August 31, 2020 – Konjit Sitotaw
ያበደው እስክንድር ሳይሆን የኢትዮጵያ ፓለቲካ ነው – የእስክንድር ነጋ እውነት እያበራ ነው ! @dawit –

እስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ከገባ ግዜ ጀምሮ የተለያዩ ወዳጆቹ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እስክንድር በታገለው ደረጃ ለእሱ ድምፅ ማሰማት እንደ ሀፍረት ተቆጥሮ እንደ ፅንፈኛ እንደ ነብሰገዳይ ተቆጥሮ በሚያሳዝን ሁኔታ ይታሰር ወደሚል ድምዳሜ በመድረስ እስክንድርን ያለሀጢያቱ እስር ቤት እንዲቆይ የኢትዮጵያ ህዝብ ፈርዶበት ነበር !
–
እስክንድር ነጋ እውነት ስላለ ግን ትናንት እሱ ሲታሰር ሲያጨበጭቡ የነበሩት እነ ኢዜማ ሳይቀር ከረፈደም ቢሆን የእስክንድርን እውነተኛነት በማስረጃ አስደግፈው አረጋግጠዋል ::
–
በጣም የሚያሳዝነው እስክንድርን ለብዙ አመታት የሚያውቁት እነ ታማኝ በየነ እነ ሲሳይ አጌና እነ አንዷለም አራጌ ስለ እስክንድር ድምፃቸውን ሳያሰሙ በአላማ ፍፁም የማይገናኜው ጃዋር መሀመድ ብቻውን አጀንዳ ቀርፆ እውነትን ይዞ የመንግስትን አስተዳደር ያንቀጠቀጠ ፓለቲከኛ ነው መንግስት በእስክንድር ላይ የሚያደርገውን አፈና ሊያቆም ይገባል በማለት ስለ እስክንድር እንዲህ የሚል ምስክርነቱን ሳይፈራ ሰቷል ::
–
እስክንድር ጋር እውነት ስላለ አይደለም በአላማ አንድ የሆነ ሰው ቀርቶ በሀሳብ ተቃራኒ የሆነ ሰው እንኳ የሚመሰክርለት እንደ ብዙዎቹ ፓለቲከኞች ነጋዴ ሳይሆን እውነተኛ የህዝብ ተቆርቋሪ ለህዝብ መብት እና ዲሞክራሲ የሚታገል የህዝብ ልጅ ነው :: እስክንድርን ወደ አንድ ፅንፍ ለመክተት ብዙ ተሞክራል ! እስክንድር ግን ኢትዮጵያዊ ነው እስክንድር ትናንት የመጣ ታጋይ አይደለም ብዙ ብዙ ዋጋ የከፈለ በኢትዮጵያዊነቱ በፍፁም የማይደራደር አንባገነንነትን የማይቀበል እውነትን አጥብቆ የያዘ ሁሌም እውነት ነፃ የምታወጣው የዲሞክራሲ ታጋይ ነው እስክንድር ነጋ !
–
በሚገርም ሁኔታ እየተከታተለ የታከለ ኡማን አስተዳደር ሴራ ሲያጋልጥ ሲቃወም እስክንድርን ወደ እብደት እያመራ ነው የሚል ትችቶች በብዛት ይደመጡ ነበር ! ነገር ግን እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና እብዱ ማን እንደሆን በተግባር እስክንድር አስመስክሯል !
–
እስክንድር እንደ ጃዋር መሀመድ ህዝብ ወቶ በተለያዩ አለማት ድምፅ ባያሰማለትም የአዲስ አበባ ህዝብ ፍትህ ለእስክንድር ብሎ ድምፅ ባያሰማም እስክንድር ነጋ ግን በያዘው እውነት አንድ ብቻውን መንግስትን አሸንፎ ከእሱ ጋ እውነት እንዳለ ሲቃውሙት ነበሩትን ጭምር ማሳመን የቻለ ብርቱ የዲሞክራሲ ታጋይ ነው !
–
እስክንድር ነጋ ከማንኛቸውም የፓለቲካ ፓርቲዎች ይልቅ ብልፅግና ውስጥ ያለ የሴራ ድብቅ አጀንዳዎችን ቀድሞ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ አንድ ባንድ ነጥብ በነጥብ ሲተገበሩ አይተናል ! ታዲያ እስክንድርን ነጋን ማክበር ማድመጥ ስለ እስክንድር ፍትህን መጠየቅ አይገባም ወይ ?
–
ፍትህ በገጀራ ሳይሆን በብእር ለታገለው እስክንድር ነጋ — @dawit
–