በትብብር ያጠናውን ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
–
7 out of 10 Ethiopians support amending the Constitution, while only 11% want it to be discarded or replaced and 18% say it should be kept unchanged, Afro Barometer new survey in Ethiopia.–

ጥናቱን የመንግስት ተወካዮች፣መገናኛ ብዙሃን ፣የህግ እና የፌደራሊዝም ምሁራን በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።ጥናቱ የሕገ መንግስት መሻሻል ጉዳይ፣የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች ብዛት፣አንቀጽ 39 ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የስልጣን ዘመን፣ የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ እና ሌሎች ጉዳዮች በጥናቱ ለተሳተፉ ዜጎች የቀረቡ ጥያቄዎች ናቸው።በዚህ ጥናት ላይ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ 2 ሺህ 400 ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ሲሆን ጥናቱ እና ቀለመጠይቁ ከ6 ወር በፊት መካሄዱም ተገልጿል።–የጥናቱ አቅራቢ እና በኢትዮጵያ የአፍሮ ባሮ ሜትር ናሽናል ፓርትነር አቶ ሙሉ ተካ እንዳሉት በጥናቱ ከተሳተፉ 10 ኢትዮጵያዊን ሰባቱ ማለትም 69 በመቶ የሚሆኑት ህገ መንግሥቱ እንዲሻሻል ይፈልጋሉ ብለዋል።–11 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ይህ ሕገ መንግስት ከነአካቴው መወገድ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።18 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህገ መንግሥቱ ባለበት መቀጠል አለበት ማለታቸው ተገልጿል።በፌዴራል መንግስት አሁን ካለው የስራ ቋንቋ ተጨማሪ የፌደራል የስራ ቋንቋ መካተት አለበት ያሉት 73 በመቶ ናቸው ተብሏል።

ሌላኛው በጥናቱ ለተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ጊዜ ነበር።በዚህም መሰረት 73 በመቶዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሁለት ምርጫ ጊዜ ብቻ እንዲያገለግሉ ይፈልጋሉ ተብሏል።የናሙናው መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰራ ወካይነት ያለው ሲሆን ፣ የስህተት ህዳጉ +/- 2 በመቶኛ ና አስተማማኝነት ደረጃው 95 በመቶ መሆኑ የአፍሮ ባሮ ሜትር ጥናት ቡድን አታውቋል።–ኢትዮጵያዊያን በፌዴራሊዝም ስምምነት ቢኖራቸው ብሄርን መሰረት ያደረገ ወይስ መልካ ምድርን አቀማመጥ የሚለው ልዩነት ጥናት ተደርጓል። 61 በመቶ በሀገሪቱ ከአህዳዊነት ይልቅ ፊዴራሊዝም መንግስት እንዲኖር የመረጡ ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉ 37 በመቶዎቹ ደግሞ ፌዴራሊዝም ከፍፋፋ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል።–እንዲሁም 49 በመቶ ብሄርን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያስፈልጋል ሲሉ 48 በመቶዎቹ ደግሞ የክልሎች አወቃቀር መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
