September 2, 2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,105 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,360 የላብራቶሪ ምርመራ 1,105 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 416 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 54,409 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 846 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 19,903 ደርሷል።